የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሰታወቀ።
በትግራይ ክልል በመቀሌ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሰታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በመቀሌ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ውሳኔን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ጥሬ ገንዘብ ወደ መቀሌ መላኩን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መግለሳቸው ይታወሳል።
ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዲጨምሩ፣ የባንክ አገልግሎት እንዲፋጠን እና ሌሎች እርስ በርስ መተማመንን የሚያጎለብቱ እና የዜጎችን አኗኗር የሚያቀሉ አገልግሎቶች እንዲፋጠኑም መመሪያ ማስተላለፋቸውም ይታወሳል። (ኢ ፕ ድ)