ጳግሜን 5 የትውልድ ቀን “ኢትዮጵያ የትውልድ ምድር” በሚል መሪ ሃሳብ በፌዴራል ደረጃ በውይይት እና ሌሎች ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ “በትውልዶች መካከል ቅብብል ወይስ ቅራኔ” በሚል ርእስ ለውይይት መነሻ የሚኾን ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘመናት በጸናው ታሪኳ እና ዘርፈ ብዙ አውድን ባስተናገደው የሀገረ መንግሥቷ ምስረታ አያሌ የሚባሉ ውጣ ውረዶችን አስተናግዳለች፡፡ ሀገር እንደውርስ በትናንት፣ በዛሬ እና በነገ መካከል ስትጸና፤ እዳ እና ምንዳ ደግሞ ትውልድ በየጊዜው የሚረካከበው እና የሚያወራርደው ነገር ኾኗል ይላሉ፡፡
ትውልድ የሚለው ስያሜ ተፈጥሯዊ ከኾነው ብያኔ በዘለለ የማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ባሕላዊ ክስተት መገለጫም ኾኖ ያገለግላል ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ትምህርት ክፍል ተመራማሪ፣ መምህር እና የጥናታዊ ጽሑፉ አቅራቢ ዮናስ አሸኔ (ዶ.ር) ናቸው፡፡
በጥናታዊ ጽሑፋቸው ነገረ-ትውልድ ፣ የትውልድ ክፍፍል ፣ ፋና ወጊ ትውልድ እና በትውልድ መካከል ቅብብል ወይስ ቅራኔ የሚሉ ነጥቦችን ያነሱት ዶክተር ዮናስ በትውልዶች መካከል የተለያየ እና የተሳሰረ ቅብብሎሽ እና ቅራኔ ሊኖር እንደሚችል ማሳያዎችን ጠቅሰው አንስተዋል፡፡
የፖለቲካል ሳይንስ ምሑሩ ትውልድ ከተፈጥሯዊ ብያኔው በዘለለ ለክስተት የሚሰጥ መለያ እና ትስስር ተደርጎ እንደሚወሰድም አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ “የ1960ዎቹ” ትውልድ በተደጋጋሚ የሚጠራ የአንድ ትውልድ መለያ ነው የሚሉት ዶክተር ዮናስ ይኽም ከማኅበራዊ ሱታፌ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም እና ከአቢዮት ጋር የተያያዘ እንደነበር አንስተዋል፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ትውልድ ያሳያቸው ባህሪያት እና የተጋፈጣቸው ክስተቶች ነበሩ፡፡ ያ ትውልድ እስከ አሁኑ ትውልድ ድረስ የዚያ ዘመን መንፈስ እና ጽንሰ ሃሳብ መገለጫ ኾኖ ይጠራል ነው ያሉት፡፡
ትውልድ በባህሪው ተከታታይ፣ ቀጣይነት ያለው እና የተንሰላሰለ በመኾኑ የተለያዩ ተከታታይ ትውልዶች ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ ንቃተ ህሊና ይጋራሉ የሚሉት ጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢው ከ1960ዎቹ ትውልድ ጀምሮ የተስተዋለውን ብሔርተኝነት በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ይህም በጊዜ፣ በታሪክ እና በባሕል መካከል ያለውን ግንኙነት እና ትስስር የሚያመላክት እንደኾነ ተነስቷል፡፡
እያንዳንዱ ትውልድ የሚጓዘው በአንድ መርከብ ውስጥ ቢኾንም የራሱ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገ አለው ያሉት ዶክተር ዮናስ “ዘመን ትውልድን ይገነባል፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል” ነው ያሉት፡፡ “በትውልዶች መካከል ቅብብል ወይስ ቅራኔ” የሚለው ጥያቄም እያንዳንዱ ትውልድ በሚገነባው የራሱ ዘመን ውስጥ የሚቀበለውን ምንዳ እና የሚከፍለውን እዳ ለመጠየቅ ነው ብለዋል፡፡
በትናንቱ እና በአሁኑ ትውልድ መካከል ትዝታ፣ ትውስታ፣ ተረኮች፣ ታሪኮች እና የባሕል መገለጫዎች በፖለቲካዊ ክስተቶች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ውርሶች ናቸው፡፡ የትኛውም ትናንት ለአሁኑ ትውልድ ህልም ግንባታ ይጠቅማል እና ነገን እንዴት ይገነባል የሚሉት ጥያቄዎች መጻዒውን እንደሚወስኑ በጥናታዊ ጽሑፉ ቀርቧል፡፡ አሁናዊውን የኢትዮጵያ ነባራዊ ኹኔታ በማስመልከትም ትውልዱ ሀገረ-መንግሥት ፋና ወጊ፣ አብዮታዊ ፋና ወጊ እና ድህረ አብዮት ወራሽ ትውልድ ተብሎ ተንሰላስሏል፡፡
የጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢው እንደመውጫም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትውልድ መካከል ነገረ-ጠመንጃን፣ አሸናፊና ተሸናፊ እንዲሁም ውርስና መነቀል አሁንም ድረስ ፈታኝ ክስተቶች መኾናቸውን አንስተው የጠመንጃን ጉዳይ ቋጭቶ የሲቪል ፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው (አሚኮ)
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ