በመንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም አማራጭ ለመፈለግ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም እየተካሄደ ያለው ንግግር መግባባት እየታየበት እንደሆነ ተመለከተ። በዚሁ ምክንያት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ድርድሩን ትላንት መቀላቀላቸው ተሰምቷል።
ኢትዮ12 የሰላም አማራጭ ንግግሩ ሲጀመር የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪ ሄሊኮፕተር ተዘጋጅቶላቸው ከደንቢዶሎ ወደ ኬንያ ማምራታቸው ንግግሩ ቀደም ሲል ብዙ ርቀት የተኬደበትና ተስፋ የሚሰጥ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ምንጭ ጠቅሳ መዘገቧ ይታወሳል።
” ኦሮሞ ዛሬ ላይ ጠብ መንጃ የሚያስፈጽመው አንዳችም ጉዳይ የለም” የሚሉ መበራከታቸው፣ ወለጋን የመሰለ ለምና ሃብታም ገበሬ ለማኝ መሆኑ፣ የቡና አምራችና ነጋዴ ሃብታም አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች መሰደዳቸው፣ ሃብታቸውና ንብረታቸው ተዘርፎ ተመጽዋች መሆናቸው፣ በጥቅል ኦሮሚያ በግፍ የሚገደሉና የሚፈናቀሉ፣ ቤት ንብረታቸው የሚነድና የሚዘረፍባቸው … አንድ ላይ ተዳምሮ ህዝብ በትጥቅ ትግሉ እንደተሰላቸ የሚያሳዩ ምልክቶች በስፋት ታይተዋል።
ከምንም በላይ ግን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚባለውን ታጣቂ ቡድን የሚመሩት ጃል መሮ በቅርቡ በውጭ አገር ያሉትንና በትግሉ ስም ገንዘብ እይሰበሰቡ እንደሚሰርቁ፣ ለታለመለት ዓላማ እንደማያውሉ አንስተው ክፉኛ መተቸታቸው ድርጅቱ የኢኮኖሚ አቅሙ መዳከሙን የሚያሳይ እንደሆነ አመላካች እንደሆነ ጉድዩን የሚከታተሉ ይናገራሉ።
ሰሞኑንን መንግስት በተደጋጋሚ እንደሚናገረው በኦሮሚያ ክልል ነፍጥ አንስቶ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ይህን ሃይል ለማጥፋት ሙሉ ዘመቻ ተከፍቷል። በዚሁ ዘመቻ ቡድኑ ቁሳዊ፣ ሰብዓዊ ኪሳራ እንደደረሰበት፣ በቁጥጥሩ ስር አድርጓቸው የነበሩ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መነጠቁን፣ አመራሮቹን ጨምሮ በርካታ መማረካቸውና እጅ መስጠታቸው መንግስት በተለይም የአገር መከላከያ እያስታወቀ ነው። የሎጅስቲክ ምንጩም መዳከሙን መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰሞኑን አመልክቷል።
ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር በጣምራ አብሮ ሲሰራ የነበረውና ከፍተኛውን በጀትም ከትህነግ ያገኝ እንደነበር የሚነገርለት የጃልመሮ ቡድን ትህነግ ለሰላም እጁን ከሰጠ በሁዋላ በጀት እያጠረው እንደሆነ በወቅቱ መገለጹ አይዘነጋም። ይህንኑ ተከትሎ ነበር ከስድስት ወር በፊት የመጀመሪያ የሰላም ንግግር የተደረገው። ምንም እንኳ ንግግሩ በሙሉ ስምምነት ባይቋጭም ክማሮው ለቀጣይ ውይይት በር ከፋች እንደሆነ ከሁለቱም ወገኖች መነገሩ ይታወሳል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪ ቡድን በዋና አዛዡ ድሪባ ኩና ወይም ጃል መሮና ምክትላቸው ጃል ገመቹ አቦዬ በንግግሩ እየተሳተፉ እንደሆነ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጎል። ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥም አመልክቷል። ንግግሩ በጦር መኮንኖች መካከል በስምምነት በመጠናቀቁ በሚታወቅ ተቋም ይፋ ባይሆንም ከመንግሥት በኩል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ በትናንትና ዕለት መቀላቀላቸው ተሰምቷል።
ቡድኑ ስለድርድሩ ባሰራጨው አጭር መረጃ ንግግሩ በበጎ ገጽታው እየቀጠለ መሆኑን አስታውቋል። ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ እንደገለጹት ንግግሩ በስምምነት እንደሚቋጭና ሰላም ለናፈቃቸው ወገኖች መልካም ዜና እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።
ጃልመሮ “ለምን ይደራደራል” የሚሉና ” እንዴት ከአሸባሪ ጋር መንግስት ለንግግር ህይቀመጣል” በሚል ከወዲሁ የራሳቸው አጅንዳ ባላቸው በኩል የሚሰራጨው ቅስቀሳ ውጤቱን በጉጉት ከሚጠብቁት እኩል ገና ለገና አጀንዳው በሰላም ከተቋጨ አሳባቸው ሊጨነግፍ እንደሚችል የሰጉ ብዙ ናቸው።
በንቅናቄ ስም በሚጠራ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ” የኦሮሚያን ጉዳይ ጨርሰው በሙሉ ሃይላቸው አማራና ኤርትራ ላይ ሊዘምቱ ነው” የሚል አስተየተ የሚያሰራጩም ታይተዋል።
በተመሳሳይ ” በነካ እጃችሁ አምራ ክልል ላይም ብዙ ኪሳራ ሳይደርስ የሰላም ንግግር እንዲደረግ ግፊት ይደረግ” የሚሉ ሰላም ወዳዶች እጅግ በርካታ ናቸው።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ