በ2012 ከነበሩት 46 ሺህ በላይ መምህራን አሁን ላይ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑት ከስራ ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የትምህርት ቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ በጦርነት ሳቢያ መምህራን ሞተዋል። ራሳቸውን ለማኖር ተሰደዋል። የኑሮ መመሳቀል ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የተሰደዱ ፣ የተፈናቀሉ ፣ አካላቸው የጎደለ እንዲሁም የሞቱ መምህራን መኖራቸውን አንስተው፤ ከ 2 ዓመት በላይ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ የተለያዩ ስራዎች ውስጥ የተሰማሩ መኖራቸውንም ሃላፊውን ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮኤፍ ኤም ነው።ሃላፊው የተቀሩት መምህራንም ቢሆኑ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ የስነልቦና ጉዳትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።
በክልሉ የነበረው ጦርነት በትምህርት ዙሪያ ሶስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷልም ነው ያሉት ሃላፊው። የት/ቤቶች መቃጠል ፣መፍረስ፣ መውደም አንደኛው ሲሆን ፤ በሰው ሃይሉ ላይ ያደረሰው ጉዳት ቀጥሎ የሚነሳ ጉዳይ ነው።
በሶስተኛነት የተነሳው ጉዳይ ደግሞ ስርዓተ ትምህርቱ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች በእድሜያቸው ልክ ማግኘት ያለባቸውን ትምህርት ባለማግኘታቸው አሁን ላይ 5ኛ ክፍል እና ከዛ በላይ መሆን የነበረባቸው ልጆች ገና የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በ2012 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቢወስዱ ምናልባት አሁን ላይ የ4ኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሚሆኑ ከ9ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ4 አመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰዳቸው የሚታወስ ነው።
በሌላ ዜና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና እንደሌለ ተገልጿል። ክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ በተጎዳበትና ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ በርካታ ቦታዎች በወራሪ ሀይሎች በተያዙበት ሁኔታ፣ ምርጫ ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ዜናው “ወራሪ” ያላቸውን አላብራራም።
ክልሉን እየመራ የሚገኘዉ ግዚያዊ አስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁነት የለዉም የሚሉት የዉድብ ናፅነት ትግራይ ዉናት ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቦ፣ አስተዳደሩ ወደ ምርጫ ገብቶ ለዉጥ እንዲመጣ ፍላጎትም ዝግጁነትም የለዉም ብለዋል።
በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ ቅርርብ መኖሩን የሚናገሩት የዓረና ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አንዶም ገ/ስላሴ ፣ በሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ውድብ ናፅነት ትግራይ እና ባይቶና አባይ ትግራይ ጥምረት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አረናም ጥሩ መቀራረብ ስላለዉ ምን አልባት መልካም ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫ ከተካሄደ በጋራ ለመወዳደር ዉይይት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ዓመት በ2016 ምርጫ ከሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች አንደኛዉ የትግራይ ክልል መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም። የትግራይ ክልልን ጨምሮ የስድስተኛው ዙር ቀሪ ምርጫዎችን በተለያዩ ጊዜያት ለማከናወን ዝርዝር ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳቀረበም አስታውቋል፡፡
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር የእግር ኳስ ኮከቦች ወደ… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ