” ግጭት የኢትዮጵያውያንን ስቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም ” ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አስታወቁ። በኢትዮጵያ ጠብመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲያመሩ ጥሪ ሲያቀርቡ መንግስትም በተመሳሳይ ሊወስድ የሚገባውን “ምክር፡ ሲሉ የጠሩትን ዘርዝረዋል።
አምባሳደሩ በንግግራቸው አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ያላትን ፖሊሲ ያመልካእቱ ሲሆን በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር እንዳለባቸው ገልጸዋል።
“የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ አሳዛኝ እንደሆነ ጠቁመዋል። የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች እንደሚፈጸም አምባሳደሩ ስም ጠቅሰው ተናግረዋል።
በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊከበሩ እንደሚገባ ያሳሰቡት የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ “ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው” ሲሉ ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው” ሲሉ ጥንቃቄ እንደሚያሻው ገልጸዋል።
የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች “እራሳቸውን ፋኖ ” ብለው ከጠሯቸው በሁዋ እነዚሁ ብድኖች ቡድኖች ለንግግርና ድርድር የቀረበላቸውን ጥያቄ አንቀበልም ማለታቸው “እራሳቸውን ይጎዳቸዋል” ብለዋል። በአማራ ክልል ያሉ ጥያቄዎች መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ እንዳለባቸው አመልክተዋል።
በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች እንደሚሆኑ አመልክተዋል። ትህግም በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ እንደሚገባውም ጠቅሰዋል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት እንዲያከብሩም መክረዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
“ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች” ካሉ በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ይህን ካሉ ባሁዋላ ንግግራቸውን ሲቋጩ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። አያይዘውም ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን እንዲታቀቡ አሳስበዋል።
የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ እንደሚያደርጉ አስታውሰው፣ ህዝብ የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል። ለዚህም ሲባል የተግባር ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
“ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል” ሲሉ ለኮሚሽኑ እውቅና ሰጥተው ጥሪ አቅርበዋል።
እሳቸው ከፌደራል ፖሊስ ጋር፣ አምባሳደር ሃመር ከኦነግና ኦፌኮ መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ንግግር ያደረጉት አምባሳደሩ ሁሉምን ወደ ውይይት እንዲያመሩ የተናገሩት ዶክተር መረራ በአሜሪካን ኤምባሲ ከሃመር ጋር ስለተወያዩት ለቢቢሲ ከተናገሩት ጋር የተለየ ሆኗል።
የአምባሳደሩ ንግግር በአብዣኛው አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ያላትን የተሳሳተና ግልጽ የሆነ ጥላቻ የቀየረ ቢመስልም ” በእዚህ ደረጃ ለህዝብ ከተጨነቁ ትህነግ አፋርና አማራ ክልልን ወሮ ሲዘርፍ፣ ሲያወድምና ንጽሃን ላይ ግፍ ሲፈጽም አሜሪካ የት ነበረች? አሁን የተሰማው አዘኔታ ከየት መጣ? ምክንያቱስ ምንድን ነው? ከጀርባው ምን አዝሏል?” በሚል ጥያቄ ያነሱ “ምን አስበው ነው” በሚል የአምባሳደሩን ንግግር በጥንቃቄ መፈተሽ እንደሚገባው አሳስበዋል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring