ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች የተባሉ ሁለት ዓይነት መረጃዎች እየሰጡ ነው። መንግስት ግን ስምምነት መኖሩን ዘርዝሮ እነሱ በሚሉት መልኩ ባለመሆኑ ” ትዕግስት ፍርሃቻ አይደለም” እያለ ነው።
ከትናንት በስቲያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሕዝብ ለሕዝብ መቀራረብን ከመፍተር ጀመሮ ፖለቲካውን በአግባቡ ለማራመድ ይበጃል በሚል የፓርቲ ለፓርቲ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሁለት ውይይት መደረጉን አመልክተዋል።
በመቀለ በተደረገ ውይይት በመርህ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መደረጉን፣ በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ደግሞ አጅንዳ ቀረጻ ላይ ስምምነት መደረሱን ያስታወቁት አቶ ፋራህ፣ በሁሉም አግባብ ህዝብ ወሳኝ በሆነበት አግባብ የይገባኛል ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ አመልክተው፣ ከዚህ ውጭ እየሆነ ያለው ነገር የቀን ጉዳይ ካልሆነ በቀር መንግስት ህግን በማስከበር እንደሚያስተካክለው ተናግረዋል። የአማራንም ሆነ የአፋር ህዝብ ሰላም መንሳት ጨርሶ ተቀባይነት እንደሌለው ሲያስታውቁ ካለፈው ጥፋት መማር እንደሚገባ በማሳሰብ ጭምር ነው።
ሰሞኑን ኮምቦልቻና ደሴ የነበሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በበኩላቸው “በትግራይ ክልል ከሕዝቡ በማፈንገጥ በጠብመንጃ አፈሙዝ ችግራቸውን ለመፍታት የጦረኝነት አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሃይሎች የሰላም ዕድሉን እንዲጠቀሙ ትጥቅ እንዲፈቱ የትግራይ ሕዝብ ተው ሊላቸው ሊመክራቸውም ይገባል። የሰላም ዕድሉን ከመጠቀም ይልቅ የጦርነት መንገድን መርጠው የሚገፉበት ከሆነ ግን መንግስት ሕግ ማስከበር ቀዳሚ ስራው ነውና ሕግ ለማስከበር ይገደዳል ” ብለዋል። ይህን ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል የቀድሞ ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ቀን ቆጥረው ስምምነት መደረጉን ትግራይ ላሉ ሚዲያዎች ያስታወቁት።
በዚህ መሰረት “የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም እንዲተገበርና እንዲፈፀም ስምምነት ተደርሷል ” ብለዋል ጀነራሉ። ይሁን እንጂ ስምምነቱ እንዴትና በማን እንደሚፈጸም፣ ስምምነቱ “የተፈናቀሉ ወገኖች ከክረምት በፊት ወደ ቀድሞ ቅያቸው እንዲመለሱ ዕቅድ ተያዟል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሲወያዩ የተናገሩትን ለመድገም ይሁን በግልጽ አልተብራራም።
ከትግራይ የሚወጡ መግለጫዎችን ቃል በቃል የማያስተባብለው መንግስት፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በቅርቡ ባወታው ሰፊ ማብራሪያ አዘል ማስተንቀቂያና ማሳሰቢያ እንዳለው የይገባኛል ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች በህዝብ ውሳኔ ሰጪነት የሚፈቱ ናቸው። ሌሎቹ ሲንከባለሉ የኖሩትን ችግሮች ጨምሮ ደግሞ በሽግግር ፍትህና በአገር አቀፍ የዕርቅ ኮሚሽኑ አማካይነት እንደሚፈቱ ማስታወቁ ይታወሳል። ከዚ በዘለለ የሚደረግ እንቅስቅሴ እንደማያዋጣ ” ጦርነት ሁላችንንም ያከስራል። ሰላም ሁላችንንም አትራፊ ያደርጋል። እኛ ከአባቶቻችን ስለጦርነት እየሰማን አደግን፤ ይበቃናል። በእኛ ትውልድ እንኳን ሁለትና ሦስት ከባድ ጦርነቶች አለፉ። ለቀጣይ ትውልድ ግን ብልጽግናን እንጂ ቁስልን ማውረስ የለብንም” ሲል ነበር ያስታወቀው።
ጀነራሉ በመግለጫቸው ፥ ” በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ላይ መሰረት ያደረገ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከፌደራል መንግስት ጋር የሁለት ቀን ውይይት በማድረግ የአፈፃፀም ስምምነት ላይ ተደርሷል ” ማለታቸውን የትግራይ ሚዲያዎች አመልክተዋል። ስምምነቱን አላብራሩም። ቀደም ሲል በተገለጸው መሰረት ባፍሪካ ህዝብረትና ዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎች የተገመገመው የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ አሁን የትግራይ ሃላፊዎች የሚያነሱት ጉዳይ ጭራሽ አልተነሳም።
” በውይይቱ የማጠቃለያ ስምምነት መሰረት የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም እንዲተገበርና እንዲፈፀም ስምምነት ተደርሷል ” ሲሉ መናገራቸው የሚዲያዎች ትኩስ አጀንዳ ሆኖ ሲዘዋወር ቢውልም ስምምነቱን አስመልክቶ መንግስት በቃል፣ በስብሰባ፣ ለትግራይ ህዝብ ወኪሎች፣ እንዲሁም በጋራ ደህንነትቱ መግለጫ ካለው ውጭ የተደረገ ስምምነት ስለመኖሩ ይህ እስከተሳፈ ድረስ ከትግራይ ሃይሎችም ሆነ ከሚደግፏቸው አካላት የተባለ ነገር የለም።
” ትጥቅ ማን ይፈታል ? ፣ እንዴት ይፈታል ? የትኞቹ አስተዳደሮችስ ይፈርሳሉ ? እንዴት ያሉ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ ? በሚሉ ነጥቦች ውይይት ተካሂዶ ዝርዝር እቅድ ወጥቶሎታል ” በሚል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል። ትጥቅ ማስፈታትን በተመለከተ ” በአንድ አገር አንድ መከላከያ ብቻ ስለሚኖርና ህገ መንግስት ስለሚያዝ የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ” መንግስት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ አጠንክሮ መግለጫ መስተቱን ለማተናከር ይሁን ሌላ የጀነራሉ መግለጫ አያብራራም።
ይልቁኑም የእቅዱ አፈፃፀም በአፍሪካ ህብረት የክትትልና ቁጥጥር ቡድን እንዲመራና እንዲተገበር ስምምነት መኖሩን ማመልከታቸው የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ የክትትልና ቁጥትር ቡድኑ ያስቀመተውን ቀነ ገደብ በይፋ አመልክተዋል።
” በትግራይ አመራር መካከል በፕሪቶሪያ የውል ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ሰላም ፈላጊና ጦርነት ፈላጊ አለ በሚል እየተፈጠረ ያለው ትርክት ስህተት ነው ” ያሉት ጄነራሉ ” ትርክቱ ስህተት መሆኑን ለፌደራል መንግስት ገለፃ ሰጥተናል ” ብለዋል። እሳቸው ይህን ያሉት ምን አቶ ተመስገን በግልጽ “ጦርነት የሚጎስሙ ክፍሎች አሉ” ሲሉ ለተናገሩት የተሰጠ ምላሽ ሆኖ ተወስዷል።
ጀነራሉ “ልዩነት የለም” ይበሉ እንጂ አቶ ጌታቸው ረዳ በግልጽ በተደጋጋሚ ለክልሉ መንግስት የማይታዘዙ መኖራቸውን፣ የክልሉ መንግስት ሳያውቀው የሚከናወኑ ተግባራት አሉ” ሲሉ አፈንጋጮች መፈጠራቸውን በገሃድ መናገራቸው፣ በትግራይ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳ የሚፈልጉ ሃይሎች እንዳሉ፣ እነዚህ ሃይሎች እንደሚፈረጁ በተከታታይ መረጃ እንደሚሰጥ የሚታወቅ ነው።
በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ ውል ለመተግበር እስከ ታች የአስተዳደር መዋቅር ድረስ መግባባት ተደርሶ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መመቻቸቱን አመልክተው “የፌደራል መንግስትም የስምምነቱ ትግበራ እስከ ታች ድረስ እንዲያወርደው እንጠብቃለን ” ሲሉ ጀነራሉ ተናግረዋል። ከመንግስት ወገን ለጊዜው የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ ህዝብ ከተረጋጋ በሁዋላ በቀጣይ በራሱ ምርጫ አስተዳዳሪዎቹን እንዲሰይም፣ ከዛም በድምጹ የፍላጎቱን እንዲወስን ታምኖበት ወደ ስራ መግባቱን በቴሌቪዥን ውይይት ወቅት፣ በመግለጫና በቃለ ምልልስ በግሃድ ከሚያስታውቀውና ለተግባራዊነቱ ከመስራት በዘለለ ምን እንደሚጠበቅበት ለጊዜው ግልጽ እንዳልሆነላቸው አስተያየት የጠየቅናቸው ባለስልጣን ነግረውናል።
” የፕሪቶሪያው ውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ከማንኛውም አይነት ግጭት በፀዳ መልኩ ተፈፃሚ ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም ፤ አሁን መሬት ላይ ካለው ሁኔታ በመነሳት እንዳችም ለግጭት የሚጋብዝ ሁኔታ የለም ” በማለት ሌተንል ጀነራል ታደሰ በመግለጫቸው መናገራቸው ተወስቷል።
ከመንግስት አቅጣጫ እንደሚሰማው ከሆነ ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎችን ያፈናቀለው የትግራይ ሃይሎች ዳግም ወረራና ትምህርት ቤቶችን የጦር ካምፕ አድርጎ መዝለቅ ስለማይቻል በአስቸኳይ ስምምነቱን አክብረው ታታቂዎቻቸውን እንዲያስወጡ ቀነ ገደብ ተቀምጧል። በተመሳሳይ በዓለም አቀፍ ደረጃና በአፍሪካ ይህን ጉዳይ ለሚከታተሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ለሚቀመጡ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በተደጋጋሚ መንግስት ፈቅዶ የትግራይ ሃይሎች ህዝብ እያፈናቀሉ የፈለጉትን አካባቢዎች እንዲይዙ ተደርጎ የሚሰሩ ዜናዎች እንድምታቸው ሌላ በመሆኑ መንግስት ዜናው ለሚመከታቸው የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አካባቢ አመራሮችን በቂ ግንዛቤ እንዳሲያዘ፣ ምንም የሚፈጠር ነገር ባለመኖሩ ስራቸውን ተረጋግተው እንዲቀጥሉ፣ የጸጥታ ሃይሉም በበቂ ዝግትና ተጠንቀቅ እንዲቅመጥ መደረጉ ተሰምቷል።
በተለይም በሱዳን ጠረፍና አቅጣጫ የሻዕቢያ ሃይልም ዝግጅት ማድረጉ ከተሰማ ጊዜ አንስቶ በዛው አቅጣጫ የኤርትራ መገናኛ የሆነው መንገድ መዘጋቱ የመንግስትን ዝግጁነት የሚያሳይ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring