የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም መታወቂያን አስመስሎ በማዘጋጀት ሰዎችን እያስፈራራ ገንዘብ ሲቀበል ነበር በተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።
የክስ መመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ የፈቀደው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲሆን÷ተጠርጣሪው ነስሩ ሳሌ ጀማል ይባላል።
ግለሰቡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰራተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ደህንነት ነኝ በማለት ግለሰቦችን በወንጀል እንደሚፈለጉ በመግለፅና መታወቂያውን በማሳየት ከግለሰቦች እስከ 200 ሺህ ብር ጀምሮ ሲቀበል እንደነበር ተመላክቷል፡፡
በዚህም ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሲከናወንበት መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ በዛሬው ቀጠሮ የምርመራ ስራ ማጠናቀቁንና መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን ለተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አስታውቋል።
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክተር ዐቃቤ ሕግ ችሎት ቀርቦ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ መረከቡን ገልጿል። መዝገቡን ተመልክቶም ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
ተጠርጣሪው በበኩሉ ÷ ከዚህ በፊት ለፖሊስ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀዱን ጠቅሶ በድጋሚ ለክስ መመስረቻ ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድ አይገባም በማለት የዋስትና መብቱ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ ለመመስረት ጊዜ እንደሚያስፈልገው በማመን የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል። ውጤቱን ለመጠባበቅም ለመስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ ፋና
- የግል ዳታ ጥበቃ በኢትዮጵያ ህግመግቢያ በዚህ ባለንበት ዘመን በፍጥነት እያደገ የሚገኘው የዲጂታል ግንኙነት ቴክኖሎጂ ዘርፈ ብዙ እድሎችና ጠቀሜታዎችን እያስገኘ የሚገኝ የፈጠራ እድገት መሆኑ ይታወቃል።… Read more: የግል ዳታ ጥበቃ በኢትዮጵያ ህግ
- የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የችሎት ሂደትን እንዳይታደሙ በፍርድ ቤት ታገዱየፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በፍቅረኛው ወጣት ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኘው የአርቲስት… Read more: የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የችሎት ሂደትን እንዳይታደሙ በፍርድ ቤት ታገዱ
- አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡከግለሰብ ከግለሰብ አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ… Read more: አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ<br>
- በቅናት የ4 ልጆቿን አባት በተኛበት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው መምህርት ተፈረደባትበምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ከተማ ነዋሪ የሆኑት በተመሳሳይ ሙያ ላይ የሚገኙት መምሕር ጉተማ ኡካ እና መምሕርት ጠይባ ቱሪ ለሀያ… Read more: በቅናት የ4 ልጆቿን አባት በተኛበት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው መምህርት ተፈረደባት
- ፌስቡክ ትግራይ ተጀምሮ አማራና አፋርን ጭምር ባወደመው ጦርነት ሚና ነበረው በሚል ክሱ ኬንያ እንዲታይ ተበየነየግዙፉ ማሕበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ወላጅ ኩባንያ ሜታ በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተዛመተው ጦርነት ተጫውቷል በተባለው ሚና ኬንያ… Read more: ፌስቡክ ትግራይ ተጀምሮ አማራና አፋርን ጭምር ባወደመው ጦርነት ሚና ነበረው በሚል ክሱ ኬንያ እንዲታይ ተበየነ