የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አዲስ አበባ ሲገቡ ሚኒስትሮቻቸውን በሙሉ በመያዝ ነው። ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ታንቃ የነበረችበትን የዕዳ ሸምቀቆና የትህነግ ወረራ ለመመክተ የመሳሪያ ድጋፍ ያደረግችው አገር መሪዎች ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የተደረገው አቀባበልም ያንን የሚመጥን እንደሆነ ታይቷል።
ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ካቢኒያቸው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በጋለና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ አቀባበል የተደረገላቸው የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች የንጉሳዊያን ቤተሰቦች ለኢትዮያ እጅግ ውለታ መስራታቸው ይህንኑ አቀባበል ተከትሎ ተነስቷል።
ትህነግ በህዝባዊ አመጽ ተገዶ ስልጣኑን ሲለቅ አገሪቱ በዕዳ ሸምቀቆ ታንቃ ነበር። ዕዳ መክፈል ባለመቻሏ ንብረቷን ልታጣ፣ ክብሯን ልክትገፈፍ ጫፍ ደርሳ ለነበረችው ኢትዮጵያ የሶስት ቢሊዮን ዶላር ስጦታ በመስጠት ውለታ የሰራች ብቸኛ አገር ኢመሬትስ በቀና አሳቢ ዜጎች ዘንዳ ክብር አላት።
መከላከያ በክህደት ታርዶ፣ መሳሪያው ሁሉ ተዘርፎ፣ ሎጂስቲኩ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተወስዶ ባዶ ቀርቶ ወረራ በተፈጸመበት ወቅይ ኢመሬትስ ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትጸናና ወረራውን እንድትመክት ድሮን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ እገዛ ማድረጓን የሚረዱ አሁንም ለዚህች አገር ውለታ እውቅና ይሰጣሉ።
በርካታ በገሃድ የማይጻፉና የማይነገሩ ውለታዎችን የፈጸመችው ይህቺ ቱጃር አገር፣ ኢትዮጵያ በተጠና ዘመቻ አገራት፣ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ የታላላቆቹ አገራት መሪዎች ጫና አሳድረው ሊያፈርሷት በተረባረቡ ወቅት የተባበሩት ኢመሬትስ ልክ እንደ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም በተለያዩ ጊዜ ወደፊት በሚገልጻቸው አግባቦች ሁሉ ድጋፍ አድርገዋል።
ለዚህም ይመስላል ኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፏን ዘርግታ ” እንኳን ደህና” መጣችሁ ስትል በኢትዮጵያዊ ክብር እንግዶቿን የተቀበለችው። ከቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ጀምሮ በጎዳና ላይ በሚማርክ አጀብ እንግዶቿን አጅባ ወደ ታላቁ ቤተመንግስት በማስገባት በዚህችው አገር እርዳታ የተዋበውን ቅጥር አስጎብኝታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው” ሲሉ ቀድመው እንደገለጹት ከጉብኝቱና መስተንግዶው ጎን ለጎን አስራ ሰባት ስምምነቶች መደረጋቸው ጉዳዩ ከአቀባበሉ ድምቀት በዘለለ ሌላ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አሳይቷል።
“ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለን” የገለጹት አብይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ያላቸው እጅግ የጠነከረ ወዳጅነትን ለማሳየት ” ወንድሜ” ሲሉ ደጋግመው ይጠራቸዋል። ይህ አጠራራቸውና ከፕሬዚዳንቱ ጋር ያላቸው የጠበቀ ግንኙነት ያልተመቻቸው ዘለፋ ሲሰነዝሩና ጉብኝቱን ሲያጣጥሉ ታይቷል።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን መላ ካቢኒያቸውን ይዘው መምጣታቸውና ከአስራ ሰባት በላይ ስምምነቶች መከናወናቸው ግርምት የፈጠረባቸው ደግሞ አድናቆትን ችረዋል።
በኢንደስትሪ፣ ግብርና፣ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ፣ ንግድ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ማህበራዊ ዘርፍ፣ የነጻ ንግድ፣ ወደብና ሎጂስቲክ፣ የንግድ ዘርፍ ተቁማት ስምምነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ አገራቱ ሽብርተኛነትን በጋር ለመዋጋትና በደህንነት ጉዳይ አብረው ለመስራት መፈራረማቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ላቀና ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገሩን የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።
ከፍተኛ ሃብት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ኢመሬትስ ባንኮች መዛወራቸው፣ የገንዘብ አጠባ ስራ የሚሰራው ባብዛኛው እዛ በሚገኙ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች መሆኑንን ያስታወሱ ግልጽ ስምምነት ስለመደረጉ ባይናገሩም አገሪቱ በቀርቡ ህገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ላይ እየወሰደች ካለው እርምጃ ጋር ተያያዞ ዜና ሊኖር እንደሚችል በርካቶች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ስለጫካው ፕሮጀክት ሲጠየቁና የገቡበትን ቆሻሻ የሞላው ቤተ መንግስት እንዴት እንዳደሱት ሲያብራሩ “ወንድሜ” የሚሏቸው ሼኽ መሐመድ ቢን ዛይድ ባበረከቱላቸው ድጋፍ አንድም የአገር ውስጥ በጀት ሳይነኩ እየሰሩ መሆናቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ