ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይኖረው ወይንም ምልክቶችን ሳያሳይ ለከፍተኛ የጤና ችግር ብሎም ለሞት ሊዳርገን የሚችለውን የአጥንት መሳሳት ችግር ምንድን ነው?
ከሰውነት ክፍሎቻችን አጥንት ጠንካራው እና በቀላሉ የማይጎዳ ነው፤ ነገር ግን አጥንት በመሳሳት ምክንያት ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። አጥንትን ደካማ እና በቀላሉ ተሰባሪ የሚያደርገው የአጥንት መሳሳት ሕመም ነው።
ለመሆኑ የአጥንት መሳሳት ምንድነው?
አጥንት ሁልጊዜ በለውጥ ላይ ነው፣ በቋሚነት ሴሎቹ ይሞታሉ ቀጥሎም ይተካሉ። የአጥንት መሳሳት የሚከሰተው አጥንት የመተካት አቅሙ ሲቀንስ ነው፤ ነገር ግን በብዛት የሚበልጠው መገንባቱ ነው።

የአጥንት መሳሳት ወንድ ሴት ሳይል ሁሉንም የሚያጠቃ ሕመም ቢሆንም ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ሕመሙ ነጮች እና የሩቅ ምሥራቅ ሰዎች ላይ ይበረታል፤ በተለይ ደግሞ በዕድሜ የገፉ ሴቶች ላይ ይበረታል። ከአጥንት መሳሳት ጋር የተያያዙ ስብራቶች በአብዛኛው ወገብ፣ መዳፍ ወይም አከርካሪ ላይ ይስተዋላሉ።
የአጥንቱ አሠራር በአንድ በኩል እየተገነባ በአንድ በኩል ሲፈርስ፤ የአጥንታችን ጥንካሬው ጤናማ ይሆናል። የማፍረሱ ሂደት ሲያይል ነው የአጥንት መለስለስ የሚመጣው።
የአጥንት መሳሳት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
– በሽታው ገና ሲጀማምር ብዙ ምልክት አያሳይም፤ ነገር ግን አንዴ አጥንት ከሳሳ ወዲህ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፡-
– የጀርባ ሕመም
– ከጊዜ በኋላ ቁመት መቀነስ
– መጉበጥ
– በቀላሉ የሚሰበር አጥንት
አጥንት መሳሳት በምን ምክንያት ይመጣል?
የአጥንት መሳሳትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች አንዱ ዕድሜ ነው፤ ነገር ግን አሁን አሁን በወጣቶችም ላይ ይህ ችግር እያጋጠመ ይገኛል።
የቫይታሚን ዲ እና የካልሺየም እጥረት፤ እንዲሁም የእንቅርት በሽታ ለዚህ አይነተኛ መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
የአጥንት መተካካት ሂደት ከ20 ዓመት በኋላ እየቀነሰ ይመጣል፤ እድሜ በጨመረ ቁጥር የአጥንት ክብደት እጅጉን ይቀንሳል በመሆኑም ተጋላጭነቱም ከፍ ያለ ይሆናል።
ሌላው በዘር፣ በአኗኗር ዘይቤ፣ አልኮል አዘውትሮ መጠታት እና ሲጋራ ማጨስም መንስኤዎቹ ናቸው።
የጤና ሁኔታ እንደ ካንሰር፣ የኩላሊት ወይም የጉበት በሽታ እና የተለያዩ መድሃኒቶችን መጠቀም እንደመንስዔነት ይጠቀሳሉ።
ውፍረት፣የመገጣጠሚያ ሕመም እና ለስላሳ መጠቶችን ማዘውተርም ሌሎች ምክንያቶች ሆነው ይነሳሉ።
የአጥንት መሳሳትን መከላከያ መንገዶች
የአጥንት መሳሳት ችግርን ለመፍታት በካልሺየም የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ጤናማ አመጋገብ እና አካዊ እንቅስቃሴዎች የአጥንት መሳሳትን ከመከላከሉም በላይ የሳሱ አጥንቶችን ያጠነክራሉ።
ወተት እና አሳ የመሳሰሉ ምግቦችን ማዘውተር እንዲሁም ጨው እና ቡና በልኩ መጠቀም ይመከራሉ፡፡ ክብደት መቀነስ፣ በቂ የጸሀይ ብርሃን ማግኘት እና የለስላሳ መጠጦችን መቀነስም እንደመፍትሄ ተቀምጧል፡፡ ከአልኮልና ከሲጋራ ሱስ ነፃ መሆን እንደሚገባም ባለሙያዎች ይመክራሉ።
የአጥንት መሳሳትና ህመም ህክምና
_ የአጥንት ማደርጃ መድሃኒት
_የስብራት ተጋላጭነት መቀነሻ መድሃኒት
_ስብራት የመጠገን ህክምና እንደሆኑ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
መረጃዎቹን ከተለያዩ ምንጮች አግኝተናቸዋል
በሜሮን ንብረት – ኢፕድ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ” – የራሱን ሰርግ አቋርጦ ቀዶ ሕክምና በማድረግ ሕይወት የታደገዉ ዶክተር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በሌ ከተማ አስተዳደር የበሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ“በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው” አስገኘው አሽኮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር :- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በአንድ ታዋቂ ሙዚቀኛ (አስገኘው አሽኮ) ሴቶችን በተመለከተ በተሰጠ አስተያየት ላይ ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ እንደሚታወቀው በሀገራችን የሴቶችና የሴት ህፃናት ጥቃት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ፣ አይነቱን እየቀያየረና በአፈፃፀሙም እየረቀቀ የመጣ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ይህንንም… Read more: ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ
- መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?ዶክተር ጽዮን ተስፋ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም ናቸው። በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ «አለርት ጉርሻ» በሚል በኦን ላይን ፕሮግራማቸው «ትኩረት ያልተሰጣቸው» በሚባሉ የበሽታ አይነቶች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በዘፈቀደ ከምንንከባከባቸው አለያም ጭልጥ አድርገን ከምንረሳቸው የአካል ክፍሎችችን አንዱ መታወቂያና መለያችን የሆነው ፊታችን ነው። የፊት ቆዳ ተጋላጭ ከመሆኑም በላይ ሲቻል ሳይንሳዊ… Read more: መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?
- ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗልየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ ሀገር ጥለው የሚሰደዱ ሴቶች መኖራቸውም ተመልክቷል።የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአገር ውስጥ ቋንቋዎች የጥላቻ ንግግሮችን መቆጣጠር አለመቻላቸው ደግሞ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል ተብሏል። ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪሲሊንስ የተሰኘው የብሪታኒያ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በዚህ ወር ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው… Read more: ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል
- የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!ስርዓተ ቀብራቸው በዝነኛው የቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን አልተፈፀመም። ስለማይገባቸው ሳይሆን እሳቸው ስላልፈለጉ ነው። በኑዛዜያቸው መሠረት ስርዓተ ቀብራቸው ከቫቲካን ወጣ ብላ በምትገኘው ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን [ Santa Maria Maggiore ] ውስጥ ተፈፅሟል። ይህ ዘላቂ ማረፍያቸው እንዲሆን የመረጡት ቦታ በሮማን ኢምፓየር ዘመን [ባሮች] የሚቀበሩበት ስፍራ ነበር። እሳቸውም ከባለጠጎች እና ከዕውቅ ሰዎች ጎን ከማረፍ ይልቅ ከባሮች እና ከ[ተራ]… Read more: የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!