በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበሩና በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ህጋዊ እውቅና በሌላቸው 111 የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በኮሚሽኑ የታክቲክ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተደራጁና የሽብር ወንጀሎች፣ በሙስና፣ በፋይናንስና ንግድ ነክ፣ በታክስና ጉሙሩክ ወንጀሎች ላይ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ምርመራዎች ተከናውነዋል።
በዚህም መሰረት 2 ሺህ 668 ጥቆማዎችን በመቀበል 1 ሺህ 438 መዝገቦችን መርምሮ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መላካቸውንም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ሀገሪቱን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበሩና ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ስያሜ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ በነበሩ አካላት ላይ ክስ መመስረቱን ተናግረዋል፡፡
እነኚህ አካላት ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም በምርመራ መረጋገጡን ነው ያብራሩት።
መረጃ ተጣርቶባቸው ክስ የተመሰረተባቸው 111 የሚሆኑት የዲጂታል ሚዲያዎች በመገናኛ ብዘሃን ባለስልጣን ህጋዊ እውቅና እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜም የእነኚህ ህገወጥ የዲጂታል ሚዲያ ባለቤቶች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ በማጭበርበር የባንኮችን መልካም ስም የማጉደፍ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸውን ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ ከ57 ሚሊየን ብር በላይ መዝረፋቸው በምርመራ በመረጋገጡ ክስ ተመስርቶባቸዋል ነው ያሉት።
የፌደራል ፖሊስ የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በተለያዩ ክልሎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ የወንጀል ምርመራዎችን እንደሚያጣራ ገልጿል። OBN
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring