ምርጫ ቦርድ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በተደነገገው አዋጅ መሠረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈቅድ መሆኑንም ዛሬ ግንቦት 5/ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ህወሓት ለምርጫ ቦርድ የሕጋዊ ሰውነት ስረዛና የፓርቲው ንብረት እገዳ ይነሳልኝ ጥያቄ ያቀረበው ፕሪቶሪያ የተደረሰውን ግጭትን በዘላቂነት ለማስቆም የተደረሰውን ስምምነት በመጥቀስ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ነው።
ደብዳቤው ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ሕጋዊ ስረዛ አስመልክቶ ጥር 10/ 2013 ዓ.ም ያስተላለፈውን ውሳኔ ጠቅሷል።
ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን ተረጋግጧል በሚል የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት እንዲሰረዝ፣ የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንዳይችሉ፣ እንዲሁም የፓርቲው ንብረት ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፣ ቀሪው ገንዘብና ንብረትና ደግሞ ለሥነ ዜጋ መራጮች ትምህርት እንዲውል የሚደነግግ ነው።
በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት በሰላም በመቋጨቱና በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ስምምነትም በመጥቀስም ፓርቲው የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል የሚለው ድምዳሜ አሁን ላይ መለወጡን ታሳቢ በማድረግ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ያስተላለፋቸውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ስረዛና ሌሎች ብያኔዎች እንዲነሳ ሲል መጠየቁንም ምርጮ ቦርድ አስፍሯል።
ቦርዱ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ አስተላለፍኩት ባለው ውሳኔ ህወሓት በላከው ደብዳቤ እንደተገለጸው ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሠረት ያደረገው የአመጻ ተግባር አሁን የለም ብሏል።
ነገር ግን እንደገና የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/ 2011 ተደንግጎ እንደማይገኝ ጠቅሷል። በዚህም ምክነያት ቦርዱ በህወሓት የቀረበለትን የሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይን በሕግ የተደገፈ ሆኖ ባለማግኘቱ አንዳልተቀበለው ጠቅሷል።
ስለዚህ በአዋጁና በተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈቅድ መሆኑን መወሰኑን አመላክቷል።
የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደ አዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ ሆነው ባለመገኘታቸው እግዱ እንዳልተነሳ ጠቅሶ የቀረበውን ጥያቄ ቦርድ ውደቅ ማድረጉ ተጠቅሷል።
ጥር 10/2013 ዓ.ም. ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን ማስታወቁ ይታወሳል።
ቦርዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ህወሓት በአመጽ ተግባር ላይ መሰማራቱን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጡን በመግለጽ፣ ሕጋዊ ሂደቶችን በመከተል የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት በመሰረዝ ማንም በህወሓት ስም መንቀሳቀስ እንደማይችል ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል።
በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ግጭት የማቆም ዘላቂ ስምምነት ተከትሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ቡድንነት ተሰይሞ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፍረጃው መነሳቱ ይታወሳል።
በትግራይ ተከስቶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት የመቶ ሺዎችን ሕይወት ቀጥፏል እንዲሁም ሚሊዮኖችን ለሰቆቃ ዳርጓል።
በመቶ ሺዎች በተቀጠፉበት ጦርነት መደፈር፣ ወሲባዊ ጥቃቶች፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ረሃብ በጦር መሣሪያነት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሪፖርት ያሳያል ሲል ቢቢሲ የምርጫ ቦርድን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ ነው።ከትግራይ ጊዜያዊ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ደኤታ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ ሌተናል ጄነራል የሚመራው አዲሱ አስተዳደር ይህን መግለጫ ያወጣው በዶክተር ደብረጽዮን የሜመራው የትህነግ አንድ ክፋይ ከሻዕቢያ ጋር መርህ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት የትግራይን ሕዝብ ዝቅ የሚያደርግ ክብረ ነክ መመሪያ መተላለፉ በገሃድ ከኤርትራ የፕሮፓጋንዳ ሰዎች በተላለፈ ማግስት ነው። ይህ መመሪያ… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው
- ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱተከሳሾቹ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ቀርበው በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት እንደየተሳትፏቸው የቀረበባቸው ክስ ተነቦላቸዋል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ ክስ የመሰረተባቸው ግለሰቦች በአሜሪካና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፥… Read more: ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱ