በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦
” … ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል Shock ሆነዋል ?
ተማሪው እና ወላጁ ብቻ ነው እንጂ ይሄንን እዳ የተሸከመው ሁሉም ባለበት እየሄደ ነው ማንም ኃላፊነት እየወሰደ አይደለም።
ምንድነው እየተወሰደ ያለው እርምጃ ? የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከዛም እስከ ታች ያሉ ዳይሬክተሮች ሁሉም በነበረበት ቀጥሏል። በቃ ተማሪ አለፈ አላለፈ ጉዳያቸው አይደለም፤ ምንም አይቀነስባቸውም ምንም ማስጠንቀቂያ የለም ተማሪ አላሳለፈ አሳለፈ ጉዳዩ አይደለም።
እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መቀጠል አለብን ወይ ? አይደለም ይሄንን ቢያንስ ተጠያቂነት መኖር አለበት ብሎ የሆነ ነገር ማድረግ ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የሚሰሩ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ኃላፊዎች ናቸው። “
ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተጨማሪ ምን አሉ?
- በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና በላይ ይማምጣት አለማቻላቸው እንዲሁ እንደኖርማል የሚወሰድ አይደለም። ይሄን ያህል ተማሪ አለማለፉ እንድምታው ቀላል አይደለም።
- በዚህ ነገር ተጠያቂ የሚሆነው ” ሁሉም ነው ” የሚለው ነገር አይቸጋሪ ነው። ተጠያቂው everybody ሁሉም ነው ነው ከተባለ nobody ማንም ነው ማለት ነው።
- ” ሁሉም ተጠያቂ ነው ” ማለት እነማናቸው ሁሉም ? ሁሉም የሚለው መፍትሄ አያመጣም። ወላጅ የራሱ ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቢሮ በየደረጃ ከሆነ ያግባባናል።
- በሀገር ደረጃ አስፈፃሚዎች (እንደ ገንዘብ፣ ጤና…ሚኒስቴሮች) የተደራጁት በራሳቸው ተልዕኮ አኳያ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ተልዕኮ ይሄ የኔ ውድቀት ነው ብሎ መውሰድ አለበት።
- ትምህርት ሚኒስቴር ውድቀቱ የኔነው ብሎ ሲወስድ በስሩ ያሉ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችን ጨምሮ ነው።
- እነዚህ ተማሪዎች ከታች ጀምሮ 50 በመቶና በላይ እያመጡ ነው እዚህ የደረሱት ይህ የሚያሳየው ከታች ጀምሮ የምዘና ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ነው። የትምህርት አሰጣጡም ችግር አለበት። አንዳንዶቹ እራሳቸው የማያውቁት እንዲያስተምሩ ይደረጋል፤ አንዳንዶች ደግሞ ኮሌጅ ሳይገቡ፣ ዲፕሎማ ዲግሪ ሳይኖራቸው የሀሰት ማስረጃ አሰርተው ዓመታት ሲያስተምሩ የቆዩ መኖራቸንም በሚዲያ ሰምተናል። ስለዚህ አጠቃላይ ስርዓቱ መፈተሽ አለበት።
- ከታች ጀምሮ ብቁዎች ብቻ ለ12ኛ ክፍል እንዲቀመጡ እያደረግን ነው ?
- ኩረጃ ስላስቀረን ነው ተማሪው የወደቀው የሚለው ሁሉንም ላያስምን ይችላል። በተወሰነ ደረጃ እውነት ነው።
- ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይጠና። #ገለልተኛ ምሁራን የተካተቱበት ጥናት ይደረግና በዋናነት ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይታወቅ፤ ሌሎችም ምክንያቶች ካሉ ይጠና። እንዴት ይሄን ማስተካከል እንደሚቻል መፍትሄ ይመላከት። ያለዛ መፍትሄ አይገኝም።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ ገለልተኛ ጥናት ምን አሉ ?
” ገለልተኛ ጥናት ቢደረግ ለተባለው፤ ይሄ ተቋም (ፓርላማው) ገለልተኛ ስለሆነ ከተቻለ ነፃ የምሁራን ኮሚቴ አቋቁሞ ጥናቱን ለምን አያደርግም ? “
ዶ/ር ነገሪ ፤ ፓርላማው በጥናቱ ሰው ማሳተፍ እንደሚቻል ነገር ግን በባላይነት ኮሚቴ አቋቁሞ ለመስራት ከአሰራር አኳያ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ጥናቱ ለሚኒስቴሩም ግብዓት ይሆናል ማለታቸውን የትክቫህ መረጃ ያስረዳል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria, and the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ።… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ