ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከቻይና ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ በጋራ ሰሜን ሸዋ በለሚና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ያሉ ሦስት ፋብሪካዎችን ወደ ስድስት በማሳደግ የኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሸጋገር ከስምምነት ላይ ደረሱ። ኢትዮጵያ ምንም ሳንቲም ሳታወጣ 600 ሚሊዮን ዶላር ለግንባታው ይውላል። 2 ቢልዮን ዶላር አጠቃላይ በጀት ተያዟል።
በለሚ በቀን አስር ሺህ ቶን ሲሚንቶ፣ ሰላሳ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር ጂፕሰን የማምረት እንዲሁም በድሬደዋ በቀን 3500 ቶን ሲሚንቶ፣ እንዲሁም ቀደም ሲል ያመርት የነበረውን ኩባንያ ሰላሳ በመቶ ምርቱን ለማሳደግና ወደ ኤክስፖርት ለመሸጋገር እየተሰራ መሆኑንን የቻይናው ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ ዋና ስራ አስኪያክ አመልክተዋል። በቋሚነት ለ5000፣ በተዘዋዋሪ ለሃያ ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚያመቻችም አስታውቀዋል።
የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ሊቀመንበር ዶክተር ብዙዓለም ታደለ በለሚ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ ከዚህ በፊት የተጀመሩ ሦስት ፕሮጀክቶችን ወደ ስድስት ፕሮጀክቶች በማሸጋገር ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክነት እንዲቀየር ለማድረግ የተደረገዉ ስምምነት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።
በለሚ በቀን አስር ሺህ ቶን ሲሚንቶ፣ ሰላሳ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር ጂፕሰን የማምረት እንዲሁም በድሬደዋ በቀን 3500 ቶን ሲሚንቶ፣ እንዲሁም ቀደም ሲል ያመርት የነበረውን ኩባንያ ሰላሳ በመቶ ምርቱን ለማሳደግና ወደ ኤክስፖርት ለመሸጋገር እየተሰራ መሆኑንን የቻይናው ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ ዋና ስራ አስኪያክ አመልክተዋል። በቋሚነት ለ5000፣ በተዘዋዋሪ ለሃያ ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚያመቻችም አስታውቀዋል።
ይህ ስምምነትም ሀገሪቱ በኢንዱስትሪ ዘርፍ አመርቂ ውጤት በማምጣት ከተሻሉ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ድርሻ ይኖረዋል ሲሉ ዶክተር ብዙዓለም ታደለ አመልክተዋል። አያይዘውም ይህን ግዙፍ ፕሮጀክ “የእኔ” የሚለው ባለቤት እንደሚያስፈለገው ደጋግመው አስታውቀዋል። በእኔነት ስሜት፣ በሁሉም ዓይነት ትብብርና ድጋፍ አንድ በመሆን ሊሰራ እንደሚገባም አመልክተዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ከፍያለው ቢሮክራሲው አስቸጋሪ ቢሆንም በመግፋት፣ የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሙም በመታገል ተደጋግፎ በሁሉም መስክ መስራት እንደሚገባ አመልክተው፣ ድህነትን ለመሸጋገር “ኑና አብረን አገራችንን እናልማ፣ አብረን እንታገል፣ አብረን የህዝባችንን ኑሮ ለለወጥ እንትጋ። ችግራችንን በጋር እንቅረፍ” ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል። የአመለካከትና የአሰራር ባህል ሊቀየር እንደሚገባም ጠቁመዋል። ይህን ለማድረግም ቃል ገብተዋል።
በሲሚንቶና ተያያዥ ምርቶች ላይ በጋራ ሲሠሩ የነበሩት ተቋማት በኹለቱ ከተሞች ያሉትን ፕሮጀክቶች ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሳደግ መስማማታቸዉ በአገር ደረጃ ጠቀሜታው ትልቅ በመሆኑ ሁሉም ወገን ሊደግፍ እንድሚገባ በስነ ስራአቱ ላይ የተገኙት የኢስት ዊስት ሆልዲንግ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሃይለማሪያም ሰዳለኝ ገልጸዋል።
እስካኹን ሲሚንቶና ጅፕሰም የሚያመርቱ ፕሮጀክት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። የአማራ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለፕሮጀክቱ መስፋፋት ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል። አኹን ላይ ተግባራዊ ለሚደረጉት ስድስት ፕሮጀክቶች አጠቃላይ 600 ሚለየን ዶላር በጀት ቢመደብም ሁለቱ ድርጅቶች በጋር ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ኢንቨስትመንት እውን እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።
ሁለቱ ኩባንያዎች በኢትዮጽያ በጋራ ለሚያከናውኑት ፕሮጀክት ደግሞ 2 ቢሊየን ዶላር ወጭ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሲገለጽ ዝርዝሩ ይፋ ባይሆንም ቀጣይ ፕሮጀክቶች በሂደት ይፋ እንደሚደረግ ተመልክቷል። ይህ ፕሮጀክት ከፍተኛ የኾነ የውጭ ምንዛሬ ሳናወጣ በሀገር ውስጥ ጥሬ እቃዎች ወደ ምርት የሚገባ መኾኑን ተናግረዋል። ሀገራዊ ቱሩፋቶቻችንን መጠቀም እንደሚገባ አቶ ሃይለማሪያም አስታወቀዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ኹለቱ ኩባንያዎች በለሚ እና በድሬዳዋ እያከናዉኑ ያሏቸዉ ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን በመጥቀስ ምሥጋና አቅርበዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በጋራ እንዳለፈች ኹሉ ድህነት ለማሸነፍ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ለሚን መርጣችሁ ወደ ክልላችን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በኢትዮጵያ ያሉ ኩባንያዎች የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል። በመንግሥት በኩልም ከሕዝብ ጋር በመኾን ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ እንሠራለንም ነው ያሉት። ክልሉም የፕሮጀክቱ ሥራ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነቱን ወስዶ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
አማራ ክልል ሰፊ ለኢንቨስትመንት የሚኾን ሀብት ያለዉ በመሆኑ ባለሃብቶች በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን ብለዋል ርእሰ መሥተዳደሩ። ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ ዋና ቢሮውን ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ አበባ ማዛወሩም ታውቋል።
የዜናው መነሻ አሚኮ ሲሆን በዜናው ያልተካተቱ ተጨማሪ መረጃዎች ተካተዋል