በአዲስ አበባ ባለድርሻ አካላት ዛሬ አጀንዳዎቻቸውን ለይተው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ የሚገኘው የምክክር ምዕራፍ ለስድስተኛ ቀን ዛሬም ቀጥሎ መዋሉንም አመልክቷል።
አምስቱ የምክክር ባለድርሻ በአራተኛና አምስተኛ ቀን በነበረው መርሃ-ግብር የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን በቡድን ሆነው ሲያጠናቅሩና ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡
ባለድርሻ አካላቱ ያጠናቀሯቸውን እና ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በቃለ-ጉባኤ በማዘጋጀት ለአጠቃላይ መድረኩ የሚያቀርቡላቸውን ተወካይ ግለሰቦችንም መርጠዋል፡፡
ቀጥሎ በተካሄደው መርሃ-ግብር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቡድን ሆነው ተስማምተው ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ለጋራ መድረኩ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በኋላ በሚኖረው መርሃ-ግብር የየባለድርሻ አካላቱ ወኪሎች ከሞደሬተሮች ጋር በመሆን የሁሉንም አጀንዳዎች በጋራ ሆነው አስቸኳይነትን፣ አስፈላጊነትን እና ወካይነትን ከግምት በማስገባት በየፈርጁ እንደሚያደራጁ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዛሬው ዕለትም በየፈርጁ የተደራጁት አጀንዳዎች የፊንፊኔ ከተማ አጀንዳ ሆነው ለምልዓተ ጉባኤው ከቀረቡ በኋላ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተገኙበት የምክክር መድረክ እንደሚካሔድ ተገልጿል።ከስር ኮሚሽኑ በረገጹ ሰተድስታፊዎቹ ያሰፈረው ነው።
ለመሆኑ የምክክሩ ባለድርሻዎች የትኞቹን አካላት ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ?
• ከየወረዳው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች
2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
• በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች
3. የተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)
• የሃይማኖት ተቋማት፣ ሲቪል ማህበራት፣ የአሰሪዎች ማህበራት፣ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ የመምህራን ማህበር፣ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት፣ የሙያ ማህበራት፣ የቀድሞው ሰራዊት ማህበር (ተቀናሽ ሰራዊት ማህበር)፣ የጋዜጠኞች ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት)፣ የንግድ ማህበራት ምክር ቤት እና የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት
4. የመንግስት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን
5. ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች
• በተለያዩ ዘርፎች በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅዕኖን መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች
ምንጭ፡- ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን