በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ አጣቢዎችን ማንነት ለማወቅ ከባህር ማዶ ቢሮ ከፍተው ዶላር የሚሰበስቡትን ከመጠርሪያ ስማቸው በመነሳት መለያየት ቀላል ነው። በውጭ አገር ሆነው ፖለቲካ በመቀመርና ለፖለቲካ ቅመራው እርዳታ በመጠየቅ የዲጂታል ለማኝ የሆኑት ቢያንስ ይህን ስራ ቢሰሩ እንደሚሻላሸው ምክር የሚሰጡት ስራው እጅግ ከፍተኛ ገንዘው ወደ ሌላ አገር እያሻገረ በመሆኑ ነው።
በዚሁ የምንዛሬ አጠባ ሁለት አበይት ጉዳዮች ይነሳሉ። አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ኮንትሮባንድ ላይ የተሳተፉ ህዝብ የሚያውቃቸው “የውጭ ዜጎች” በህገወጥ ንግድ በሚሊዮኖች ብር ይሰበስባሉ። የአገሪቱን ኢኮኖሚ ያደቃሉ። ከውጭ ሆነው ምንዛሬ በመቀበል ኢትዮጵያ ውስጥ በኮንትሮባንድ በሚሰብሰበው ብር ከፍተኛ ምንዛሬ ይሰጣሉ።
በዚህ ስራ የተሰማሩት ክፍሎች ከውጭ ገንዘብ ለተላከላቸው ሰዎች ያለው ውድድር፣ ያለቀረጥ ክፍያ በኮንትሮባንድ ያፈሱትን ገንዘብ ወደ ውጭ ገንዘብ በመቀየር ለራሳቸው አገር የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንደሆኑ ስራውን የሚያውቁ በተደጋጋሚ ያስረዳሉ። አዲስ አበባ ከትመው ኢትዮጵያን በሁለት ካራ የሚገዘግዙት እነዚህ ክፍሎች በህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ በስፋት ከሚሰሩት መካከልም ናቸው። ይህን የኋላ ጉዳይ ያስታወሰው ዛሬ የተሰማው የህገወጥ ዶላር ህትመትና አዘዋዋሪዎች መያዝ ነው።
በአዲስ አበባ በህገወጥ የታተመ የውጭ ምንዛሬ በድብቅ ሲያዘዋውር ነበር የተባሉ ተጠርጣሪ ተይዟል። የመንግስት መገናኛዎች ባሰራጩት በዚህ የሌብነት ዜና የተያዘው ተጠርጣሪ ማንነትና ስም አለመጠቀሱ ጥርጣሬ አስነስቷል። ዜናውን ተከትሎ ” ባትነግሩንም አውቀናቸዋል። ገንዘብ ዝውውር ስር የሚራወጡት ይታወቃሉ” የሚል አስተያየትም ተሰጥቷል።
ከ28ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሲያስታውቅ፣ ይፋ የተደረገው ተጠርጣሪው ሲጠቀምበት የነበረ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C 32496 አ/አ በሆነ ተሽከርካሪና ኤግዚቢት የተያዘውን ብር ነው።
ስሙ እንዲገለጽ ያልተፈለገው ተጠርጣሪ 284 ባለ መቶ ኖቶች(28 ሺህ 400) ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መክሊት ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። በተደረገ ፍተሻ ከሃሰተኛ ዶላሩ በተጨማሪ ስታር ሽጉጥ ከ 8 ጥይቶች ጋር ተገኝቶበታል።

በአዲስ አበባ የዶላር አጠባ ላይ በብዛት የተሰማሩ ወገኖች እነማን እንደሆኑ የሚታወቅ በመሆኑ፣ የስም ስወራው ጉዳዩን ለማድበስበስና ታልሞ ሊሆን ይቻላል የሚል ስጋት ያላቸው ” ማንነቱና ስሙ ይገለጽ። ሌብነት ላይ የተተከለ ዲፕሎማሲ ጥንቅር ብሎ ይቅር” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የአገር ስም ጠርተው ” ሚስጢር አይደለም” ያሉም አሉ።
ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማተምና ወደ ገበያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና ሐሰተኛ የውጭ ሀገራትና የኢትዮጵያን ብር በማተምና በማሰራጨት የተጠረጠሩ የካሜሩንና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦቸ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ፖሊስ ስማቸውንና ማንነታቸውን ይፋ አደጓል።
ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመትና ስርጭት እንዲሁም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉና የወንጀል አፈጻጸም ሂደቶቻቸውም እየተወሳሰበ መምጣቱን ተከትሎ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምስጢራዊ ክትትል ሲደረግ መቆየቱንና በጸጥታ አካላት እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ሐሰተኛ የውጭ ሀገራትና የኢትዮጵያን ብር በማተምና በማሰራጨት የተጠረጠሩ የካሜሩንና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች እንዲሁም በተባባሪነት ስትሳተፍ የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ ላይ ይገኛል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 እና 04 እንዲሁም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የግለሰቦችን ቤት በመከራየት ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመትና ስርጭቱን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ለረጅም ጊዜ በተደረገው ክትትል በመረጃና በማስረጃ በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

አልበርት ናዲፎን በሚል ስም የሚጠራው ካሜሩናዊና መሀመድ ጉኒ የተባለው የጊኒ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከስድስት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ማህሌት ጥላሁን ከተባለች ኢትዮጵያዊት ጋር ሕገወጥ ድርጊቱን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከግለሰቦች ተከራይተው ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመቱን ሲያከናውኑባቸው የነበሩ ሦስት የመኖሪያ ቤቶች በጥናት ተለይተው ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደባቸው ወቅት ለወንጀል ድርጊቶቹ የሚጠቀሙባቸው በርካታ ኤግዚቢቶች ተይዘዋል፡፡
ሐሰተኛ ገንዘቦቹን ለማተም የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ቁሶች፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ፓውደሮች፣ሐሰተኛ ገንዘቦች፣ የዶላር ማረጋገጫ ቴስት ላይት፣ ፓስፖርቶች፣ የባንክ ደብተሮች እንዲሁም አደንዛዥ እፅና ሌሎችም ማስረጃዎች ከተያዙት መካከል ይገኙበታል ሲሉ የመንግስት መገናኛዎች ዘግበዋል።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል