የአኙዋና ኑኤር ጎሳዎች ጊዜ እየጠበቀ የሚያገረሽ ግጭት ማንሳት ለማዳቸው ነው። የኑኤር አብላጫ ቁጥር ያለውና ከሱዳን እርስ በርስ ተፋላሚዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አመረሮችም ያሉበት በመሆኑ ብዙ ጊዜ የግጭቱ መነሻዎች እነሱ ናቸው። ከጋምቤላ የተሰማው ለበርካቶች ሞትና ንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው አዲሱ ግጭት ተዋንያኖቹ ለህግ እንደሚቀርቡ፣ መከላከያ ጸቡን አብርዶ የማደን ስራ እየሰራ መሆኑንን ነው።
የኮሙኒኬሽን ሃላፊውን ጠቅሶ ጀርመን ድምጽ እንዳለው ቀስቃሾቹ ባለስልጣናት እነማን እንደሆኑ እየተጣራ ነው። የደረሰውም ጉዳይ ሰፊ ሲሆን አሁን ላይ መከላከያ በሁሉም ወረዳዎች ተሰማርቶ እያረጋጋ ነው። ግጭቱ ቆሞ ስጋት ላይ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ሰላም እስከሚሆኑ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣል አስፈልጓል። ዲ ደብሊው ዘገባ ያንብቡ
የሰዓት እላፊ ገደቡ የተቀመጠው ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነ የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በሰው እና ንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን በተከተሰው የጸጥታ ችግር በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡ የጸጥታ ችግሩን ለመቆጣጠር እንዲያመች የሰዓት ዕላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለዶቼቬለ ተናግረዋል፡፡ ከትናንት ማታ ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የሰዓት እላፊ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ከተፈቀደላቸው የጸጥታ ሐይሎች ውጪ ሰው እና ተሽከርካሪ መንቀሰቃስ እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ የሰዓት እላፊ ገደቡ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ነው ያሉት ኃላፊው ሰሞኑን “ጨለማን ተገን አደርገው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች” ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ በተከሰተው ግጭት በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸው የጉዳት መጠኑ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡ ያነጋርናቸው የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ከባለፈው ሰኞ አንስቶ የጸጥታ ችግር ተባበስቦ መቆየቱ እናን ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የጋምቤላ ክልል መንግስት ካቢኔ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ አስቸካይ ጉባኤ ካደረገ በኃላ የሰዓት እላፊ ገደቡ መጣሉን አመልክቷል፡፡ የሰዓት እላፊ ገደቡ የተቀመጠው ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽፈት ቤት አመልክተዋል፡፡ የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ በሰጡን ማብራሪያ ሰሙኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በሰው እና ንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፈደራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት በየወረዳው ተሰማርተው እንደሚገኙም ለዲዳብሊው አብራርተዋል፡፡ ለዘመናት አብሮ የኖረ ማህበረሰብን ወደ ግጭት እንዲያመራ ያደረጉ እና በድርጊቱ የተሳተፉ የክልሉ አመራሮች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ አመራሮች ጉዳይ ተጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አመልክተዋል፡፡ጋምቤላ ውስጥ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት
የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ አቶ ማሙሸት ደረሰ ከባለፈው ሰኞ አንስቶ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ግጭት መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ በገበያ ስፍራ በዝርፍያ የተሰማሩ ግለሰቦችም እንደነበሩ አክለዋል፡፡ በገጠርማ ስፍራዎች ደግሞ ቤቶች መቃጠላቸውን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ነዋሪዎች ላይ የሞት እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችም
በግጭት ውስጥ መሳተፋቸውን የገለጹት ነዋሪው ግጭቱ የብሔር መልክ ያለው እና በአካባቢው አብሮ በሚኖሩ የአኙዋና ኑኤር ብሔረሰብ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ በክልሉ እንደ ላረ እና ኢንታግ አካባቢ አሁንም ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ጠቀመዋል፡፡ከማክሰኞ አንስቶ የመስሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሙሉ በሙሉ ከትጥቅ ትግል መውጣቱን ዐስታወቀ
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ትናንት ይፋ ባደረገው መረጃ የመንግስት ሰራተኞች እና ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራቸውን እንዲጀምሩ ውሳኔ ማሳለፉን ጠቅሷል፡፡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ማንኛውንም ድምጽ አልባ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይችል የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡ ይህን ተላልፎ ይዞ የተገኘ ግለሰብ እርምጃ እንደሚወሰድበትም ተጠቁሟል፡፡ በግጭቱ ለደረሰው የሰው ህይወት ህልፈትና ንብረት ውድመት የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥቅል ሀዘን ገልጸዋል፡፡
ጀርመን ድምጽ እንደዘገበው
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበትየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን በስራ ፈጣሪ ቅድሚያ የሚነሱትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን… Read more: በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበት
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው
- ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱተከሳሾቹ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ… Read more: ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱ