አሜሪካ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል ማስታወቋን ተከትሎ ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ ማድረጓን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።
የቻይና ጦር ቃል አቀባይ በትናትናው እለት እንዳስታወቀው፤ ቻይና እራሷን በራስዋ የምታስተዳድር ደሴት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ለማሳየት በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን አድርጋለች።
የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን እና ሌሎች የስልጠናዎችን በባህር እና አየር ላይ ማካሄዱንም የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረዋል።
ልምምዱ አሜሪካ ለታይዋን እውቅና ለመስጠት እያደረገችው ላለው እንቅሰቃሴ “ከባድ ማስጠንቀቂያ” መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።
ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ጭምር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ስትገባ ይታያል።
ባሳለፍነው ሳምንት በእስያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኀገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው ይታወሳል።
ባይደን ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም ብለዋል፤ የንሰጠው መልስ ለሩሲያ እንደሰተነው አይደለም ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። በጋዜጣ መግለጫቸው ወቅት ጠያቂው ደግሞ ሲጠይቃቸው ” አዎ ወታደራዊ እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጅንፒንግ ከወራ በፊት ታይዋንን ከቻይና ጋር ለማዋሃድ መዛታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንቱ ለማዋሃድ ኃይል መጠቀም ስለማሰባቸው አልተናገሩም። ታይዋን ነጻ ሀገር ነኝ የምትል ሲሆን፤ በአንጻሩ ቻይና ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ ትመለከታታለች። በቅርቡ የተዋሃዱ አገር እንደሚሁኑ አስታውቃለች። ዜናው ከአል አይን የተደበላቀ ነው።
- Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack… I am trying not to be an alarmist, but there are a lot of things that have… Read more: Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
- U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near BerberaAccording Financial Times a U.S. official, discussions have begun regarding a potential deal that would involve the United States… Read more: U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near Berbera
- Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa ConferenceBy Beyene Gerezgher The Ethiopia branch of Brigade Nhamedu (also known as the Blue Revolution Movement) will host… Read more: Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa Conference