ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ÷የከተማ አስተዳደሩ እና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም ከክልሉ መንግስት እና ሕዝብ ጎን በመቆም ይሄንን ሀገር አፍራሽ እና የዘራፊ ስብስብ ኢሰብአዊ ድርጊቱን በፅኑ ይቃወማል! ብሏል፡፡
ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም እንደ ወትሮው ሁሉ ደጀንነቱን ያረጋግጣል! የከተማውን ሰላም በማረጋገጥ የህገ-ወጦችን ተግባር በህግ ሥርአት ያስከብራል! ሲልም ገልጿል።
ክልል ከጦርነት ጉዳት ሳያገግም በስሙ ምለው በሚገዘቱ የጥፋት ኃይሎች ይህን አይነት አስከፊ ችግር ስላጋጠመው እያዘነ ፤ እንደ አስፈላጊነቱ የከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ረገድ ከክልሉ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም ይህንን አጥፊ ቡድን ኢሰብአዊ ድርጊቶቹን እንደሚቃወምም አስታውቋል።
የዚህ የጥፋት ኃይል ከአማራ ክልል ቀጥሎ አዲስ አበባን የሽብር እና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ በተለያየ መንገድ እየሞከረ እንደሚገኝም ተደርሶበታል ነው ያለው በመግለጫው።
እነዚህ አጥፊ ቡድኖች እራሳቸው በጠመቁት የፀብ አጀንዳ አዲስ አበባን እና የአዲስ አበባን ህዝብ የአላማቸው ማስፈፀሚያ ለማድረግ ከተማዋን ደግሞ የግጭት እና ብጥብጥ አውድ ለማድረግ በተግባር እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡
ሆኖም ሰላም ወዳዱ እና ሚዛናዊው የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ግዜውን፣ እውቀቱን፣ ገንዘቡን እና ጉልበቱን ለሰላም እና ልማት የሚያውል ቢሆንም፣ በህልውናው ላይ በሰላሙ ላይ እና በልማቱ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም አደጋ እና ስጋት እንደ ወትሮው ሁሉ በግንባር ቀደምነት ይፋለማል። ልማቱንም ያስቀጥላል !! ብሏል የከተማ አስተዳደሩ በመግለጫው፡፡
ይህ የጥፋት ቡድን ለዚህ እኩይ ዓላማው ማስፈፀሚያነት የሚያገለግሉና ምንም አይነት ግጭት ከሌለበት አካባቢ የግጭት ሽሽት እና ተፈናቃይ በማስመሰል በርካታ ፀጉረ-ልውጦችን አስርገው በማስገባት በከተማው ውስጥ የጥላቻ፣ የመከፋፈል እና የአመፅ አላማቸውን ለማራመድ እና የጠመቁትን ሴራ ወደ ህዝቡ ለመርጨት ሲሞክሩ በእኩይ ተግባራቸው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውንም ገልጿል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ በቁርጠኝነት ህገ ወጦችን በህግ ስርዓት ያስይዛል!ሲልም በመግለጫው አስፍሯል፡፡
በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን መሰል እንቅስቃሴ በንቃት እየተከታተለ ለህዝቡ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን ህዝቡን ያሳተፈ እርምጃዎችንም እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም እንደ አገር የገጠመን ይህንን ችግር የጋራ ርብርብ የሚሻ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የከተማችን ነዋሪዎች ከጀግናዉ የመከላከያ ስራዊታችን፤ ከአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ ጎን በመቆም እንደ ወትሮው ሁሉ አስፈላጊውን ቁርጠኛ ድጋፍ ያደርጋል!! ብሏል፡፡
ሰላም ወዳድነቱን በሥራ እና ደጀንነቱን በቁርጠኛ ትግል ያረጋግጣል! ሲል ገልጿል በመግለጫው፡፡
…………………………………………………………………..
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ ሌተናል… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበትየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን በስራ ፈጣሪ ቅድሚያ የሚነሱትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና “ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ” የተባለ ኩባንያን ጨምሮ… Read more: በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበት
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት የትግራይን… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው