የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

Rising tensions and aggravating rhetoric grave risk to human rights situation in Northern Ethiopia
On all parties to the conflict, national actors, civil society organizations, the media, religious leaders, and other actors, to renew efforts for a peaceful …
ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።
ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።
ጦርነቱ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ እንግልት እንዲዳረጉ፣ የሚወዷቸውን ሰዎች እንዲያጡ፣ ህይወታቸውን በእርዳታ ላይ እንዲመሰረቱ፣ መሰረታዊ የዜጎች አገልግሎቶችን እንዲነፈጉ እና የሌሎችን ጉዳቶችን እያስተናገዱ እንደሚገኙም ተቋሙ ከዚህ በፊት ባደረኳቸው ተደጋጋሚ ምርመራዎች አረጋግጫለሁ ብሏል።
የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የሰሜን ኢትዮጵያ ሶስቱ ክልሎች ዋነኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ያለምንም ገደብ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ ማድረግ እንደነበርም ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።
ከዚህ በፊት በተካሄደው ጦርነት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ ሳይደረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ አጥፊዎች ሳይጠየቁ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ሳይጠገኑ እና ሌሎች አስፈላጊ ስራዎች መከናወን እያለባቸው ወደ ሌላ ጦርነት መግባት እንደሌለበት ገልጿል።
ምንጭ፦ አልዓይን / ኢሰመኮ