የዓለማችን ግዙፉ ቦይንግ የአውሮፕላን ማመረቻ ኩባንያ የአፍሪካ አገራት ዋና ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ። ዜናው ታላቅ ዝና ላለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ አጋጣሚዎችን ይዞ እንደሚመጣና ዕድሉም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅንነትና ዝና የተነሳ የተገኘ እንደሆነ ተመልክቷል። ዜናው ትልቅ ቢሆንም ከአየር መንገድ አጥር ክልል ውጭ እሳት ተነሳ በሚል ሲያራግቡ የነበሩ ሚዲያዎች ዝም ብለውታል።
ኩባንያው ይህን ይፋ ያደረገው በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ ከፈረንጆቹ ግንቦት ሃያ አንድ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የአፍሪካ የአቪዬሽን ጉባዔ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ በተስተፈችበት በዚሁ ጉበዔ ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዱን ይፋ ማድረጉን በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ተመልክቷል።
አፍሪካ ዲ ደብሊው እንደዘገበው ቦይንግ ኩባንያ ፥ የአፍሪካውያን የመጓጓዣ አገልግሎት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከ1,000 በላይ አዳዲስ ጄት አውሮፕላኖችን እንደሚፈልጉ ግምቱን አስቀምጧል። ስሌት በቀጣይ ገበያውን ያሰላበት ነው።
ቦይንግ በድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ” የአፍሪካ ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና እያደገ የመጣው ወጣት የሰው ሃይል በሚቀጥሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ በአየር ትራፊክ እና በአውሮፕላን ፍላጎት ላይ ከፍተኛ እድገት ያመጣል” ሲል ጽፏል።
ቦይንግ የአፍሪካ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ እንደሚከፍት ማስታወቁ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል እንደሆነ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ መሪነትን፣ በአለም ኩሩ ተወዳዳሪ አየር መንገድ ስላላት ከቦይንግ አዲስ አበባ መከፈት ጋር ተዳምሮ ብዙ መልካም አጋጣሚዎች እንደሚያስገኝ ከወዲሁ እየተገለጸ ነው። በሂደትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኖሎጂ የሚጋራበት አገባብም እንደሚኖር አስተያየት ተሰጥቷል።
ይህም ደግሞ ኬንያ ወይም ደቡብ አፍሪካ የቦይንግ የማስፋፊያ ቦታዎች ይሆናሉ የሚለውን ግምት ውድቅ አድርጓል።
እ.ኤ.አ. በ2023 ላይ ኢትዮጵያ እና ቦይንግ አንዳንድ የአውሮፕላን ክፍሎችን በኢትዮጵያ ለማምረት የጋራ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚህ ላይ ኩባንያው አዲስ አበባ ላይ የሚከፍተው ጽህፈት ቤቱ ሲታከልበት የቴክኖሎጂ ልውውጡን ወደ አንድ ከፍተኛ እርከን እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
ቦይንግ በድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ” የአፍሪካ ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና እያደገ የመጣው ወጣት የሰው ሃይል በሚቀጥሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ በአየር ትራፊክ እና በአውሮፕላን ፍላጎት ላይ ከፍተኛ እድገት ያመጣል ” ብሏል።
ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካውያን የመጓጓዣ አገልግሎት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከ1,000 በላይ አዳዲስ ጄት አውሮፕላኖችን እንደሚፈልጉ ስሌቱን አኑሯል። ከእነዚህ ውስጥ 80% ነባር አውሮፕላኖችን ለማስፋት ያለመ እንደሆነ የDW ዘገባ ያስረዳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው መጋቢት ወር በአፍሪካ የመጀመሪያ ሞዴል የሆኑትን ስምንት ቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
ባሳለፍነው ሕዳር ወር ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ትልቅ የተባለለትን 67 ቦይንግ ጀት አውሮፕላኖች የግዢ ሥምምነት መፈረሙም የሚታወስ ነው፡፡
ይህን ታላቅ ዜና አየር መንገዱን ለማጠልሸት ዘመቻ ከፍተው በመናበብ ለሚሰሩት ሚዲያዎች ባይመችም ተጨማሪ ዜና ተሰምቷል። በ110ሚሊየን ዶላር ኢትዮጵያ የአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት እንደምትጀምር ተመልክቷል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ናሽናል ከተሰኘ ሀገር በቀል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር የአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ ነው ዜናው ይፋ የሆነው።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በስምምነቱ ወቅት ስምምነቱ ለኢትዮጵያን ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም በኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ እና ግብአቶች ማምረት ውስጥ ኢትዮጵያ ያላትን ተሳትፎ ከፍ እንደሚያደርግ ማሳያ ጠቅሰው ገልጸዋል።

የተፈረመው የ110 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን አካላትንና መለዋዎጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚያስችለው እንደሆነ ተነግሯል።
ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሙሉ ለሙሉ ወደ ተግባር ሲገባ 1 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም ሀገሪቱ ለአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎች የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀርና እቃዎቹን ወደ ሌሎች ሀገራት ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።