የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በቅርብ ጊዜ የወረራት ፣ የተጣባት ቫይረስ ዘመድኩናዊነት ይባላል። ዘመድኩናዊነት እንደ ቀደመው ዘመን ፈሪሳዊነት 99.9% ጊዜውን የሚያጠፋው የእግዜሩን ቃል በማካፈል ፣ ቀን የጎደለባቸውን ደገፍ ማድረግ ላይ አይደለም። ዘመድኩናዊነት አሳዳጅነት ፣ ስድነት ፣ ተሳዳቢነት ነውርን ክብር አድርጎ አደባባይ የመውጣት ህመም ነው።
ዘመድኩናዊነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ እነ መምህር በጋሻው አጠፉ ለሚባሉት ይቅርታ ጠይቀው ቤተክርስትያኒቱን አማኙን ባገለገሉ ነበር። ዘመድኩናዊነት ባይገን ኑሮ ዛሬ መነኩሴው ፣ ዘማሪው ፣ ሰባኪው ውሎውን ቲክቶክ ፣ ፌስቡክና ዩቱይብ ላይ ባላደረገ ነበር። ዘመድኩናዊነት በጓዳ የሰማኸውን የጓደኛህን ህጸጽ በአደባባይ በሞንታርቦ ለህዝብ የማወጅ ነውረኝነት ነው።
አቡነ ጴጥሮስ ክርስትናን ሊኖሩት የሚሞክሩ ፣ የሚታትሩ ክህን ናቸው ስል አስባለሁ ። አቡነ ጴጥሮስ እና ካህናት ወዳጆቻቸው እነ አቡነ ሳዊሮስን ረግሞና አዋርዶ ከቤተስኪያን ከማራቅ ይልቅ ይቅርታን ፣ ክርስትያናዊ ወንድማማችነትን ለምዕመኑ ያስተማሩ ይመስለኛል። አቡነ ጴጥሮስ በትናንትናው ንግግራቸው የማህበራዊ ሚዲያን አጥፊነትን በገደምዳሜም ጠቆም አድርገዋል ። የዚህ ዘመን ምዕመን መንፈሱ ለዘመድኩናዊነት ቅርብ ነው ፣ ትናንት አባ ያላቸውን ካህናት ዛሬ በመንደር ቃል ለመዘርጠጥ ሰከንዶች አያመነታም። ብዙው አማኝ የእግዜሩን ቃል ከማዳመጥ ፣ በየሰፈሩ ቀን ለጎደለባቸው የሚላስ የሚቀመስ ከማካፈል የቤተስኪያን ጠላቶች የሚላቸውን ቢያሳድድ ለአምላኩ ትልቅ ውለታ የሚውል የሚመስለው ነው።
ክርስትና ሌሎችን መውደድ ፣ ደከም ያሉትን ( በመንፈስም በስጋም ) ማገዝ ነው። ክርስትና ውስጡ የአሳዳጅነትና ከሳሽነት መንፈስ ፍጹም የለበትም። አቡነ ጴጥሮስ ውስጥ ፍቅርና ትህትና የሞላበት ክርስትናን አያለሁ ።
መምሬ Samson Michailovich እንደጻፉት !
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ ነው።ከትግራይ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ” –… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies in Washington. Conflict, famine and a great-power competition are colliding… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ ሰባት ለአንድ፣ ቶትነሃም ቦዶን በድምሩ አራት ለአንድ አሸንፈው ነው ለፍሳሚ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል