“በአንድ ልብ፤ በአንድ ሃሳብ የተወሰነ ነው” ሲሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ማስታወቃቸው ተዘገበ። ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተቀምጦ እያለ ተከበበ፣ በወታደሮች ትጥለቀለቀ፣ ህዝብ ሁኒታውን ተከታተል፣ በግድ የማይፈለጉ ሰዎችን እንዲሾም መሳሪያ ተመዞባቸዋል ….ወዘተ በሚል ዜና ሲሰራጭ ቢውልም፣ በስተመጨረሻ ውሳኔውም ሆነ ስብሰባው በምን መልኩ እንደተካሄደ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አመልክተዋል።
“ሁላችንም ተወያይተንበት፣ ቤተክርስቲያንን የሚጠቅማት ምንድነው? ብለን በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብ የወሰንነው ነው። በእውነት ደስ የሚል ነበር፤ ለዚህም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን” ሲሉ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ተናግረዋል።
አቡነ ጴጥሮስ አክለውም “ብዘዎች የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንደነበራችሁ እናውቃለን፤ አንዳንዴ እውነት ነው፤ ብዙ ጊዜ ግን ወሬ ይበዛዋል !… በዚህ ሚዲያ በበዛበት ዘመን … ” ሲሉ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በለሆሳስ ሲሰራጭ የነበረውን ወሬና ቅስቀሳ አጣጥለዋል።
ሰፊ ቅስቀሳና ህዝብ በነቂስ ለመውጣት እንዲዘጋጅ ጥሪ የቀረበበት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸው እና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት ዘጠኝ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል። ሹመቱም ወደፊት ይፋ እንደሚሆን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አስታውቀዋል።

ይህ የተገለጸው የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ በሰጡትበት ወቅት ነው። መግለጫውን ተከትሎ የሃሰት መረጃና ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ አካላት ይቅርታም ሆነ ማስተካከያ ዜና አልቀረቡም።
” የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል።” ሲሉ አቡነ ጴጥሮስ ማስታወቃቸውን ተከትሎ የሚጠብቃቸው ነቀፌታና ተቃውሞ እስካሁን ለአየር ባይበቃም እንደማይቀርላቸው አካሄዱን የሚያውቁ እየገለጹ ነው።
“ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ዛሬ ውሳኔ ተላልፏል።” ብለዋል።
የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን አሁን ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል እነሱ በሚያቀርቡት ጥናት ሹመት ይካሄዳል። የሹመቱ ቀን ወደፊት ይገለፃል። ዋናው ነገር ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመው የትኛው ነው ? የሚለውን የጉባኤው አባላት በሙሉ ተስማምቶ ፣ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሃሳብ፣ በመነጋገር ውሳኔ መተላለፉን ዋና ጸሃፊው አረጋግጠዋል።
ረቡዕ የማጠቃላይ መግለጫ በቅዱስ ፓትርያኩ እንደሚሰጥ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ተናግረዋል። “ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን፤ ምዕመናን በሙሉ ተጨንቃችኃል፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ነው ሌላ ጊዜ ወሬም ብዙ ይበዛል በዚህ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በጣም ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን ፤ በእውነት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ግሩም የሆነ የትምህርት ጊዜ፣ ግሩም የሆነ የውይይት ጊዜ ፣ ቤተክርስቲያን ለይተን የምትፈልገው ምንድነው የሚለውን የተወያየንበት ጊዜ ነው” ሲሉም ለቤተክርስቲያኒቷ ቤተሰቦችና ዜናው ላሳሰባቸው ሁሉ የእረፍት መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲስ አበባ ከብልጽግና ከፍተኛ አመራሮችና የመከላከያ አዛዦች ጋር አብሮ ሲሰራ የነበረው አቶ መሳይ መኮንን “ሁለት አስቸኳይ መረጃዎች” ሲል “ቤተክርስቲያን አካባቢ ጥሩ ነገር የለም” ሲል መነግስት የስብሰባውን ውጤት ለመቀልበስ የኦሮሚያ ብልጽግና የፖሊስና የደህንነት ሃይል ማሰማራቱን አመልክቶ ነበር።
በሌላ መረጃ ከሲኖዶስ ስብሰባ ጋር ያለው ግንኙነት ግልስ ባይደረገም የኦነግ ሰራዊት ከተሞችን እየተቆጣጠረ ግምቱን አስቀምጦ መረጃ አሰራጭቶ ነበር።
ዋሱ በቴሌግራም ገጹ ፎቶ አስደግፎ ” ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ መሆኑ ይታወቃል።ፎቶው ሲነሳ ቀንና ሰዓት ይመዘግባል። እኔ አሁን ስብሰባው በሚካሄድበት በር ላይ እያለፍኩ ነው።የፀጥታ ሀይሎች ሲርመሰመሱ ያየሁበት ነገር የለም።ከፍ ብሎ አንዲት የፌደራል ፖሊስ ፓትሮል ተመልክቻለሁ።ያለው ነገር ይሄ ነው።ሠላምን እንመኝ።መልካም ነገሮችን ያብዛልን ለማለት ነው” ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ እውነቱን ካስታወቁ በሁዋላ አንዳችም ማስተባበያ ይህ እስከታተመ ድረስ አልተሰማም።
ይህን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡ ” ውሸት የተለመደ ነው። ውሸታም ሚዲያን ሁለተኛ አላድምጥም የሚልም የለም። በሰበር መረጃ ሃሰት ሲረጭ የሚቀበሉ ሃሰቱ ሲገለጽ ለምን እንደተዋሸ የሚመረምሩ አለመኖራቸው፣ እንዲያውም በማህበራዊ ሚዲያው ሰፈር ውሸታሞችን የሚያምኑ መበራከታቸው አሳሳቢ ነው”
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria, and the ongoing tensions with Iran, its Foreign Minister Gideon Sa’ar found more time to visit Ethiopia. This visit underscores the importance of what the Israeli occupation minister discussed, and opens the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ የሚገነዘቡ ምሁራን የራስ ዱሜራን ጉዳይ ወደ አደባባይ ይዘውት ቢመጡ እንዴት ጥሩ ነበር ምክንያቱም መልካም ሀሳቦች ሲጠራቀሙ ሀገር ያጸናልና! በጅቡቲ ላይ ወሳኝ ጥያቄ ማንሳት የሚያስችሉ ታሪካዊ አጋጣሚዎች የነበሩት ደርግ እና በኤርትራ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ ነው።ከትግራይ ጊዜያዊ መንበራቸው በአመጽና በጠመንጃ ኃይል እንዲወገዱ የተደረጉት አቶ ጌታቸው ውስን ያሉዋቸውን ጄነራሎች ስም እየጠቀሱና በጥቅሉ ተጋባራቸው “የብረሃን ስራ በብርሃን ነው” እንደተባሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ” – የራሱን ሰርግ አቋርጦ ቀዶ ሕክምና በማድረግ ሕይወት የታደገዉ ዶክተር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በሌ ከተማ አስተዳደር የበሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት በ “X” ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን ተቸካይ ነው። የትህነግ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ