ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚለው ቡድን ህገመንግስቱን አክብሮ ከመንግሥት ጋር ለሁለተኛ ዙር ንግግር መቀመጡ ተከትሎ የተደበላለቀ ስሜት መፈጠሩ ተሰማ። በአማራ ክልል የተጀመረውን ጦርነት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ለማቀናጀት በግልጽና በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ ዜናው የሚታመን አልሆነም። በተለይም ለኤርትራ መንግስት አስደንጋጭ መሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮ 12 ከመንግስት ወገን ጠይቃ እንዳረጋገጠችው ንግግሩ የተጀመረው ትናንት ነው።
በታንዛንያ በተጀመረው የሁለቱ ወገኖች ንግግር እየተካሄደ ያለው በታንዛንያ ዳሬሰላም Hyatt Regency Hotel ነው። በንግግሩ የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ አምባሳደር ሚክ ሃመር የኢጋድ ወኪል የሆኑ አንጋፋ ዲፕሎማቶች፣ የኖርዌይና ኬንያ መንግስት ተወካዮች እንዳሉበት አዲስ ስታንዳርድ ምንጮች ጠቅሶ ጽፏል።
ተቀማጭነታቸው በውጭ አገር የሆነና በአገር ውስጥ የሚደረገውን የትጥቅ ትግል የሚደግፉ፣ የሚመሩና ጦርነቱን ከሚፈልጉ አገራትና ሃይሎች ሎጅስቲክ በማሰባሰብ ላይ ያሉ ዜናው “መርዶ” እንደሆነባቸው ተሰምቷል። በተለይም በአደባባይ “የጋላ መንግስት” በሚል ባነር ለጥፈው ሲሳደቡ የነበሩ ሃይሎ ዜናውን አልወደዱትም። ይህ እንቅስቃሴ በይፋ “ወለጋ የእና ነው” በሚልና “የኢትዮጵያ ብቸኛ ባለቤት እና ነን” በሚል በይፋ መናገሩ በኦሮሞ ተወላጆች ዘንዳ “ልዩነት ይወገድ፣ አንድ እንሁን” የሚል ስሜት መፍጠሩን ኢትዮ12 መዘገቧ አይዘነጋም።
ከዚህም በተጨማሪ በኦሮሚያ የታጠቁ ሃይሎች እያደረሱ ያለው ጉዳትና ዝርፊያ፣ እገታና ግድያ ነዋሪዎችን በማማረሩ የተነሳ እያደር የተቀባይነት ማጣትም ለንግግሩ ገፊ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል። ኢትዮጵያና ኬንያ የገቡት ስምምነት በቅርቡ ወደ ትገባር የሚሸጋገር በመሆኑ ቦርና ጫፍ ላይ ያለው ይህ ሃይል ህልውናው አደጋ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል ቅድሚያ ስምምነቱን ተከትሎ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።
በንግግሩ የመከላከያ ደህንነት ሃላፊ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ምክትላቸው ሜጀር ጄነራል ደምሴ አመኑ ኢትዮጵያን ከወከሉት አባላት መካከል እንደሚገኙበት አዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። አክሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊይ የደቡብ ኮማንድ አዛዥ ናቸው የተባሉት ገመቹ ረጋሳና ምክትላቸው ጃል ገመቹ አቦዬ ከኬንያ ተነስተው ወደ ንግግሩ ስፍራ ማምራታቸው አምልክቷል።
ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም ዓይነት ይፋዊ ማብራሪያም ሆነ ፍንጭ ባይሰማም ንግግሩ መጀመሩን ያረጋገጡልን አንድ ከፍተኛ የኦሮሚያ ክልል አመራር ስማቸውና ማንነታቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጓቸው የክልሉ ነዋሪዎች ለንግግሩ መሳካት ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱና ከመጀመሪያው ንግግር የተለየ ውጤት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በኩል በመጀመሪያው ንግግር ህገመንግስት የሚጻረር ጥያቄ መቀረቡን፣ ያም ሆኖ ጥሩ የሚባል ንግግር መደረጉን ከመንግስት ወገን ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ ዝርዝሩን ባያቀርቡም የኦሮሞ ነሳነት ሰራዊት አመራር እንደሆኑ የተሚነገርላቸው በተመሳሳይ ንግግሩ የሚፈለገውን ውጤት ባያመጣም በጎ የሚባል እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም።
ዜናው በአማራ ክልል የተነሳውን ጦርነት ከኦሮሚያው ንቅናቄ ጋር የማጣመር ስራ እየተሰራ መሆኑን፣ ይህም ተጠናክሮ መንግስትን ለማስወገድ ልዩ ሃይል እንደሚፈጥር ሲገልጹ በነበሩ ሃይሎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል።
ኦነግ ከነአመራሮቹ አዲስ አበባ ተቀምጦ የኦሮሞ ነጻ አውጪ በሚል ስያሜ ሃይል አሰባስቦ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ይዞታውን አስፍቶ የቆየው ይህ ሃይል አሁን ላይ አብዛኛውን አካባቢዎች እንደተነጠቀ ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው። የመንግስት ሃይሎች አብዛኛውን አካባቢዎች ነጥቀው በያዙበትና ኦፕሬሽናቸውን አስፍተው እየሰሩ መሆናቸውን እያስታወቁ ባሉበት ወቅት የእርቅ አማራጭ ለመፈለግ ንግግር መደረጉ ከኤርትራ በኩልም ደስታን አልፈጠረም።
ከሃያ አመታት በላይ የኦነግ ሰራዊትን ስልጠናና ድጋፍ በማድረግ ሰብስቦ በማገት እርከንና የልማት ስራ ሲያሰራቸው እንደነበር እማኞች ክስ የሚያቀርቡበት የኢሳያስ አፉወርቂ መንግስት፣ በኦሮሚያ ዕርቅ ከወረደ በሌሎች አካባቢዎች የሚካሄዱ የጠብመንጃ እንቅስቃሴዎች የመክሰማቸው ጉዳይ ሰፊ በመሆኑ ስጋት እንደገባው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው።
ትህነግ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ፈጽሞ በተቀሰቀስው ጦርነት ሳቢያ ከመንግስት ጎን ለጎን ሆኖ የተዋጋው ሻዕቢያ፣ አሁን ድረስ የያዘውን መሬት እንዲለቅ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ፈቃደኛ እንዳልሆነ የሚገልጹ፣ በኦሮሚያ ሰላም ከወረደ ምን አልባትም መንግስት ሃይል ሊጠቀም ይችላል የሚለው የሻእቢያ ስጋት እንደሆነ አመልክተዋል።
በድርድሩ በተለይም ሚክ ሃመር እዚህ ጉዳይ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትግራይ ክልል አመራሮች ጋር ያላቸው ግንኙነት አንድ ላይ ተዳምሮ አሜሪካ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ ያላት አቋም ዳር እንዲደርስ የታሰበ ነገር እንዳለ አመላካች አድረገው የሚያዩም ድምጻቸው እየተሰማ ነው።
በሌላ በኩል ዜናው በስምምነት ከተቋጨ በኦሮሚያ ሸኔ በሚባል ስም የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ የማን ወገን እንደሆነ በየፊናቸው ሲሰራጩ ለነበሩ መረጃዎች ምላሽ የሚሰጥ፣ አቶ ዳውድ የሚመሩት ቡድን ሚና ምን እንደነበር አደባባይ የሚያወጣና ሁሉንም ወገን ከነተግባራቸው የሚያጋልጥ በመሆኑ ግራ የተጋቡ ውጤቱን በጉጉት እየተበቁ ነው።
በኦሮሚያ ዘራፊና ዓላማ የሌለው የሰፈር ልጆች ስብስብ ያለው ታጣቂ፣ ከኦነግ ሸኔ ነኝ የሚልና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚል ሃይል እንዳለ ነዋሪዎች ከነተግባራቸው በመለየት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። አንዳንዴም የኦሮሚያ ብልጽግና ውስጥ ያሉ በዚህ ጉዳይ ሲከሰሱ ይሰማ ነበር። በስጋትና በኩርፊያ ከጀርባ ሰራዊት እያደራጁ ክልሉን የሚያምሱ መኖራቸውን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም በራሱ በፓርቲ ውስጥ ያሉ ሲያስታውቁ ነበር።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል