የኬንያ መንግስት በህግ ሊያጸናው ያሰበውን አዳዲስ የቀረጥ ህጎች ተከትሎ ህዝብ አደባብይ ወጥቶ ተቃውሞ ማሰማት መጀመሩን የዓለም ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። የኢትዮጵያ አንዳንድ “አንቂ ነን” የሚሉና በስም ለማይታወቁ ድርጅቶች የሚሰሩ “የኬንያ ጀግኖች” እያሉ ከኢትዮጵያ ጋር አነሳጽረው ህዝብ አመጽ እንዲያደርግ እየቀሰቀሱበት ያለው የኬንያ አመስ አሁን ላይ የአገሪቱ መከላከያ ሃይል ጣልቃ ገብቶ እንዲያቆመው መደረጉ በሰበር ዜና ተሰምቷል።
ዳቦን ያካተተው አዲሱ ቀረጥ፣ በምግብ ዘይት፣ በሴቶች የንጽህና መጠበቂያ፣ የሞባይል ስልኮች፣ ኮምፒውተሮች፣ ተሽከርካሪዎችና በሌሎች ተመሳሳይ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ቀረጥ ጭማሪ እንደሚያደርግ የሚደነግገው ረቂቅ ህግ ” ኑሯችንን ያስወድድብናል ” በሚል ቅሬታ የገባቸው ኬንያውያን ወጣቶች ከአገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ቁጥራቸውም እጅግ ከፍተኛ ነበር።
የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት፣ ሙስናና ድህነት ያጎሳቆላቸው ኬንያውያን፣ በቲክቶክ ጀምረውት ያፋፋሙት ተቃውሞ ከጋለ ብሁዋላ መንግስት ለውጥ እንደሚያደርግ አስታውቆ ነበር። የዳቦ 16 በመቶ ቀረጥን ጨምሮ፣ የምግብ ዘይት፣ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት እና በተሽከርካሪዎች ላይ ሊጣሉ የነበሩ ቀረጦች ለማንሳት መንግስት ቢገደድም ነገሩ የሚበርድ አልሆነም።
የኬንያ ፓርላማ እንዳጸደቀው በተነገረለት ህግ ሳቢያ ሰኞ ዕለት አደባባይ በወጡ ሰልፈኞችና ፖሊስ ክፉኛ ተጋጭተዋል። በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃውሞውን በሚመለተ የወጡ የቪዲዮ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝርፊያ፣ ንብረት ማውደምና የመንግስት ተቋማትን ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስራ ሁለት ሰዎች በፖሊስ መገደላቸው ተዘግቧል። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም እየተሰማ ነው። የቆሰሉም አሉ።
ተቃዋሚዎቹ ወጣቶች ፓርላማው በመሄድ የምክር ቤቱን አጥር ጥሰው በመግባት ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ሲዘልቁ ታይተዋል። ፖሊስም በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት እና አስቀሽ ጭስ ተጠቅሟል። ለጊዜው ቁጥራቸው ይፋ ያልሆነ ሰልፈኞች በጥይትተመተዋል።ሰዎች ሮይተርስ የዜና ወኪል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ጠቅሶ አስር የሚልቁ ሞተዋል ሲል ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ ፓርላማውን ጥስወ ሲገቡ፣ የፓርላማ አባላት ከምክር ቤቱ ምድር ቤት ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሯሯጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ሆኗል። ፓርላማውን ሰብረው የገቡ አንድ የፓርላማ ክፍል በእሳት አጋይተዋል። ፓርላማው ውስጥ እሳት ሲቀጣጠል በምስል አስደግፈው የተለያዩ ሚዲያዎች አሳይተዋል። ይህ ከመሆኑ ከሰዓታት በፊት የፓርላማ አባላቱ አነጋጋሪውን ህግ አጽድቀው ነበር።
የመንግሥት ቀደም ብሎ የተፈቀደ ሰልፍ እንደሌለ ቢያስታውቅም፣ወደ ቤተመንግስትና ፓርላማ እንዳያመሩ ቢያስጠነቅቅም ፓርላማ በኃይል ጥሰው የገቡት ወጣቶች ፓርላማውን ጥሰው መግባትና ማቃጠል ብቻ ሳይሆን በካፍቴሪያ ውስጥ ያለ ምግብ እየተሻሙ ሲበሉ ታይተዋል።
ከተሰራጩት የቪዲዮ መረጃዎች መካከል አጋጣሚውን በመጠቀም ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ በርካታ መሆናቸውንና የመንግስትን ብቻ ሳይሆን የግል ንግድ ቤቶችንም የዘረፉ መኖራቸው ነው።

የቀረጥ ተቃውሞን ተስታኮ በኬንያ የነገሰው ዝርፊያና ወንጀል መስፋፋቱን ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ጦር የጸጥታና የህግ ማስከበሩን፣ እንዲሁም የዜጎችን ደህንነት እንዲያስተብቅ ትዕዛዝ ተላልፎለታል። የአገሪቱ የመንግስት መግናኛዎች በሰበር ዜና ያሰራጩት ዜና እንዳለው ፕሬዚዳንት ሩቶ ይህንኑ ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለህዝብ ባደረጉት ንግግራቸው የተቃውሞ ስም የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ለህግ እንደሚቀርቡ ይፋ አድርገዋል። አያይዘውም ድርጊቱን ” ክህደት” ብለውታል።
ሩቶ ታቃውሞውን እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር እንደሆነ ገልጸው ፤ የጸጥታ ኃይሎች የኬንያውያንን ደህንነት እንዲያስጠብቁ መመሪያ እንደሰጡ ሲያስታውቁ፣ ስልተፈጸሙ ወንጀሎች፣ ፓርላማው ተሰብሮ ስለተገባበት አግባብ ሁሉ ምርመራ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
“ህገ መንግስታዊ መብታቸውን በአግባቡ ተጠቅመው የተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርጉትን የወንጀል ድርጊትና ወንጀለኞችን ከሚፈጸሙት መለየት ይገባል” ሲሉ የተደመጡት ሩቶ ውንጀለኞች እንደሚጠየቁ አስረግተው ተናግረዋል።

ፕ/ት ሩቶ “ አደገኛ ወንጀለኞች “ ሲሉ የጠሯቸው አካላት ሊፈጸሙት የሚችልን ማንኛውም ሙከራ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር የደህንነት አካላት እርምጃ እንዲወስዱ እንዳዘዙ ገልጸዋል። ለህዝቡ “ ዛሬ ማታ ተኙ” ብለዋል። የአገሪቱ መከላከያ ሃይል ህግ እንዲያስከብር በመታዘዙ የዜጎችን ንብረትና ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚጠብቅ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።