“ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበት ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” ሲሉ በዓሉ 119 ዓመታትን ወደሁዋላ ሄዶ በዓሉን ማክበር የተፈለገበትን ምክንያት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ116ኛ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ላይ ንግግር ነው ይህን ያሉት። ፊልድ ማርሻሉ ኢትዮጵያ ረጅም ዕድሜ ያላት ቀደምት እና በትውልድ ቅብብሎሽ የዘለቀች ታላቅ ሀገር መኾኗን ገልጸዋል።
በእነዚህ ረጅም የታሪክ ዘመናትም በየትውልዱ በነበሩ ልጆቿ ተጋድሎ ነጻነቷ እና ክብሯ ተጠብቆ የተላለፈችልን ሀገር ናት ብለዋል።
መንግሥት በተለወጠ ቁጥር የሀገር እሴቶች እየፈረሱ በመሄዳቸው ቀደምት ጀግኖች እና ባለድሎች እየተዘነጉ፣ ተተኪው ትውልድም የጀግንነት እና የአርበኝነት ሞዴል እንዳያገኝ የሚያደርጉ ፖለቲካዊ እሳቤዎች ሲያጋጥሙን ቆይተዋል ነው ያሉት።
በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሥልጣን በመጡ መሪዎች እሳቤ ላይ ብቻ ተመስርተው ሲጻፉ የነበሩ ታሪኮች የጭቅጭቅ እና የግጭት መንስዔ ስለመኾናቸውም ተናግረዋል።
ትውልድ በጋራ የተግባባበት የጋራ ታሪክ ባለመኖሩ በአንድነት ቆሞ ሀገሩን ከመገንባት ይልቅ ገዥዎች በሚሰጡት አጀንዳ ጎራ ለይቶ ለመናቆር ተገዷል ብለዋል።
ለአብነትም በፊት ይከበር የነበረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን የቀደምት ጀግኖችን ታሪክ ቆርጦ ያስቀረ እና የረሳ ነበር ነው ያሉት። ከለውጡ በኋላ በተደረሰው ውሳኔ መሠረት ቀኑ ታሪክን አካታች በኾነ መልኩ እንዲከበር ኾኗል ነው ያሉት ፊልድ ማርሻሉ።
የመከላከያ ሠራዊት ቀን የሚከበርበትን ወቅት ለመምረጥ ጥናት ስለመደረጉም ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በዘመናዊ የመንግሥት አሥተዳደር ውስጥ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቋሚነት ተደራጅቶ እንደተቋም የተመሠረተበትን ቀን የሠራዊት ቀን በዓል ለማድረግ ተመራጭ ኾኖ ተወስዷል ነው ያሉት።
በዚህም መሠረት “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበት እና ሚኒስትር የሰየሙበት ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እየተከበረ ነው” ብለዋል ፊልድ ማርሻሉ።
ይህ ታሪካዊ ቀን ጥቅምት 15/1900 ዓ.ም ነበር። ለዚህም ነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን በየዓመቱ ጥቅምት 15 እንዲኾን የተወሰነው ብለዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን በዚህ ታሪካዊ ቀን መከበሩ ቀደምት ጀግኖችን ሞዴል ያደረገ፣ ከቀደምቶች ታሪክ የሚማር እና የሀገር አለኝታ የኾነ ሠራዊት ለመገንባት ስለማስቻሉ ፊልድ ማርሻሉ አመላክተዋል።
ዜናው የአሚኮ ነው
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበትየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን በስራ ፈጣሪ ቅድሚያ የሚነሱትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና “ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ” የተባለ ኩባንያን… Read more: በህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፤ ኤርሚያስ አመልጋ አሉበት
- በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸውአሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት… Read more: በመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ኢሳያስ ” አትራቡም የምንበላውን ቂጣ እናካፍላችኋለን” አሉ፤ ኢሳያስና መጨረሻቸው