የሀሞት ከረጢት ጉበት የሚያመርተውን ሀሞት የሚይዝ ከጉበት ሥር የሚገኝ አነስተኛ ከረጢት ሲሆን ቅባታማ ምግቦችን እንዲፈጩ ያግዛል።
የሀሞት ጠጠሮች የሀሞት ከረጢት ውስጥ ተፈጥረው የሀሞት ከረጢት ቱቦን እስኪዘጉ እና ሕመም እስኪፈጥሩ ድረስ በቀላሉ የማናቃቸዉ ትንንሽ ጠጣር ነገሮች ናቸው።
- ሁለት ዓይነት ዋና ዋና የሀሞት ጠጠሮች አሉ
- ኮሌስትሮል ጠጠር፦ አረንጓዴ-ቢጫ ቀለም ያለው ነው 80% የሚሆነው የሀሞት ጠጠርም የዚሁ ዓይነት ሲሆን ከሴት ፃታ፣ ውፍረት፣ እርግዝና፣ በፍጥነት ክብደት ከመቀነስ ጋር ይያያዛል።
- ቀለማማ ጠጠር ሲሆን ጥቁር ቀለም ያለው የቀይ ደም ሕዋስ ጉዳት ሲጨምር የሚፈጠር ሲሆን ቡናማ ቀለም ያለው ደግሞ የሀሞት ፍሰት ሲቀንስ የሚፈጠር ነው።
- ለሀሞት ጠጠር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
የቤተሰብ ታሪክ
ብዙ የቅባት መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዝወተር
ውፍረት
እርግዝና
ኮሌስትሮል መጠን መብዛት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደትን በመቀነስ
በስኳር ሕመም
የእድሜ መግፋት - የሀሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
አብዛኞቹ የሀሞት ጠጠሮች በጊዜ ምልክት የማያሳዩ ሲሆን የሚታዩት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸዉ እነርሱም፦
ለረጅም ሰዓት የሚቆይ በላይኛው የሀሞት ከረጢት እና ጀርባችን የሚከሰት ሕመም
ማቅለሽለሽ
ማስመለስ
ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች
የሆድ መነፋት፣ ቃር፣ ማቃጠል እና ጋዝ የመሳሰሉትን
ናቸው። - የሀሞት ጠጠር መፍትሄዎች
አብዛኛውን ጊዜ የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ቀዶ
ጥገና በማድረግ ጠጠሩን ያስወጣሉ።
ጠጠሩን ማሟሟት የሚችሉ መድኃኒቶችንም መውሰድ
ሌላኛው መፍትሄ ነው።
ቅባታማ ምግቦችን መቀነስም ይገባናል።
Via የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
