Radric Davis ( ጉቺ ሜን ) አሜሪካዊ ራፐር ነው ። ከጎኑ ያለችው ደሞ Keyshia Ka’Oir ትባላለች ሞዴሊስት ጎበዝ አክትረስና ኢንተርፕረነር ነች ። እና ከአመታት በፊት ፍቅረኛዋ ጉቺ ሜን በአንድ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበና የሶስት አመት እስር ተፈረደበት ።
ጉቺ ሜን ይህን የዳኞቹን ውሳኔ እንደሰማም ፍቅረኛውን ኬይሽያን ወደ እስር ቤት እንድትመጣ ላከባት ። እየውልሽ በእስር ቤት ቆይታ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም። ስለዚህ በስሜ ያለውን ሁለት ሚሊየን ዶላር ወደ አንቺ ባንክ አካውንት እንዲዛወር እፈልጋለሁ አላት ። እና በባንክ ያለውን ብር በሙሉ አንድም ሳያስቀር ለፍቅረኛው ኬይሽያ ሰጣት ። ጓደኞቹ ቀለዱበት። ታስረህ ስትፈታ ጎዳና ልትወድቅ ነው? ይህን ሁሉ አመት ትጠብቀኛለች ብለህ አታስብ አሉት።

.Keyshia Ka’Oir ፍቅረኛዋ የሰጣትን ገንዘብ ከባንክ ያወጣችው ብዙም ሳይቆይ ነበር ። እናም በገንዘቡ የራሷን Ka’Oir የሚባል የኮስሞቲክስ ማምረቻ ከፍታ መንቀሳቀስ ጀመረች ።
.ጊዜው ሳይታወቅ ሄዶ ፍርደኛው ራፐር ጉቺ ሜን የእስር ጊዜውን ጨርሶ ወጣ ። ጓደኛው ኬይሺያ በስራ ምክንያት ቢዚ ብትሆንም አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቀው ነበር ። እና እንደተፈታ በዘመናዊ መኪና መጥታ ወደ አዲስ ቤት ይዛው ሄደች ። ከዚህ ሁሉ አመት መለያየት በኋላ ትጠብቀኛለች ብሎ ባያስብም እሷ ግን ከአመታት በኋላም ሳትቀየር ነበር ያገኛት ። እና ቤት ደርሰው አረፍ ካሉ በኋላ ፡
” ጉቺ እስር ቤት ስትገባ በወቅቱ ሚስትህ ሳልሆን ትክደኛለች ሳትል ሁለት ሚሊየን ዶላር ሰጠኸኝ ነበር አይደል ? ” አለችው ።
“አዎ” ሲል መለሰላት። “ይኸው ስድስት ሚሊየን ዶላር ሆኖ ጠብቆሀል አለችና” የባንክ ቡኳን እንዲያየው ሰጠችው ።
..ዛሬ ላይ ጉቺ ሜን ከዛች ፍቅሩን ብቻ ሳይሆን የሰጣትንም ገንዘብ በእጥፍ አሳድጋ ከጠበቀችው Keyshia Ka’Oir ጋር ተጋብተው ትዳራቸው በልጅ ደምቆ አብረው ይኖራሉ ።
Wasihune Tesfaye