በበሄሊኮፕተር መከስከስ ህይወታቸው ያለፈው ኢብራሂም ራይሲንን ጨምሮ ስ፣ንት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ፕሬዚዳንት ኢብራሂም እሁድ እለት ያደረጉት የሀገር ውስጥ በረራ የህይወታቸው ማብቂያ ሆነ።
ቀደም ብሎ እንድተገለጸው ሀሰን ሮሃኒን በመተካት ከነሐሴ 2021 ጀምሮ የሀገሪቱ ስምንተኛው ፕሬዝደንት የሆኑት ራይሲ የተሳፈሩባት ሄሊኮፕተር አዘርባጃን ድንበር አቅራቢያ ከተራራ ጋር ተጋጭታ መከስከሷን የኢራን ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። በዚህ አደጋ ራይሲን ጨምሮ ኢራን ስምንት ዲፕሎማቶቿን ተነጥቃለች።
የፕሬዚዳንቱን ህልፈት ተከትሎ ወዲያውኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑትን ሞሀመድ ምክበርን ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አድርገው መሰየማቸው ተገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ ወደ አገሪቱ ሰሜን ምዕራብ የኢራን አካባቢ (የአዘርባጃን ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ) ሟቹ ፕሬዚዳንት ወደ አዛርባጃን ምዕራባዊ አቅጣጫ የአገራቸው ድንበር ያመሩት ቂዝ ቃላሲ የተሰኘውን ግድብ ለማስመረቅ ሲሆን ግድቡ የተሰራው ሁለቱ አገራት በሚጋሩኡት የአራስ ወንዝ ላይ የተገነባ ኃይል ማመንጫ ነው።
የኢራን ፕሬዚዳንት በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት ኢልሐም አሊይቭ ጋር ተገናኝተዋል። ስነ ስርዓቱ ተጠናቆ ጉዟቸውን በታብሪዝ ከተማ ሁለት የነዳጅ ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ ሲያቀኑ በወዳጅነት መሰናባበታቸውን መገናኛዎች አመልክተዋል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሲን አሚር አብዶላሂን፣ የምሥራቅ አዘርባጃን ግዛት አገረ ገዢ ማሌክ ራሕማቲ፣ የታብሪዝ ከተማ የአርብ ፀሎት መሪ አያቶላ መሐመድ ዓሊ ሐሺም እንዲሁም በምሥራቅ አዘርባጃን ከፍተኛ የሺዓ እምነት መሪው ዓሊ ካሃሜኒ ተወካይ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ እንደነበሩ ታውቋል። በተጨማሪም የበረራ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩትና የፕሬዝዳንቱ የግል ጠባቂዎች እንደነበሩ የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገባ ያስረዳል።
ስለ ሄሊኮፕተሩ ምን እናውቃለን? ሲል ቢቢሲ በብሔራዊ ቴሌቭዢን ጣቢያ የተላለፈው መረጃ ጠቅሶ ሄሊኮፕተሩ ቤል 212 መሆኑን ጠቁሟል። ይህም ለካናዳ መከላከያ ሠራዊት በአሜሪካ ተቋም እአአ በ1960ዎቹ የተሠራ ሞዴል ነው።
የኢራን የባሕር ኃይል እና አየር ኃይል 10 ተመሳሳይ ሞዴል ያላቸው ሄሊኮፕተሮች እንዳሏቸው ‘ፍላይትግሎባል’ በ2024 የአየር ኃይሎች ዝርዝሩ ውስጥ ገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ ምን ያህሉን የኢራን መንግሥት እንደሚያንቀሳቅስ ግልጽ አይደለም።
በኢራን ብሔራዊ ቴሌቭዢን ጣቢያ መረጃ መሠረት፣ ፕሬዝዳንቱን ይዞ የነበረው ሄሊኮፕተር ስድስት ተሳፋሪዎች እና ሁለት የበረራ ሠራተኞችን ማጓጓዝ ይችላል። ፍላይት ሴፍቲ ፋውንዴሸን’ የተባለው ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በኢራን ቤል 212 ሄሊኮፕተር ለመጨረሻ ጊዜ አደጋ የደረሰው በአውሮፓውያኑ 2018 ነበር።
በማይመች የአየር ሁኔታና ዘናብ ሳቢያ እንደተከሰከሰ የተነገረለት ሄሊኮፕተር የአደጋ መንስኤ እንደሚጣራ ከመገለጹ ውጭ ለጊዜው የተሰጠ አዲስ መረጃ የለም።

ምስል – አል አይን ካዘጋጀው አጭር ታሪክ መግለጫ ላይ የተወሰደ
በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያንን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላልፏል።
መግለጫው ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ አስታውሶ፣ አደጋውን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኀዘን መግለጫቸውን ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ አስተላልፈዋል።
በኀዘን በመግለጫው ሕይወታቸው ላለፈው ባለሥልጣናት ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።