በመጪው አዲስ ዓመት ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ አካሂዷል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩ አዲሱን 2016 ዓመተ ምህረት በይቅርታና በእርቅ መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው የጳጉሜን ቀናትን የጸሎትና ንስሐ መርሐ ግብር በማውጣት ቤተ እምነቶች ለሀገር ሰላምና አንድነት እንዲጸልዩ ማውጁ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የጸሎት መርሐ ግብሩ ማጠቃለያ የተካሄደ ሲሆን፤ በስነ-ስርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የጸሎት መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ኢትዮጵያ ዘመናትን ተሻግራ በጽናት የቆየችው በሕዝቧቿ መካከል ባለው ጠንካራ አንድነትና አብሮነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንዳንድ አካላት ይህን የሕዝቦች ትስስር ለመሸርሸር የሃሰት ትርክቶች እንደሚያሰራጩም ጠቅሰዋል፡፡ በመሆኑም በመጪው አዲስ ዓመት ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አገር የሚገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ የኃይማኖት ተቋማት በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በማፍራት ረገድ የጀመሩትን ሰራ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት መፍታት አንደሚገባም እንዲሁ፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም የእርቅና አብሮነት እንዲሆን የኃይማኖት አባቶች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ ሌተናል ጄነራል የሚመራው አዲሱ አስተዳደር ይህን… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት የትግራይን ሕዝብ ዝቅ የሚያደርግ ክብረ ነክ… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው
- “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበርበቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በስምምነቱ የቃል ኪዳን ሰነድ መሠረት አካታች ሊሆን እንደሚገባ የኢሮብ ማህበረሰብ ሲቪክ ማህበር ዋና ዳይሬክተር እና ፖለቲከኛ አቶ ስዩም… Read more: “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበር