በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ – አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።
ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ሩሲያ የአፍሪካ ልሂቃን ዲግሪ ለማግኘት ከሚሄዱባቸው አገሮች አንዷ እንደነበረች ያነሱት በውይይቱ የተሳተፉት ምሁር ቱንዴ አጂሌዬ÷አሁን ላይ ሩሲያ እና አፍሪካ የትምህርት ልውውጡን መቀጠል አለባቸው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ምሁሩ ገለጻ በግብርና፣ በኃይል እና ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies in Washington. Conflict, famine and a great-power competition are… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ ሰባት ለአንድ፣ ቶትነሃም ቦዶን በድምሩ አራት ለአንድ አሸንፈው ነው… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል