Ethiopia | የኪነ ሀውልት ስራው ሠዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን ነው::
ከኪነህንፃው እስከ ኪነ ሐውልቱ ድረስ የከያኒያን የእውቀትና የጥበብ አሻራ ያረፈበት ቤተመጽሐፍት
(ይትባረክ ዋለልኝ)
ትላንት የተመረቀው ቤተ መጻሕፍት ‹አብርሆት Enlightenment› ይሰኛል። ቤተመፅሐፍቱ ከውጭ ጀምሮ ከኪነህንፃው እስከ ኪነ ሐውልቱ ድረስ የከያኒያን የእውቀትና የጥበብ አሻራ ያረፈበት ቤተመፅሐፍት ነው:: በተለይ በአውሮፓ አገሮች ውስጥ የሚገነቡ ህንፃዎችና ሁል ጊዜ እንደቀናሁ ነበር የኖርኩት:: አብርሆት ቤተመፅሐፍ ህንፃው ከውጫዊ ገፅታው ጨምሮ የቤተመፅሐፋን ሃሳብና ርዕይ መሰረት አድርጎ እንደተሰራ ያመለክታል:: በሌላው ሐገር የምንቀናው የሐገርን ቁሳዊና መንፈሳዊ እሴትን የያዘ የህንፃ ግንባታን በአብርሆት ቤተመፅሐፍ ላይ መመልከታችን ነገ ለኪነ ህንፃ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን በመንግስትም ሆነ በግል ለሚሰሩ የህንፃ ግንባታዎች እንደ ማዕዘን ድንጋይ እንዲቆጠር ያደርገዋል ::

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ትላንት በምርቃቱ ላይ ስለ ቤተመፅሐፍቱ ዓላማና ኪነህንፃውን አስመልክተው ሲናገሩ “ከሥነ ሕንጻው ጀምሮ ዕውቀትንና ታሪክን እንዲያንጸባርቅ ተደርጎ የተገነባ ነው። ‹አብርሆት ቤተመፅሐፍ ዋና ዓላማውም እውነትና ዕውቀት ነጻ የሚያወጣውን ማኅበረሰብ ለመመሥረት ስለሆነ ነው።
ኢትዮጵያ ለልጆቿ የሥልጣኔን መንገድ መርጣለች። ለጠላቶቿ ደግሞ ክንደ ብርቱ ሆና ትጠብቃቸዋለች። የሥልጣኔው መንገድ ደግሞ መማር፣ መመራመር፣ መወያየት፣ መከራከር፣ በሐሳብ መሸናነፍ፣ ዕውቀትን ማነፍነፍ፣ በአመክንዮ፣ በማስረጃና በመረጃ ላይ መመሥረት ናቸው። ” ነበር ያሉት ::
ሌለው አብርሆት ቤተመፅሐፍ ደጅ ላይ የቆመውን ኪነ ሐውልት ሰራው ነው:: ይህ የኪነ ሐውልት ስራ ለህንፃውና ለቤተመፅሐፍቱ ግዙፍ ጌጥና ውበት እንዲላበስ አድርጎታል:: ይህንየኪነ ሐውልት ስራ የሰራው ሰዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን ነው:: በቀለ መኮንን ሐገራችን ካሏት የኪነሐውልት ስራ በለሙያዎች መካከል አንዱ ነው::

ስለዚህ የኪነ ሃውልት ትርጏሜና አጠቃላይ ስራውን በተመለከተ እንዲነግረኝ በስልክ ጠይቄው ነበር:: በቀለ መኮንንም አጠቃላይ ስለኪነ ሀውልቱ ያዘጋጀሁት ፁሑፍ ስላለ ለምን አልክልህም አልኝ :: እኔም የላከልኝ ፁሑፍ ይሄው ለእናንተ አድርሻለሁ::
“በአዲሱ የአብርሆት የህዝብ ቤተመፃሕፍት ደጃፍ የቆመው ኪነ ሀውልት በቅርፁ ፣ የስነውበትን ደስታ በሚፈጥር ቀረፃና የልጅነትን ደፋር ነፃነት ባጣመረ መልክ የተዋቀረ ነው። ከቅርብም ከሩቅም በሰዎች መተላለፊያ መንገድ ዳር በመሆኑ ለሁሉም አይኖች የተጋለጠ ነው።
ወደ መፃሕፍት ቤቱ ዘልቀው ኮስታራ ንባብ ከመጀመራቸው በፊት ሁሉም ተመልካቾች ባለፉበት የልጅነት ወራት ተናፋቂና አስገራሚ ድርጊት ዘና የሚሉበትን ዕድል እንዲፈጥር ሆን ተብሎ የተመረጠ ነው ይዘቱ ።
ከነሀስ ቀልጦ የተሰራው ህፃን በልጅነት ነፃነቱ ከዚህ ዓለም ማናቸውም ተፅዕኖ ነፃ ስለሆነ ነባር የዕውቀትና የመረጃ ክምር ላይ ተኝቶ ባደግንባቸው ፊደልና ቁጥር የተሰራ ሉል/ ዓለም ጋር ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዟል። ይጠይቃል ይገረማል ይፈልጋል።እያደር ሲጎለምስ የሚፈራውን ገለባብጦና ተገለባብጦ ራሱንና አካባቢውን የማየት ድፍረት በዚች ዕድሜ ላይ ጀምራ እዛው ላይ የምታበቃ ድንቅ የቅፅበት ዘመን ናት።
ሁሉም ሰው ኋላ ተመሳሳይ ሰልፍ ውስጥ መግባቱ ባይቀርም ከርሞ በሚያጣው በነፃነቱ ዘመን የታደለውን ተሰጥዖ በዚህ ቅርፅ ውስጥ ማስቀረት ዋናው የዚህ ቅርፅ ዒላማ ነው ። የቅርፁ ትልቅ ተሸካሚ መሠረት ደግሞ እንደተፈጠረ የተተወ ትልቅ አለት ሲሆን ( subliminal )ውበትን ከሌላው የኤስቴቲክ ቀመር ጋር እንዲያዋህድና ግርምታን እንዲጨምር የተመረጠ ነው ።
ህፃኑና የፊደል ሉል ደግሞ በቀለም ፣በመጠን በቴክስቸር፣ በእይታ ክብደትና ቅለት ተናበው የተቀናበሩ የቅርፁ ይዘትና ቅርፅ ተጫዋችና አጫዋች ኤለመንቶች ናቸው።
በቀለ መኮንን 2021
በቄ እንኳን ደስ ያለህ!!
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ