የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው።
እንደ ሌሎች የካንሰር ሕዋሳት ሁሉ የጡት ካንሰርም በጡት ዙሪያ ወደሚገኙ ሕዋሳት ውስጥ ገብቶ ሊያድግ እና ሊሰራጭ ይችላል፡፡
ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም በመጓዝ አዳዲስ ዕጢዎችን ሊፈጥር ይችላል።
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው።
የጡት ካንሰር ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ በብዛት ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።
የጡት ካንሰር ብዙውን ጊዜ ከ 50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
ሲጋራ እና አልኮል መጠቀም ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት ፣ የሆርሞን ወሊድ መከላከያ ወይም ሌላ የሆርሞን መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም እና የጨረር ሕክምና ለጡት ካንሰር መከሰት ምክንያቶች ናቸው::
በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጅን ከ30 ዓመት በኋላ መውለድ፣ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት ፣ ከ12 ዓመት ዕድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ 55 ዓመት ዕድሜ በኋላ የወር አበባ ዘግይቶ መቆም እንደ መንስዔ ሊወሰዱ ይችላሉ::
የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
በብዛት የሚስተዋሉ የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት መጠን ወይም ቅርጽ ላይ ለውጥ ማየት ፣ የአተር መጠን ያለው እብጠት፣ በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የመልክ ወይም የቆዳ ለውጥ፣ ከቆዳው በታች እብነ በረድ የመሰለ ጠንካራ ቦታ መኖር ናቸው፡፡
በተጨማሪም ከጡት ጫፍ ውስጥ በደም የተበከለ ወይም ንጹህ ፈሳሽ መኖር ፣የተሰራጨ ዕጢ ከሆነ ደግሞ የደረት ሕመም፣ የአጥንት ሕመም እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
ሕክምናውን በተመለከተ
የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ ፣ አልትራሳውንድ ፣ እና ፒኢቲ(PET) የተሰኙት ምርመራዎች የሚታዘዙ ሲሆን አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል ::
ሕክምናን በተመለከተም ቀዶ ጥገና ፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በርካታ የጡት ካንሰር ሕክምና አማራጮች አሉት።
ሕክምናው የሚወሰነው ዕጢው ያለበት ቦታ እና መጠን፣ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶች እና ካንሰሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መስፋፋቱን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ይደረጋል።
ሕክምናው ቀደም ብሎ ከተሰጠ የመዳን ዕድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያለበት ሰው በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ዶክተሮች ይመክራሉ፡፡
ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ + fana
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ“በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው” አስገኘው አሽኮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር :- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በአንድ ታዋቂ ሙዚቀኛ (አስገኘው አሽኮ) ሴቶችን… Read more: ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ
- መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?ዶክተር ጽዮን ተስፋ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም ናቸው። በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ «አለርት ጉርሻ» በሚል በኦን ላይን ፕሮግራማቸው «ትኩረት ያልተሰጣቸው» በሚባሉ የበሽታ… Read more: መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?
- ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗልየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ ሀገር ጥለው የሚሰደዱ ሴቶች መኖራቸውም… Read more: ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል
- የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!ስርዓተ ቀብራቸው በዝነኛው የቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን አልተፈፀመም። ስለማይገባቸው ሳይሆን እሳቸው ስላልፈለጉ ነው። በኑዛዜያቸው መሠረት ስርዓተ ቀብራቸው ከቫቲካን ወጣ ብላ በምትገኘው ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን [… Read more: የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!