ዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት ውሉን እንደተወው፣ የሶማሌ ማንግስትም መንግስት በአደባባይ ስምምነቱን ማቆሙን እንዲያውጅ እንደሚያደርግ አስታውቀው እንደነበር ይታወሳል።
ሌሎች አገራት ከሶማሌላንድ ጋር መሰል ስምምነትን ሲያደርጉ ዝምታን የመረጡ፣ የግብጽን፣ የኤርትራንና የሶማሌን የተቀነባበረ ሴራ ተከትለው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የተጀመረውን ዘመቻ የደገፉ “ኢትዮጵያዊያን” መንግስትን ማውገዛቸውና ዜናው ላስደሰታቸው ኢትዮጵያዊያን እጅግ ያስቆጣ ነበር።

ቀደም ሲል አሜሪካ ዋይትሃውስ ውስጥ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ሰብሳቢነት የአባይ ግድብን አስመልክቶ የኢትዮጵያና ግብጽ ባለስልጣናት ሲደራደሩ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ግብጽ ያስቀመተችው ቅድመ ሁኔታና የሚተከሉት የተርባይን መጠን እንዲቀንስ በመስማማት ፈርማችሁ ኑ” ሲሉ ለኢትዮጵያ ልዑካን በስልክ መመሪያ መስጥተታቸውን በተመሳሳይ ሚስጢር ሰማን ያሉት “ኢትዮጵያዊያው” ዜግነት ያላቸው ሚዲያዎችና ለውጭ ሚዲያዎች ተቀጥረው የሚሰሩ አስተጋብተው ነበር።
አብዛኞች እንደሚሉት በኢትዮጵያ ” ማስተባበያ መስራትና ይቀርታ መጠየቅ የሚባል ባህል በኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎችና ባለሙያዎች ዘንዳ በአብዛኛው አይታይም። ሚዲያውን የሚከታተሉም በብዛት ወደ ሁዋላ መለስ ብለው አይጠይቁም” ሲሉ አንዳንድ ባለሙያዎች ስም ባይተሩም በደፈናው ወቀሳ ያሰማሉ። በደቦ ስም ማጠልሸትና መፈረጅ እጅግ ቀላል በሆነበት የሚዲያ ስውድ ውስጥ ሰለባ ላለመሆን በርካቶች ዝምታን የሚመርጡበት የኢትዮጵያ መረጃ ስርጭት ተዓማኒነት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ያመለክታሉ።
ከውጭና ከውስጥ ባሉ ልዩ ፍላጎቶች፣ በብሄር አመለካከትና ቡድንተኛነት እንደተበተበው የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሚዲያ አብዛኛውን መረጃ ማዛባት፣ ከልጅርባቸው ላዘሉት ዓላማ በሚጠቅም መልኩ መረጃን ማንጋደድ፣ እነሱ ከሚፈልጉት አውድ ውጪ የሚነገሩ ምስክርነቶችን አንስቶ ተናጋሪዎችን በደቦ ማጠልሸት ልዩ መለያው እየሆነ የሂደው የኢትዮጵያ ሚዲያ ጥቂት ትጋት ያላቸውን እንደዋጡዋቸው ዘርፉን ያጠኑ ሰሞኑንን አስታውቀዋል። ጥናቱ ወደፊት ዝርዝር እንደሚቀርብበትም አመልክተዋል።
“ተሸጠ” በሚል ዜና የተሰራበትና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ኢላማ አድርጎ የማቆሸሺያ ዘመቻ የተፋፋመበት የአባይ ግድብ ሊጠናቀቅ ወራት ቀርተውት፣ የተባለው ሁሉ ውሸት ሆኖ ኤሌክትሪክ ማምረት ጀምሮ እያዩም የሃሰት መረጃቸውን ማስተባበል ወይም ይቅርታ ጠይቀው ማስተካከል ያልፈለጉ ወገኖች ዛሬም በተመሳሳይ “ከሽፏል” ያሉት የባህር በር ኪራይ ስምምነት ጉዳይ በራሳቸው በሶማሌሎአንድ ባለስልታን በውጭ ሚዲያ ሊጠናቀቅ ሁለት ወር እንደቀራው ሲገለጽ ያሉት ነገር የለም።
ሶማሌላንድ ለኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ይፋ አድርገዋል። ሚኒስትሩ ይህንኑ ያሉት ዶይቼ ቬለ ድምጽ በኩል ነው።
ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ አመልክተዋል። የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ዲፕሎማቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሙሴ ቢአብዲ የተፈራረሙት “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በመጪዎቹ ወራት ወደ ተግባር ይሸጋገራል ተብሎ ታምኗል።
የመግባቢያ ሥምምነቱ ከአራት ወራት በፊት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ሲፈረም ድርድሩ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ አስታውቆ ነበር። በተባለው ፍጥነት ባይኬድም የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ የመግባቢያ ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መታጨታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
“ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነበር” ያሉት ዶክተር ኢሳ ካይድ በረመዳን የጾም ወር ወቅት ሒደቱ ቢቀዛቀዝም በመጪዎቹ ወራት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሥምምነቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የመጨረሻውን ሥምምነት ሊፈራረሙ ዝግጅት ማድረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
“ሁሉም ነገር ሁለቱ ቡድኖች በሥምምነቱ ላይ ለመደራደር ሲገናኙ ይወሰናል” ያሉት ዶክተር ኢሳ “የሕግ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ። በመጪዎቹ ወራት ምን አልባትም በሁለት ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሳዓድ አሊ ሽሬ ሥምምነቱ ተፈርሞ “ዕውቅና ስናገኝ በዓለም አቀፍ መድረክ ድምጽ ስለሚኖረን በፖለቲካ ረገድ ጠቃሚ ነው” ሲሉ ተስፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።
ሶማሌላንድ የምታገኘው ዕውቅና “ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለጉዞ እና በዕድገት በር ስለሚከፍት በኤኮኖሚ ረገድ ጠቃሚ ይሆናል” የሚሉት የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሶማሌላንድ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት እንድትተሳሰር ይረዳታል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።
“ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ መበደር እንችላለን” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳዓድ አሊ “በዕውቅናው ምክንያት እጅግ በርካታ በሮች” ለሶማሌላንድ እንደሚከፈቱ ይጠብቃሉ።
ሥምምነቱ ከተፈረመ ሶማሌላንድ ዕውቅና ስታገኝ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር የምታቋቁምበትን ወደብ በኪራይ ታገኛለች።
ሶማሌላንድ 850 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚረዝመው የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያ ልትከራይ የምትችልባቸውን ሦስት ቦታዎች በአማራጭነት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ አረጋግጠዋል።
“የለየናቸው የተወሰኑ ቦታዎች አሉ። ከኢትዮጵያ አቻዎቻችን ጋር ከተገናኘን በኋላ አንዱ ይመረጣል” ያሉት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተለዩትን ሦስት ቦታዎች ስሞች ከመናገር ተቆጥበዋል።
ኢትዮጵያ የደርግ ሥርዓተ መንግሥት ወድቆ ኤርትራ ነጻነቷን ስታውጅ የፈረሰውን የባሕር ኃይል መልሳ ያቋቋመችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንሳይ እና የቀድሞ የባሕር ኃይል መኮንኖች ድጋፍ የባሕር ኃይሉን በአዋጅ መልሶ ያቋቋመው በ2011 ነበር።