ህዩዋ..ህዩዋ
ህንግጫ-የኮንታ_ብሔር_ዘመን_መለወጫ!!
የኮንታ ብሔር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለየ መልኩ የሚገለጽባቸው በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ቅርሶች ባለቤት ነው።
ብሔሩ ካሉት በርካታ የማይዳሰሱ ሀብቶች መካከል አንዱ የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል-ህንግጫ አንዱ ነው፡፡
ህንግጫ በብሄሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫም ነው።
በኮንታ ብሔር ዘንድ ህንግጫ የአሮጌው ዓመት ማብቅያ እና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም መሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡
የሚከበረው የዘመን መለወጫ ‹‹ህንግጫ›› በአል ዘመን ተሸጋሪና ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች በአብሮነት የሚያከበሩበት በአል ነው።
‹‹ህንግጫ›› ያማረ፣ ያጌጠ፣ የለመለመ ማለት ሲሆን አደይ አበቦች ፈክተው የሚታዩበት በአል ከመሆኑም ባለፈ በብሄረሰቡ ዘንድ በታላቅ ጉጉት ተጠብቆ በየአመቱ የሚከበር ልዩ በዓል ነው።
በዓሉ ከጳጉሜ 5/6 እስከ መስከረም 30 ድረስ የመስቀል በዓልን አካቶ የሚከበር ሲሆን ህብረተሰቡ ከቤት ውስጥ ጀምሮ ደጃፍና አከባቢውን የማጽዳት ዘመቻ በማድረግ በማጽዳትና በማስዋብ አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ ለመቀበል የሚሰናዱበትና ለበአሉ ከ12 አይነት በላይ ባህላዊ ምግቦች የሚዘጋጅበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ እጅግ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው።
የዘመን መለወጫ በአል ማብሰሪያ እሳት የሚወጣው ከጳጉሜ5/6 ምሽት ሲሆን ሲነድ የቀረው የማገዶ ጫፍ ከእሳት ዳር ተመዞ ወደ ዉጪ በመጣል ነዉ፡፡
መጠሪያውም ‹‹ ፂፋ ››ተብሎ ይጠራል።
የቤቱ አባወራው በያዘው ‹ፂፋ› ለዘመን መለወጫ/ለህንግጫ/በዓል ያደረሰውን ፈጣሪ እያመሰገነ እቤት ውስጥ ሰላም፤ ደስታና ጥጋብ እንዲሆን እየተመኘ ከቤት ደግሞ ክፉ መንፈስ እንዲወጣ እቤት ውስጥ ባሉት እቃዎች ላይ ‹በጺፋው› እየነካካ ወደ ውጪ ይዞት ይወጣና ይጥለዋል፡፡
በህንግጫ በዓል ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚበላበት፥ ድሃውም ሀብታሙም እኩል የሚያከብሩት የአብሮነት ተምሳሌት ክብረ-በዓል ነው።
ህንግጫ በአል ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ ዛሬ ላለንበት ጊዜ የደረሰ በመሆኑ ሁሉም የብሄሩ ተወላጆች የታሪክ መዛነፍ ሳይኖር ባህሉን ጠንቅቆ በማወቅና ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነታችንን ሊንወጣ ይገባል፡፡
“ህዩዋ ህዩዋ” ህንግጫው ብለናል።
አቤ ነኝ ከኮንታ ከሃበሻ የተወሰደ
- ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ“በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው” አስገኘው አሽኮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር :- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በአንድ… Read more: ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ
- የቶማስ ሳንካራ ባለቤት ደብዳቤ ለካፒቴን ትራኦሬወገግ ብሎ የጠፋው መብራት፣ በውጥኑ የከሰመው የአፍሪካ ኮከብ፣ ተስፈኛ፣ ባለ ራዕይ፤ ብሎም አፍሪካዊው ቼ ጉቬራ እየተባለ የሚወደሰው የቡርኪናፋሶ አብዮታዊ መሪ… Read more: የቶማስ ሳንካራ ባለቤት ደብዳቤ ለካፒቴን ትራኦሬ
- መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?ዶክተር ጽዮን ተስፋ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም ናቸው። በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ «አለርት ጉርሻ» በሚል በኦን ላይን… Read more: መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?
- ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗልየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ… Read more: ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል
- ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 ሀገራት የሩሲያ-ቻይና የጨረቃ ምርምር ጣቢያ ፕሮጀክትን ተቀላቀሉኢትዮጵያን ጨምሮ 13 ሀገራት ሩሲያ እና ቻይና ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ የጨረቃ ምርምር ጣቢያ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት መቀላቀላቸውን፤ የብሪክስ ሀገራት (BRICS)… Read more: ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 ሀገራት የሩሲያ-ቻይና የጨረቃ ምርምር ጣቢያ ፕሮጀክትን ተቀላቀሉ