ከለውጡ በሁዋላ ኤርትራ አምባሳደር ሆነው የከረሙት ሬድዋን ሁሴን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። በምትካቸው ማን እንደሚሰየም እስካሁን ይፋ አልሆነም።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የተለያዩ ሹመት መስጠታቸውን ተከትሎ ነው አቶ ሬዲዋን አቶ ገዱን መተካታቸው የታወቀው። ይፋ በሆነው የሹመት ዜና ይፋ ባይነገርም ሹመቱ የማያሻማ ትርጉም እንዳለው ታውቋል። አቶ ገዱ የደህንነት አማካሪ ሆነው በፋኖ ስም በሚደራጀው አደረጃጀት ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ሲታሙ እንደነበር ይታወሳል።
በኢህአዴግ የምርጫ ዘመቻ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን አንጀት እንዳራሱ የሚነገርላቸው አቶ ሬድዋን እስካሁን በስልጣን መቆየታቸው በበርካቶች ዘንዳ ብልጽግና ከሚወቀስበት ጉዳይ አንዱ ነበር። አቶ ሬድዋን ህዝብ የሚወዳቸውን የተቃዋሚ አመራሮችንና አመለካከትን በማበሻቀጥ የሚታወቁ የቀድሞው ስረዓት ታማኝ እንድነበሩ በርካቶች ሲናገሩ ቆይተዋል። አሁን የተሰጣቸው ስልጣን ረጋ ብለው ስለ ጡርታቸው እንዲያስቡ የሚረዳቸው እንደሆነ ተገምቷል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ዳባ ደበሌ፣ የቀድሞ ኦሮሚያ ሊቀመንበር ሙክታር አይነት ሰዎችን መሸከሙ አሁንም ድረስ ብልጽግናን የሚያስወቅስ ነው።
ዛሬ ይፋ በሆነው ሹመት መሰረት አቶ ሄኖስ ወርቁ የነዳጅና ኢነርጂ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ካሊድ አብዱራሂማን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል፣ አቶ ወንደሙ ሴታ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸው ታውቋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል ዋና ኦዲተርነት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተርነት ወይዘሮ መሰረት ዳምጤን እንዲሁም አቶ አበራ ደምሴን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተርነት በማድረግ ሹመቱን እንዲያጸድቅላቸው መተየቃቸው ታውቋል።
- በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበትየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን በስራ ፈጣሪ ቅድሚያ የሚነሱትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና “ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ” የተባለ ኩባንያን ጨምሮ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን ለህዝብ በመሸጥ ገንዘብ ሲያሰባስቡ… Read more: በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበት
- ማንነት የሚሸጥና የሚቀየር አደለም – ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ“አሁን ለተገኘው ነጻነት መላው የአማራ ሕዝብ ዋጋ ከፍሎበታል” በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ስልጠና በትናትናው እለት ተጠናቋል። ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት… Read more: ማንነት የሚሸጥና የሚቀየር አደለም – ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
- የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት እና ልማት ቢሮ ኃላፊና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ተነሱየአዲስ አበባ ከተማ የመሬት እና ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ተሰማ። “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዶ መሬት ይዘወርበታል” ተብሎ የሚነገርለት ይህ ተቋም፤ የተለያዩ ኃላፊዎች ለአጭር… Read more: የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት እና ልማት ቢሮ ኃላፊና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ተነሱ
- “የፌደራል ፖሊስ ሀገራዊ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚችል ጠንካራ ተቋም መሆን ችሏል “የፌደራል ፖሊስ ባለፉት 7 ዓመታት ባደረገው ሪፎርም በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የተደራጀ፤ ፖሊሳዊ ተልእኮን መወጣት የሚችል ጠንካራ ተቋም መሆን ችሏል ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ተናገሩ። 116ኛው የኢትዮጵያ… Read more: “የፌደራል ፖሊስ ሀገራዊ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚችል ጠንካራ ተቋም መሆን ችሏል “