ፎቶ – ትግራይ የመከላከያ ሰራዊት እህል አጭደው በሚከምሩበት ወቅት
” አይሰራም” አንድ – መንግስት ከባድ መሳሪያ የታጠቀ፣ መድፍና ታንክ የተሸከመ፣ ከፍተኛ ሰራዊት የገነባ ሃይል በህገ መንግስቱ መሰረት ስለማይፈቀድ ትህነግ መሳሪያውን ያስረክብ፣ ወታደሩን ይበትን ባይ ነው።
“አይሰራም” ሁለት – በሰጥቶ መቀበል ህግ መሰረት መሳሪያ መፍታትና ሰራዊት መበተን የሚባለው ጉዳይ ተቀባይነት እንደሌለው ትህነግ በመመሪው አማካይነት አስታውቋል።
“አይሰራም” ሶስት – አማራ ክልልም ሆነ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ አማራ ክልል ድርድር ብሎ ነገር እንደማይታሰብ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደሮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አገነሁ አስገብተዋል። ራሳቸውን ችለው በጀት እንዲሰታቸውና ወሰናቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።
የትግራይ ሕዝብን ከኢትዮጵያ ነጻ ለማውጣት እታገላለሁ የሚለው ትህነግ ከተፈጠረ አርባ ሰባት ዓመት ሆነው። ከአርባ ሰባት ዓመቱ ውስጥ ኢትዮጵያን ሃያ ሰባት ዓመት ሲገዛ ትግራይን ነጻ ለማውጣት ካለው ዓላማ አንጻር ማንም ከላካይ ስላልነበረው ከሚጠራበት ስም ጋር በተያያዘ የትግባር እርምጃ ይወስዳል በሚል የሚያምነው የለም። እንደውም አሁን አሁን “ግልግል ነው። ሂድ” የሚሉ በርከተዋል።
ከለውጡ ጋር ተያይዞ ወደ ትግራይ በመመለስ ሰፊ ጦር ያደራጀውና የኢትዮጵያን መሳሪያ ሙሉ በሙሉ የታጠቀው ትህነግ የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ” መብረቃዊ ጥቃት” ያለውን የክህደት እርምጃ ከውሰደ በሁዋላ የወጡት መረጃዎችና አሁን ድረስ በየአቅጣጫው ከሚሰሙት ዜናዎች ጋር በተያያዘ “እነሱም ይረፉ፣ እኛም እንረፍ” የሚሉ በዝተዋል።
አንድ ትውልድ ተወልዶ እስኪያረጅ ድረስ ከትህነግ ጋር በተያያዘ መከራውን የሚያይበት፣ ሰላሙን የሚያጣበት ምክንያት ሊኖር አይገባምና እንደስማቸው ” ይሰናበቱ” የሚሉ በበረከቱበት ወቅት አማራ ክልል የተፈጸመው ጉድ ይፋ መሆኑ ትህነግ ከኢትዮጵያ ጋር ውል የቀደደ ሆኗል። ከአፋርም ጋር ላይታረቅ ተለያይቷል።
የተፈጠሩበትን 47ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ተጀምሯል በተባለው የሰላም ድርድር ትህነግ “መሳሪያ ፍታ” የሚለው ቅድመ ሁኔታ እንደተቀመጠለት፣ ሃይሉንም በትን መባሉን አምኗል። ሊቀመንበሩ ዶክተር ደብረጽዮን እንዳሉት በአምስት ጉዳዮች ” ሰጥቶ መቀበል” የሚባለው የድርድር መርህ አይሰራም። በተመሳሳይ የአማራ ክልል “አይሰራም” ሲል በቀይ መስመር ያሰመረበት ጉዳይ ከደብረጽዮን “አይሰራም” ጋር አንድ ሆኗል።
ሶስት አይሰራሞች
” አይሰራም” አንድ – መንግስት ከባድ መሳሪያ የታጠቀ፣ መድፍና ታንክ የተሸከመ፣ ከፍተኛ ሰራዊት የገነባ ሃይል በህገ መንግስቱ መሰረት ስለማይፈቀድ ትህነግ መሳሪያውን ያስረክብ፣ ወታደሩን ይበትን ባይ ነው።
“አይሰራም” ሁለት – በሰጥቶ መቀበል ህግ መሰረት መሳሪያ መፍታትና ሰራዊት መበተን የሚባለው ጉዳይ ተቀባይነት እንደሌለው ትህነግ በመመሪው አማካይነት አስታውቋል።
“አይሰራም” ሶስት – አማራ ክልልም ሆነ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ አማራ ክልል ድርድር ብሎ ነገር እንደማይታሰብ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደሮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አገነሁ አስገብተዋል። ራሳቸውን ችለው በጀት እንዲሰታቸውና ወሰናቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።
ትህነግና አምስቱ ምህላው
ትህነግ ይፋ ያደረጋቸውና ለድርድር የማይቀርቡ ካላቸው አምስት ጉዳዮች መካከል በትግርኛ ከተናገሩትና ቢቢሲ ከተረጎመው ቃል በቃል “በመጀመሪያ ደረጃ በሠራዊታችን ላይ አንደራደርም። አሁን ያለው ብቻ ሳይሆን ገና እንጨምርበታለን ስለዚህ በሠራዊታችን ጉዳይ ላይ አንደራደርም። ከዚህ በኋላም ኃይላችንን ይዘን ነው የምንኖረው” ማለታቸው፣ የትግራይ ድንበር ከጦርነቱ በፊት እንደሚሆን (ወልቃይት ጠገዴን አካቶ)፣ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ለቆ መውጣቱ፣ የትግራይ ሕዝብ ሪፈረንደምና ወንጀል የፈጸሙ ለጥያቄ መቅረባቸው ላይ ድርድር የለም።
ትህነግ በዚህ መልኩ ስለ ድርድሩ ባስቀመጠው አቋሙ መሰረት ወልቃይት ጠገዴን በጠረጴዛ ዙሪያ የሚሰጠው ባለመኖሩ ወደ ማይቀረው ጦርነት ለመምራት ዝግጅት ላይ መሆኑንን አመልክቷል። 300 ሺህ ሰራዊቱ የት እንደገቡበት እንደማይታወቅ ገልጾ መንግስትን የከሰሰው የትህነግ የወጣቶች አደረጃጀት ከአማራ ክልል ጋር ለሚደረገው ቀጣይ ጦርነት ምን ያህል ሰራዊት እንዳዘጋጁ ወደፊት ይፋ ያደርግ ካልሆነ በቀር ለአቤቱታ ያመች ዘንድ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
የመንግስት ቅድመ ሁኔታና የተደፋበት መከራ
ከትህነግ ጋር የገጠውመ ጦርነት በአይነቱም ሆነ በይዘቱ አስገራሚ እንደሆነ በርካቶች በሃዘን ይገልጻሉ። መንግስት የሚወጉትን ያበላል። ነዳጅ ይልክላቸዋል። ከባድ ተሽከርካሪ ያደርስላቸዋል። ገንዘብና ቁሳቁስ ያስተላልፋል። መልሶ ከነሱ ጋር ይዋጋል። ይህን ሁሉ አላደረግም ካለ ጉልበተኞቹ አፍንጫውን ይዘው ያስገድዱታል። አለያም በድህነቱ ላይ ሰንሰለት አክለውበት ያጎብጡታል። ይከሱታል። ይወነጅሉታል። የታየውም ይህ ነው።
“ቆልማጣው” የሚባለው ትህነግ ምንም ቢያደርግ የሚያወግዘው፣ ተው የሚለውና የሚያቅበው አካል በለመኖሩ መንግስት ጨክኖ እንዳይወቅጠው መከራ ሆኖበታል። በርካቶች እንደሚሉት የማይደራደርበትን የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ትቶ አፋር ክልል ምስኪኖች ላይ የሚደነሰው ለዚህ ነው። የተማመነውን ተማምኖ ነው። አፋር 300 ሺህ ሰዎችን ሲያፈናቅል ” ተው” ያለ የለም።
ይህ ሁሉ እየሆነ የሰላም እንቅስቃሴ ንግግር ተጀምሯል። ኦባሳንጆ ትግራይ ሲመላለሱ ያቀረቡት ጥያቄ አንድና አንድ ነው። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት ትህነግ መሳሪያውን ፈቶ ለድርድር እንዲቀመጥ መንግስት ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ መቀበል። ሰራዊቱን ጥትቅ ማስፈታት ብቻ ሳይሆን ራሱ ትህነግ ስልጣል ላይ በነበረበት ወቅት ሲመከር እምቢ ብሎ የመሸነፊያውን ሰነድ ይዞ ባልጀርስ ድርድር በተሸነፈው መሰረት ባድመ አካባቢ ለኤርትራ የተወሰነውን ስፍራ ማስረከብ፣ ለሰላም ሂደቱ ቅድመ ሁኔታ ሆነው የቀረቡ ናቸው።
ትህነግ ድንበር ሲተብቅ የነበረውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ካረደ በሁዋላ የኤርትራ ሃይሎች ይገባናል ያሉትንና ይጋባኝ የሌለው የአልጀርስ ውሳኔ ያጎናጸፋቸውን መብት ተግባራዊ አድርገዋል። እናም መንግስት ይህን የትግራይ ጥያቄ በምን አግባብ ሊያስተናግደው እንደሚችል ግራ እንደሚሆን ለትህነግ መሪዎች ተገልጾላቸዋል። የኤርትራ መንግስትም በአፈሳጸም ጉዳይ ብቻ ከፌደራሉ መንግስት ጋር ካልሆነ በስተቀር በዚህ ጉዳይ ከትህነግ ጋር ለመነጋገር ጨርሶ አልሞት እንደማያውቅ ተመልክቷል።
ትህነግ ከቶውንም ከማይደራደርባቸው ጉዳዮች መካከል ብሎ ካነሳቸው ውስጥ የኤርትራ፣ የወልቃይት ጠገዴና የሪፈረንደም ጥያቄዎች ማሟሟቂያ ሲሆኑ ዋናው ስጋት ጦር የመፍታቱ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ” የሰሜኑ ኮሪዶር አይከፈትም፤ እዛ ላይ ቀልድ የለም። ለሰኮን አንተኛም። ሃይላችን ሁሌም ዝግጁ ነው” ሲሉ የመንግስት ቀይ መስመር መሆኑን ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ወልቃይት ጠገዴ – “በሃይል ተነጥቆ፣ በሃይል የተመለሰ ምድር ለድርድር አይቀርብም”
በወልቃይት-ጠገዴ የማንነት ኮሚቴ ሰብሳቢና የዞኑ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እንዲሁም የሰሜን ምዕራብ ጎንደር የወልቃይት-ጠገዴ የሰላም አምባሳደር አባ ዳዊት አማረ የተመራ ቡድን በወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ጉዳይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በማግኘት በአዲስ አበባ ውይይት ሲያደርግ መሰነበቱ የተሰማው ሰሞኑንን ነው።
ውይይቱ የፌድሬሽን ም/ቤት፣የማንነትና ወሰን ኮሚሽን፣የገንዘብ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይና ም/ጠ/ሚኒስትር ተራ በተራ በቢሯቸው በማግኘት ነበር የተካሄደው።
ሙሁራን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ያሉበት በወልቃይት-ጠገዴ የማንነት ኮሚቴ የተመራው ቡድን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ጨምሮ የተለያዩ ተጨማሪ ባለድርሻ አካላትን በማግኘት ውይይት አድርገዋል።
የማንነቱ እውቅና ጉዳይ፣ የበጀት ጉዳይ ፣ የመብራትና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ጉዳይ በዋናነት ያተኮረ ንግግር ሲሆን ጉዳዩን በህግ መደበኛ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። ሕዝቡም ሙሉ እሙሉ ወታደር ሆኖ ” በጉልበት የተቀማ፣ በጉልበት ተመልሷል” በሚል ተመሳሳይ አቋም በመያዝ ወልቃይት ጠገዴ “ቀይ መስመር” ነው ብሏል።
ትህነግ የመንግስትነት ወግ ሲሰጠው ቀደም ሲል የነበረውን ካርታ ቀይሮ እንደወሰደው ክስ የሚቀርበበት ወልቃይት ጠገዴ ልክ ትህነግ እንዳደረገው የህግና የድንበር ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ ጥያቄ እየቀረበ ነው። ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ አማራ ክልል ሰፊ ሃይል እየገነባ ሲሆን መከላከያም ድጋፍ ማድረግ ግድ ስለሚሆንበት የሃይል አማራጩ ብዙም እንደማያስኬደው አስተያየት የሚሰጡ አሉ።
በዚህ የሶስት ” አይሰራም” አቋም እንዴት ሰላም ይመጣል? የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል። ተስፋም የለውም። ትግራይ ሪፈረንደም ከማድረጓ በፊት የሃይማኖት ተቋሞቿ ከፌደራሉ አካላቸው መገንጠላቸውን አውጀዋል። የሚገርመው ሕዝብ ወሬውን እንደ ወሬ ከመስማት በዘለለ ምላሽ አልሰተም። የሃይማኖት ተቋማቱም ብዙም ያሳሰባቸው አይመስሉም።
ትህነግ እየበጣጠሰ ከሚያስገነጥላቸው አንደናውን ለምን የትግራይን ሕዝብ ፈቃድ ካገኘ ለምን ስንብት እንደማያውጅ በረካቶች በመገረም ይጠይቃሉ። በትህነግና በሌሎች የአገሪቱ ሕዝብ መካከል የተፈጠረው ግንብ እንዲሁ በቀላሉ የሚናድ ባለመሆኑ ጉዳዩን ለማለዘብ አዳጋች እንደሆነ የሚገልጹ በቅርቡ አምነስቲ ያወጣውና ገና ሁሉንም አካባቢዎች ያላካተተው ሪፖርት ምን ይዞ እንደሚመጣ በርግጠኛነት መናገር አልቻሉም።
የትህነግ አመራኦች ያሰማሩዋቸው ወራሪዎች በአማራ ክልል የጦር ወነጀል ስለመፈጸማቸው የቀረበው ሪፖርት፣ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሃፊ ይህንኑ ጉዳይ ማየታቸው፣ አሁንም ከፍተና የተባበሩት መንግስታት ሃላፊዎች አማራ ክልልን እየዞሩ መሆኑ፣ ቀደም ሲል የቀረቡ ሪፖርቶች፣ ዲፕሎማሲው መሻሻሉና ኢትዮጵያ ላይ የነበረው ጫና መላዘቡ፣ አሁን ላይ በአፋር እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋና መፈናቀል፣ በኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ላይ ግድያ፣ ዘረፋና አፈና መካሄዱ አንድ ላይ ተዳምሮ ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ትህነግ ላይ ምን ዓይነት የአቋም ለውጥ ያደርጋል? የሚለውና መንግስት እያሳየ ያለው ከልክ ያለፈ ትዕግስት ምንክንያቱ ምንን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ በስፋት እያነጋገረ ነው።