ፕሮስቴት እጢ በወንዶች ፊኛ በታች የሚገኝ ተፈጥሯዊ የሰውነት አካል ነው ፡፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ዩሮሎጂ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አብዱልሀዚዝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷የፕሮስቴት እጢ ዋነኛ ተግባር የዘር ፈሳሽ በማመንጨት ወደ ፊት ለፊት እንዲወጣ በማገዝ ለመራቢያነት ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የበሽታው መንስኤ ብለን የምንጠራቸው ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ተፈጥሯዊ መሆናቸውንም ነው በቆይታቸው የገለጹት፡፡
እጢው በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ እንደመሆኑ መንስኤው በጾታ ወንድ መሆን ሲሆን÷ እጢው ሊያድግ የሚችልባቸው ጊዚያቶችም አንደኛው ምክንያት አንድ ወንድ ለአቅመ አዳም ሲደርስ መሆኑን እና ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ እድሜው በ50ቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ ነው ይላሉ፡፡
ሌላኛው መንስኤ ቤተሰብ ውስጥ በፕሮስቴት እጢ ምክንያት የጤና ችግር ያጋጠመው የቤተሰብ አባል ሲኖርም በዘር ምክንያት የመጋለጥ እድል እንደሚኖረውም ያነሳሉ፡፡
በተጨማሪም÷ አንድ በጾታ ወንድ የሆነ ሰው የስኳር ፣የደም ግፊት፣የኮሌስትሮል መብዛትና የክብደት ከመጠን በላይ መጨመር ካለ ተጋላጭነቱ ሊሰፋ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
የእጢው እድገት ችግር ላያመጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የጤና ችግር በሚፈጥር መልኩ የሚያስቸግርበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ይጠቅሳሉ፡፡
የጤና ችግር የሚፈጠርበት ምክንያት የእጢው መገኛ የሽንት ፊኛ አንገት ላይ በመሆኑ የእጢው ማደግ ቀጥታ ከመሽናት ችግር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡
የፕሮስቴት እጢ ምክንያት የሚመጣው የጤና ችግር የሚከተሉትን ምልክቶች እንዳሉት የሚገልጹት ዶ/ር መሀመድ ሽንት ለማጠራቀም መቸገር (ቶሎ ቶሎ መሽናት)፣ሲሸኑ የማቃጠል ስሜት መሰማት፣ለመሽናት መቸገር ፣ሽንት በደምብ ያለመፍሰስ፣ የሽንት መቆራረጥ የመሳሰሉት በዋነኝነት እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል፡፡
የፕሮስቴት እጢ ቀላልና ከባድ ህመሞች የሚያስከትል ሲሆን÷ እንደ ችግሩ ሁኔታ መፍትሔውም የሚለያይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ቀለል ያሉ የፕሮስቴት እጢ ችግሮች በምክርና በክትትል ሊሻሻሉ የሚችሉ እንደሆኑ የሚገልጹት ዶ/ር መሀመድ ከበድ ያሉት ደግሞ የህክምና እገዛ የሚፈልጉ ማለትም በመድሃኒትና በቀዶ ጥገና ጭምር የሚታገዙ እንደሆኑ ያነሳሉ፡፡
እጢው ከበድ ያለ ህመም ወደ ማስከተል ደረጃ ደርሶ የህክምና ክትትል ካልተደረገ ግን እንደ የኩላሊት ስራ ማቆምና ወደ ሌሎች ውስብስብ ችግሮች ሊያመራ ስለሚችል ከላይ የተጠቀሱትን የህመሙ ምልክቶች የሚያሳይና በተለይ ደግሞ እድሜው በ50ቹ የእድሜ ደረጃ ላይ ያለ ወንድ የጤና ባለሙያ ሊያየው እንደሚገባም ይመክራሉ፡፡
FBC
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ“በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው” አስገኘው አሽኮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር :- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በአንድ ታዋቂ ሙዚቀኛ (አስገኘው… Read more: ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በድምፃዊ አስጌ ላይ የተሰጠ መግለጫ
- መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?ዶክተር ጽዮን ተስፋ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም ናቸው። በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ «አለርት ጉርሻ» በሚል በኦን ላይን ፕሮግራማቸው «ትኩረት ያልተሰጣቸው»… Read more: መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?
- ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗልየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ ሀገር ጥለው የሚሰደዱ… Read more: ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል
- የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!ስርዓተ ቀብራቸው በዝነኛው የቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን አልተፈፀመም። ስለማይገባቸው ሳይሆን እሳቸው ስላልፈለጉ ነው። በኑዛዜያቸው መሠረት ስርዓተ ቀብራቸው ከቫቲካን ወጣ ብላ በምትገኘው ቅድስት ማሪያም… Read more: የኖሩት ከድሆች ጋር – የጮኹት ለድሆች – ቀብራቸውም በድሆች መሐል !!