ስማቸውን ካሰራጩት ደብዳቤ ግርጌ የዘረዘሩ ሰላሳ አምስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመጪው አዲስ ዓመት የ”ሰላም ጥሪ ” ሲሉ ባሰራጩት ጽሁፍ መንግስት ሁሉን አቀፍ መድረክ እንዲያመቻች ጠየቁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን ሲያሰባስብ የቆየውን ግብአት አደራጅቶ በመጪ አዲስ ዓመት ሁሉ አቀፍ የዕርቅ ማድረክ እንዲያዘጋጅ ማስታወቁን ተከትሎ የቀረበው ጥሪ ነው።
በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እንዲታዩ ዕቅድ ተይዞባቸው ከአራት ወረዳዎች፣ እንዲሁም በውልቃይት ጠገዴ ባለው የባልቤትነት ጥያቄ የተነሳ ከሃሜት ለመዳን ካለመከናወኑ በቀር በመላው አገሪቱ ግብዓት በመስብሰብ የትነተና ስራ ብቻ እንደቀረ ባለፈው ሳምት ኮሚቴው ማስታወቁ ይታወሳል። እርቅን ከፍትህ ጋር አስተሳስሮ አገሪቱን በየጊዜው ለውዝግብና እልቂት የሚዳርገውን ትርክት ለመቋጨት የተቋቋመው ኮሚሽን የተጋብር ስራውን በአዲሱ ዓመት ማግስት እንደሚያስጀምር የሚታወስ ነው።
ተጠያቂነትን ለማስፈን ፍትህ ሚኒስቴር
ኮሚቴው ” ለዘላቂ ሰላምና ለአገረ መንግስት ግንባታ የራሳቸዉ መሰረታዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸዉና የሽግግር ፍትህ ዋነኛዉ ትኩረት ተፈፀሙ የሚባሉ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ መሆኑንና በእነዚህ ሂደቶች ክስ የሚኖር መሆኑን በመግለፅ በአገራዊ ምክክር ላይ ግን በአብዛኛዉ ክስ የሌለ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል ሲሉ ከተቋማዊ አደረጃጀት አነፃርም የሽግግር ፍትህ በሁለት አይነት እንደሚደራጀና እነዚህም እዉነት ኮሚሽንና ፍርድ ቤት ላይ የሚተገበሩ ሲሆን አገራዊ ምክክር በአገራዊ ምክክር ኮሚቴ መሰል ቡድኖች እንደሚደራጅና በጥቅሉ አገራዊ ምክክር በሽግግር ፍትህ አማራጮች እንደ አንድ አማራጭ መካተቱንም አያይዘዉ አዉስተዋል” ሲል በጋዜጣ መግለጫው ወቅት መናገሩን ፍትህ ሚኒስቴር በገጹ አመልክቷል።
እነዚሁ ድርጅቶች ላቀረቡት ጥሪ የመንግስት ምላሽ ለጊዜው አልታወቀም። በኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም እንዲሰፍን መናፈቅ የእለት ተዕለት ስራው ሆኗል። የዚያኑ መጠን ሚዲያዎችና ማህበራዊ አውዶች ምንጩ ከማይታወቅ መረጃ በተጨማሪ በተቀነባበረና በተናበበ የፈጥራ ዜና የአገሪቱን ሰላም በስፋት እያወኩ እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው።
ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግርና የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት እንዲቆም፣ ህዝብን በጅምላ መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ ጨምርው ካነሱዋቸው አሳቦች በተጨማሪ በዋናነት ያነሷቸውን አሳቦች ከስር የመለከቱ። መግለጫቸውንም ያንብቡ።
- አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ይመቻች
- ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት ይስፈን
- ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸው
- የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ ይዘርጋ
- ሕዝባዊ ተሳትፎ ይረጋገጥ
- የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት (Early warning System) ይኑር
- የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሳይስተጓጎል ይቀጥል
- የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም
- የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ ይደረግለት
- ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ይወጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ጥሪያቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሰጡት መግለጫም አመልክተዋል።
ድርጅቶቹ በአሳብ ተመሳሳይ ይዘት ይዞ በስፋት ሲሰራ ከቆየው ከአገር አቀፍ የምክክር መድረክ በተለየ አዲስ የምክክር መድረክ እንዲመቻች የጠየቁበትን ምክንያት ይፋ አላደረጉም። ድርጅቶቹ አብዛኞቹ በስም መኖራቸው ጭምር የማይታወቅና ቀደም ሲል ተዘግተው ወይም በህግ ገለልተኛ አይደላችሁም በሚል በር የተዘጋባቸውና ከለውጡ በሁዋላ ህልውናቸውን ዳግም የገኙ ድርጅቶች ናቸው። ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው
- ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱተከሳሾቹ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ቀርበው በተፈጸመው የወንጀል… Read more: ብርቱካንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሽብር ወንጀልን ጨምሮ በሶስት ክሶች ተከሰሱ