የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሩ ክብር የሚከፍለው መስዋዕትነት በተግባር ከታየባቸው ቀናት መካከል ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አንዱ ነው፡፡ በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በሀገራችን ታሪክ ጥቍር ጠባሳ አሳርፎ ያለፈ ክስተት ነው፡፡ ይህ በሠራዊቱ አባላት ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡
በሠራዊታችን ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ፣ ወደ አውዳሚ ጦርነት ጎትቶ ያስገባንና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ በመኾኑ ሊረሳ የማይችልና ሊደገም የማይገባዉ አሳፋሪና አሳዛኝ የታሪክ አንጓ ነው፡፡ ምንም እንኳን ጥቃቱን ተከትሎ የተገባበትን ጦርነት በሠላም ስምምነት መቋጨት ቢቻልም ቀኑ በታሪካችን እንደ ነውር መቆጠር ያለበት ተግባር የተፈፀመበት ቀንና ትምህርት የሚወሰድበት ክስተት በመሆኑ ዕለቱ ሁሌም ሊዘከር ይገባል፡፡
ይሄንን ቀን የምናስበው ለቂምና ለበቀል አይደለም። ያ ስሕተት እንዳይደገም ነው። እናቶች የሚያለቅሱበት፤ ወጣቶች የሚማገዱበት፣ የሕዝቦች ትሥሥር የሚላላበት፤ ቤተሰብ የሚበተንበት፣ የሀገር ሀብት የሚወድምበት የጦርነት መንገድ ይብቃ ለማለት ነው።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተፈጸመዉን ጥቃት በመቀልበስ በኢትዮጵያ ላይ ተከፍቶ የነበረዉን ጦርነት በጋራ ርብርብ መክተን የሀገራችንን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት አስጠብቀናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ሊሳካ እንደማይችል ፅኑ ማሳያ ነው:: በመሣሪያ ኃይል ሥልጣን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት በኢትዮጵያ ምድር ሊሳካ እንደማይችል አረጋግጧል፡፡
መንግሥት ለዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ለሀገር አንድነት ሲል ችግሩን በሠላማዊ መንገድ ለመቋጨት የወሰነው፤ ተመሳሳይ ስሕተቶች በየትኛውም አካባቢና ጊዜ እንዳይደገሙ ትምህርት እንዲወሰድበት ለማስቻል ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊትን ማጥቃት መደገም የሌለበት ትልቅ ስሕተት መኾኑን በዚህ ወቅት በየጥሻዉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ሊገነዘቡት ይገባል፡፡
መከላከያ ሠራዊታችንን ማጥቃት የሀገራችን የኅልውናዋ የመጨረሻ ምሽግን መንካት እንደኾነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በየመንደሩ እየዞሩ የሕዝብን ሰላም የሚነሱ፣ ዝርፊያ የሚፈጽሙና ሀብት የሚያወድሙ አካላትም እየሄዱበት ያለው መንገድ የስህተት መሆኑን ተገንዝበው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የሚፈፅሙትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል፡፡
ወንዝ የማያሻግር የፅፈኝነት ዓላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ የመንደር ታጣቂዎች፤ ትልቅ ሀገራዊ ራእይ ሰንቆ የተሰለፈዉን መከላከያ ሠራዊታችንን በማጥቃት ምንም አይነት ድል እንደማያገኙ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዘብ የቆመው ሰራዊታችን ዛሬም በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
መከላከያ ሠራዊታችን በጥቅምት 24 የደረሰበትን ጥቃት አልፎ፣ ሀገራችን ላይ የተከፈተውን ጦርነት መክቶና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በመሥዋዕትነቱ አስከብሮ ኢትዮጵያን ከታላቅ አደጋ ታድጓል፡፡ በዚህ ወቅት መከላከያ ሠራዊቱ ለሀገራችን እየከፈለ ያለዉን ክቡር መሥዋዕትነት በማቃለል የሐሰት ቅስቀሳ የሚያሰራጩ አካላትም ከባለፈው ስህተት ተምረው ከእኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል፡፡
ጥቅምት 24 ጥቃት የተፈጸመበት ጀግናዉ ሠራዊታችን አሁን ላይ የበለጠ ዐቅሙን በሰው ሃይል፣ በስነምግባር፣ በመሳሪያ፣ በቴክኖሎጂና በወታደራዊ ሳይንስ ገንብቶ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ከማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጥቃት ጠብቆ ኢትዮጵያን ወደላቀ ከፍታ ለማሸጋገር በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ምንግዜም ፍላጎታቸው ሰላም፣ ልማትና አብሮነት ብቻ ነው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንም እነዚህን የሕዝብና የመንግሥት ፍላጎቶች እውን ለማድረግ ማንኛዉንም መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው፤ እየከፈለም ነው፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ ቅጥረኞች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሐሰት ዘመቻዎችን ከፍተው የሰራዊቱን ክቡር ስም ለማጠልሸት ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ ሆኖም ሠራዊታችን እንኳን ከሃሰተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈጸመበት ጥፋት እንኳ የማይንበረከክ ፅኑ መሰረትና ኢትዮጵያዊ ጀግንነት የተላበሰ መኾኑን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም በተለመደው ደጀንነቱ ሠራዊቱን ለላቀ ድልና ክብር እያበረታታ ይገኛል።ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል፡፡ መከላከያ ሠራዊትን የማጥቃት የባንዳነት ተግባር በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ለዚያም ነው ዘንድሮ የጥቅምት 24ን ለሦስተኛ ዓመት ስናስብ ይህ አይነት የሃገር ክህደት እንዳይረሳም እንዳይደገምም የምንዘክረው፡፡
ክብር ለሀገር ሉዓላዊነት ለተሠዉ ጀግኖች!!
ይቅር እንላለን ግን አንረሳም፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies in Washington. … Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ ሰባት ለአንድ፣… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል