ፕሬዝዳንት አልሲሲ በይፋ ያለረዘሩትን ድጋፍ ለሶማሊያ እንደሚያደርጉ አስታወቁ። “ሶማሊያ አረብ መሆኗን እና አረቦች በጋራ ሊጠብቋት ይችላሉ” ብለዋል። ግብጽ ከሶማሊያ ጥያቄ ከቀረበላት ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ድጋፍ እንደምታደርግ በይፋ ተናግራለች። ይህ የተሰማው የሶማሊያው መሪ ግብጽ መከተማቸውን ተከትሎ ነው። እሳቸውም አሁን አሁን ንግግራቸው ወደ ሃይማኖት ጉዳይ እየተቀየረ ነው።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ጋር ኢትዮጵያ በሊዝ የናህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። አዲስ አበባ ላይ በተደረው በዚህ ስምምነት እንድተገለጸው በወር ጊዜ ውስጥ ስምምነቱ ተግባራዊ ይሆናል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎ የሚረዝም የባህር ክልል እንዲኖራት ይፈቅዳል። በምትኩ ከኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ባይገለጽም ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንደሚሰጥ ተምሰምቷል።
“ያለፈውን ቁጭት ከወደፊቱ ተስፋ ጋር የሚያቆራኝ” የተባለለት ስምምነት ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ግብጽ፣ ኤርትራና ሶማሌያ በአንድነት ገጥመው ውሉ ተግባራዊ እንዳይሆን እየሰሩ ነው። ኤርትራ በገሃድ ሶማያን መደገፏ ኢትዮጵያዊያንን አስቆጥቷል። ከሚሊዮን የማያንሱ የኤርትራ ተወላጆችን ከዜጎቿ ሳትለይ አቅፋ የያዘቸው ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷን ተከትሎ ኤርትራ ያሳየችውን አቋም የሚደግፉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የኤርትራ ተወላጆች መኖራቸው ጉዳዩን አስተዛዛቢ እንዳደረገው እየተገለጸ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ወደድንም ጠላንም አንድ ህዝብ ነን” ማለታቸው ይታወሳል።
የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ የምትገኘውና “ሉዓላዊነቴ ተደፈረ” የምትለዋ ሶማሊያ በዋናነት ግብጽ በምትመራውና ኤርትራ አባል በሆነችበት የአረብ ሊግ፣ በራሷ በግብጽና ኤርትራ በይፋ ድጋፍ ከማግኘቷ ውጪ ወሳኝ በሚባሉት ተቋማትና አገራት ቀጥተኛ ድጋፍ አላገኘችም። በርካታ አገራት ዝም ሲሉ፣ ተሰሚነት ያላቸው ተቋማት መሪዎች ሶማሊላንድን ሲደግፉም እየተሰማ ነው።
ግብጽ አብዝታና ስራዬ ብላ የያዘቸው ይህ ጉዳይ ከፖቲካ አልፎ ሶማሌያ ከፍለገች የሚፈለገውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀቷን እስከመግለጽ አድርሷታል።
ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ ወታደራዊ አታሺዎች ” የባህር በር ጉዳይ የህልውና ነው። በጋራ የመጠቀም እንጂ ሌላ ፋጎት የለንም። ይህንን ጉዳይ ሊያስቆም የሚችል ሃይል የለም” በሚል ካስታወቀች በሁዋላ ወደ ግብጽ ያመሩት የሶማሌያ መሪ በዝግ ከአቻቸው ጋር መምከራቸውን ሪፖርቶች እያስታወቁ ነው።
ከዚህ የዝግ ውይይት በሁዋላ ነው ግብጽ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ድጋፍ አደርጋለሁ ስትል ቅድሚያውን የያዘችው። በማለዳው ስምምነቱን እንደማትደግፍ አስታውቃ የነበረችው ግብጽ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጉዳዩን ወደ ሃይማኖት እንዲያንጋድዱት እያደረገችም ነው። ሁለቱ መሪዎች ከመከሩ በሁዋላ የጋራ መግለጫ ምስጠታቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል
“አንድን መሬት ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አይሳካም በዚህ የሚስማማም የለም” ሲሉ አልሲሲ ለኢትዮጵያ ያላቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
“ሶማሊያ አረብ ሀገር ናት፣ በአረብ ሊግ ቻርተር መሰረትም አረቦች ከጥቃት እንዲጠብቋት የመጠየቅ እና የመጠበቅ መብትም አላት“ ሲሉም ፕሬዝዳንት አልሲሲ ጉዳዩን አረባዊ ይዘት አሲዘውታል። ይህን ያሉት አልሲሲ ሶማሊያ በአልሸባብ ስትደማ አንድ ወታደር አልላኩም። የአረብ ሊግም እንዲጠብቃት ጥሪ አላቀረቡም።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም “የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት ተቀባይነት የሌለው ነው፣ ከተጠየቅን ደግሞ በሶማሊያ ላይ የሚፈጸም የሉዓላዊነት እና ግዛት አንድነት ጥቃትን ለመመከት ድጋፍ እናደርጋለን” ሲሉም በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ቻይና፣ ህብረት፣አፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ሀገራት ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ድጋፍ እንደሚሰጡ ቢጠቁሙም፣ በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊ ላንድ የጀመሩትን ስራ ወደማገባደዱ መድረሳቸው የጦርነት ስጋት እንደሚፈጥር፣ አልሸባብ በርካታ ሰራዊት ሊያገኝ እንደሚያስችለው ከመግለጽ የዘለለ ነገር እስካሁን አልተሰማም።
ለዚህም ይመስላል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያም አለመግባባታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጥሪ እያቀረቡ ያሉት። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት ካልሰረዘች በቀር ለውይይት አስታውቀዋል።
የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ያሳደሩት ተጸእኖ እያየለ በሄደበት፣ የመሳሪያና የህገወጥ ስደተኞች ወደ አውሮፓ መጉረፍ ያሳሰባቸው አገራት ከኢትዮጵያ ጋር የውስጥ ለውስጥ ስምምነት ማሰራቸውን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ይህን ተከትሎ በዓመት 10 ቢሊዮን ዶላር የሚልቅ ገቢ ከስዊዝ ካናል የምታገኘው ግብጽ ገቢያዋ አርባ በመቶ ማሽቆልቆሉ ተሰምቷል። የሁቱ አምጺያን የመን ላይ ሆነ በሚሰነዘሩት ጥቃት ሳቢያ ቀይ ባህር መታውኩ የሚታወስ ነው። ይህን የሽብር ጥቃት በዝምታ ያለፉት ኤርትራና ግብጽ የኢትዮጵያን የባህር በር ማግኘት፣ የወታደራዊ ሃይል መገንባት በተቃወሙበት ልክ እንኳን ባይሆንም ለአፋቸው እንኳን “ያሳሰበናል” አለማለታቸው ይታወሳል። በዚሁ ቀውስ ምክንያት ግብጽ አርባ በመቶ ገቢዋ ቀንሷል።
የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት ተከትሎ በቀይባህር የንግድ መርከቦች ላይ የሚደረገው ጥቃት ገቢዋን እንድታጣ ያደረጋት ግብጽ የሁቲ አማጺያን እንደምትከላከል እስካሁን አልገለጸችም።
አልአረቢያ እንዳለው ላለፉት አራት ወራት ሲካሄድ የቆየው የሃማስና እስራኤል ጦርነት ተከትሎ በቀይ ባህር የሚመላለሱ የንግድ መርከቦች ቁጥር ቀንሷል። በግብጽ የስዊዝ ካናል በኩል ይስተናገዱ የነበሩ መርከቦች ቀንሰዋል። በዚህ ሳቢያ ግብጽ ገቢዋ ወርዷል።የ
የየመን ሂቲ አማጺያን ከእስራኤልና አሜሪካ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን መርከቦች ደጋግመው ማጥቃታቸው የዓለም ሎጅስቲክስ ኩባንያዎችሌላ አማራጭ እንዲከተሉ አስገድዷቸዋል።
በተጠናቀቀው የነጮቹ ዓመት ግብጽ ከሲዊዝ ካናል 9 .4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። በ2022 ሰባት ቢሊዮን ዶላር አግኝታ እንደነበር ዘገባውን ያሰራጩት የዜና አውታሮች ገልጸዋል።
ሲዊዝ ካናል በዓመት ሃያ አምስት ሺህ መርከቦችን የሚያስተናግድና ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ቶን በላይ ጭነት የሚተላለፍበት ሰርጥ ነው።
ኢትዮጵያ አሁን የባህር ሃይሏን የምትተክለው ወደዚሁ ሰርጥ በሚያስገባውና በሚያስወጣው ባቢልማንደብ ጉሮሮ ላይ እንደሆነ ሮይተርስ ስምምነቱ ይፋ በሆነበት ዕለት መዘገቡ የሚታወስ ነው። ሮይተርስ ይህን ያለው ኢትዮጵያ ምን ያህል ቁልፍ ቦታ ላይ እንደምትቀመጥ ለማሳየት ነው።
አባይን የገደበችው ኢትዮጵያ ግብጽ እርቀት ሄዳ ከፖለቲካ ወሬ ባለፈ ሌላ እጆን ከዘረጋች የኢትዮጵያ መንግስት በአባይ ግድብ ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ሊወስድ እንደሚችል የሚገምቱ፣ ግብጽ ጉዳዩን ከማራገብና እንደለመደችው የአገር ውስጥ ትርምስን ስፖንሰር ከማድረግ ያለፈ ጉዳይ ውስጥ እንደማትገባ ነው።
ኢትዮ12 ዘገባ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring