ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚንቀሳቀሱና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ አንድ መቶ አስራ አንድ ሕገ ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን መኖራቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የፌደራል ፖሊስ ሕገ ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃንን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፈቃድ ሳይኖራቸው የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ሕዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 ሕገ ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን መኖራቸውን ነው ያስታወቀው፡፡
ከዚህ ሕገ ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን መካከል በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ያላቸውን 10 ተጠርጣሪዎችን ለይቶ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ፌደራል ፖሊስቸ በዚሁ መግለጫው÷ ህብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት አሳስቦ፣ በሕገ ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሃይማኖት እና በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አካላትን በማጋለጥና ለሕግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታና የፍትሕ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የሕግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቀው፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል። ከዚህ ውስጥ በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን ለይቶ 10 (አስር) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው ይገኛል።
እነዚህ ግለሰቦች የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል።
ተቋሙ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸውና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ግለሰቦቹ የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሶበታል።
በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል።
ፖሊስም ህግን አክብረው በማይሰሩት ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይወዳል፡፡
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ያገኛውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት እያሳሰበ በህግ-ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሀይማኖት፣ በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አከላትን በማጋለጥና ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ለህዝብ ሲገለጽ እንደነበረው ከሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
- Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack… I am trying not to be an alarmist, but there are a lot of things that have happened over the last 16 months that I was previously led to believe would never happen. And the tension between… Read more: Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
- U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near BerberaAccording Financial Times a U.S. official, discussions have begun regarding a potential deal that would involve the United States recognizing Somaliland in exchange for establishing a military base near the strategic port of Berbera. This development, if confirmed, could… Read more: U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near Berbera
- Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa ConferenceBy Beyene Gerezgher The Ethiopia branch of Brigade Nhamedu (also known as the Blue Revolution Movement) will host a vital conference in Addis Ababa on January 25, 2025. The event will bring together Brigade Nhamedu leaders and representatives… Read more: Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa Conference
- Eritrea Is the North Korea of Africa: America Must ActThe U.S. Department of the Treasury should also tighten sanctions on Eritrean banks, financial institutions, and money transfer agencies such as Himbol. That an Eritrean ambassador identified Himbol’s operation is significant; that the Eritrean government scrambled to erase… Read more: Eritrea Is the North Korea of Africa: America Must Act