አማራና አፋር ክልል በወረራ አመድ ሲሆን ትንፍሽ ያላሉት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት መንገዶች መዘጋታቸው እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ የሰብዓዊ እርዳታን ማድረስ እና ግንኙነትን ለማስቀጠል ከባድ እንደሚያደርገው አመለከቱ። ሃዘናቸውን መግለጻቸው ደግ ቢሆንም በርካቶች ” የካድሬ ስብዕና ያስደንቃል” ሲሉ፣ ቀደም ሲሉ በነበራቸው የታጋይነት አቋም ሲዘልፏቸው የነበሩ ዜናቸውን እየተቀባበሉት ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገጻቸው ይህን ያሉት በአማራ ክልል በታጣቂዎች እና በመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች መካከል የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ግጭቶች በሰዎች ጤና ላይ በፍጥነት አሉታዊ ተጽእኖ ከማሳደራቸው በተጨማሪ በጤና ስርዓቱ ላይ ረዥም ጊዜ የሚዘልቅ ጉዳት ያስከትላሉ ብለዋል። ስጋታቸው ትክክል ቢሆንም ቴዎድሮስ ትህነግ አማራና አፋርን ወሮ ሲያወድም፣ ክሊኒክና ሆስፒታል ሲዘርፍና ሲያቃጥል ይህን አላሉም።
ዶ/ር ቴድሮስ ሰዎች የጤና ድጋፍ እንዳይቋረጥባቸው እና የዓለም ጤና ድርጅት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ በክልሉ የጤና ስርዓቱ ጥበቃ እንዲደረግለት ጠይቀዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “ከምንም በላይ ለሰላም ጥሪ እናቀርባለን” ማለታቸውን ቢቢሲ ነው የዘገበው። ትህነግ ተሸንፎ የሰላም ስምምነት ካደረግ በሁዋላ አደብ ገዝተው የተቀመጡት ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁን ላይ የሰጡት መግለጫ ሳይሆን ቀደም ሲል ” እኔ ወያኔ ነ” እስከማለት ደርሰው ሲያስተላለፉ የነበሩት መረጃና አቋም ምን ግዜም ቢሆን ተዓማኝ እንደማያደርጋቸው ብዙዎች መግለጫውን ተከትሎ ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት በአማራ ክልል ጨምሮ በጤና ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎ እንደነበር የገለጸው ቢቢሲ ሃላፊ በወቅቱ በትህነግ አባልነታቸው ታውረው የአማራና አፋር ህዝብን ስቃይ በዝምታ ያልፉት እንደነበር አልተቆመም።
በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን በሚያስተናግደው ክልል የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳ ቁስ ግብዓት እጥረት ከሰላም እጦት ጋር ተደማምሮ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንቅስቃሴን ገድበው ቆይተዋል።
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት።… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ።… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበትየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን በስራ ፈጣሪ ቅድሚያ የሚነሱትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና “ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ” የተባለ… Read more: በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበት