” በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ” የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል። በአዋጁ ከብርበራ ጋር በተያያዘ በረቂቁ ላይ በክፍል አምስት ሰፍሯል። “ስለ ምርመራ ” በሚል ንዑስ ርዕስ የተመከተው ዝርዝር ጉዳይ የሚከተሉትን ጉዳዮች ይዟል።
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት የዳኝነት_አካላት ለተወሰነ ጊዜ፦
- በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ ክትትል_ለማድረግ፤
- የኮምፒዉተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችንና ሰርቨሮችን ለመለየት፣
- መገናኛዎችን በክትትል ሥር ለማዋል ወይም ለመጥለፍ፣
- ድርጊቶችን፣ ባህሪዎችንና ንግግሮችን በድምፅ እና በምስል ለመቅረፅ እና ፎቶግራፍ_ለማንሳት፣
- የደብዳቤ ልዉዉጦችን ለመጥለፍ እና ለመያዝ፤
- በሽፋን ሥር ስለሚደረግ ምርመራና በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍ ለመጠቀም፣የሚያስችል ትዕዛዝ ለወንጀልመርማሪ አካላት መስጠት ይችላሉ።
- የመርማሪ አካል የተደነገጉትን የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለዉ ፍርድ ቤት አስተማማኝ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥ #ሲፈቅድ_ብቻ ነዉ።
- መርማሪው አካል #አስቸኳይሁኔታካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል፡፡
- መርማሪ አካል #ያለፍርድቤትትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ የጥያቄውን አግባብነት መርምሮ ለመቀበል ወይም ደግሞ ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡
- ፍርድ ቤት የምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበስብ ለመርማሪ አካል ፈቃድ ሲሰጥ፡-
ሀ. ማስረጃ ስለሚሰበሰብበት ዘዴ እና ስለሚከናወንበት አግባብ፤
ለ. የሚከናወንበት ጊዜ በተመለከተ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡ - የማስረጃ ማሰባሰቢያው ዘዴ ጠለፋ ወይም ክትትል እንደሆነ #ጠለፋዉ ወይም #ክትትሉ የሚደረግበትን የስልክ ፣ የፋክስ ፣ የሬዲዮ ፣ የኢንተርኔት ፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የፓስታና የመሳሰሉትን የግንኙነት መስመሮች አድራሻ ወይም መለያ መጥቀስ አለበት፡፡
- ማንኛውም የመገናኛ አገልግሎት አቅራቢ በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ ሲጠየቅ ጠለፋው በፍ/ቤት ወይም በአቃቤ ሕግ የበላይ ሃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት፡፡
- በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሕግ አስከባሪ አካላት በጠለፋ የተገኘ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ #በጠለፋበተገኘበትመልክ_በቀጥታ ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም፡፡