ከ23 269 የምርጫ ጣቢያዎች በ23 292 የድምጽ አሰጣጡ ተጠናቋል። 2024 National and Provincial Elections ድረ ገጽ ይፋ እንዳደረገው ምርጫው 99 በመቶ ተጠናቋል። ኤኤንሲ 41.20 በመቶ፣ ዲ ኤ 21. 77 በመቶ፣ ኤምኬ 14.59 በመቶ ድምጽ አስመዝግበዋል። በዚሁ ዳታ መሰረት ኤኤንሲ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ብቻውን የተቆጣጠረውን የአብላጫ ድምጽ ዘንድሮ ከስሯል። “ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ያላቀቀው ይህ ታሪካዊ ፓርቲ አብላጫ ድምጽ ተነፈገ” የሚለው ዜና ዓለም ላይ እየተሰራጨ ነው።

ከሶስት አስርት ዓመታት በሁዋላ ኤኤንሲ በደቡዑብ አፍሪካ ምርጫ ቁልቁል ወርዷል። እስካሁን በሚወጡት መረጃዎች አብላጫ ድምጽ ማግኘት አልቻለም። በምርጫዉ 50 በመቶ በታች ዉጤትን እንደሚያገኝ ቀደሞ ተተንብዮ ነበር። ትንቢቱ ገሃድ ሆኖ ዛሬ ፓርቲው ጥምር መንግስት ለማቋቋም ተገዷል።
እየወጡ ባሉ መውረጃዎች መሰረት የመጀመርያ ዉጤቶች መሰረት ምናልባትም የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚያመቻቹ ንግግሮች መጀመራቸው እየተሰማ ነው። ሌብነት እንዳነቀዘው የተነገረለት ANC በደቡብ አፍሪካ ወጣቶች ድምጽ ተነፍጓል። ይህ ለደቡብ አፍሪካዊያን አሞኮ ሆኖ የኖረ ፓርቲ በሙስና መንቀዙ፣ ስራ አጥነት አንድ ላይ ተዳምረው የቀደመውን የምርጫ ውጤት እንዳያስመዘግብ ምክንያት እንደሆነው በስፋት የሚወጡ ሪፖርቶች አስቀድመው ሲገልጹ ነበር። እንደተባለውም ሆኗል።
ቢቢሲ አማርኛ የፓርቲውን ውድቀት አስመልክቶ ያሰባሰበውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው ምንም እንኳን ፓርቲው ለዘመናት በደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ የነጻነት ተምሳሌት ቢሆንም፣። ደቡብ አፍሪካውያን በግፍ የተነጠቁትን የሰውነት ክብር ቢያስመልስም፣ በዚሁ ተግባሩ ንቅናቄው በብዙዎች ልብ ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራ ቢኖረውም፣ ከሦስት አስርት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በኋላ ይሄ ሁሉ ተቀያይሯል። ፓርቲው በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና እና የመጥፎ አስተዳደር ተምሳሌት ሆኗል። ይህም በምርጫው ላይ ዋጋ አስከፍሎታል።
በዚህም የተነሳ ግንቦት 21/ 2016 ዓ.ም. በነበረው ምርጫ ወጣቶች በምርጫ ካርዳቸው ፓርቲውን ቀጥተውታል። ወጣቶቹ ከዚህ በፊት ከነበሩ ምርጫዎች በተለየ መልኩ በከፍተኛ ቁጥር ወጥተው ነው ድምጽ የሰጡት።
“ሙስና ሰልችቷቸዋል፣ በሥራ አጥነት ክፉኛ ተጎድተዋል። ስለዚህ የኤኤንሲ ተጻራሪ ሆኑ” ሲሉ ዲሞክራሲ ወርክስ ፋውንዴሽን የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሊቀ መንበር ዊልያም ጉመዴ ያስረዳሉ። በርካታ ወጣቶች ኤኤንሲን ተቃውመው መነሳታቸው የትውልድ መከፋፈልንም ያሳየ ሆኖ ተመዝግቧል። ምርጫው ባለፈ ታሪክ መኖር እንደማይቻል አሳይቷል።
ትግሉን የሚያውቁት የወጣቶቹ ወላጆች ከአፓርታይድ ሰንሰለት ነጻ ያወጣቸው የነጻነት ንቅናቄ በመሆኑ አሁንም ለኤኤንሲ ታማኝ ናቸው። ሆኖም የኤኤንሲ ድጋፍ በዕድሜ በገፉ መራጮችም ሆነ በገጠሩ አካባቢ ጭምር ቀንሷል።
“ኤኤንሲ በትልልቅ ከተሞች ድጋፉን ያጣው ከረጅም ጊዜ በፊት ነው። አሁን ደግሞ በገጠሮችም ቢሆን ድጋፉን እያጣ ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ጉመዴ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኤኤንሲ በአውሮፓውያኑ 2004 በተደረገው ምርጫ 70 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ከፍተኛ ድል ያስመዝግቧል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉ ምርጫዎች የ3 በመቶ ወይም 4 በመቶ ድጋፍ እያጣ መጥቷል። በዚህ ምርጫ ደግሞ ፓርቲው በአስርት ዓመታት አይቶት የማያውቀው ውድቀት አጋጥሞታል። አብላጫ ድምጽ ማግኘት ተስኖት ለጥምር መንግስት ምስረታ የሌሎችንም ፈቃድ እየጠበቀ ነው።
በፕሬዝዳንት ሲረል ራማፎሳ የሚመራው የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ANC ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ሳያጣ አይቀርም፤ ጥምር መንግሥት መመስረት ይኖርበታል፤ የሚል የሕዝብ አስተያየቶች የተሰሙበት ምርጫ፤ የድምፅ ቆጠራዉ እየተካሄደ ነዉ። ባለስልጣናት ከፍተኛ መራጮች የታዩበት ምርጫ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

ፎቶ – AFP/Getty Images የምርጫ ቆጠራ
በፕሬዝዳንት ሲረል ራማፎሳ የሚመራው የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ANC ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ሳያጣ አይቀርም፤ ጥምር መንግሥት መመስረት ይኖርበታል፤ የሚል የሕዝብ አስተያየቶች የተሰሙበት ምርጫ፤ የድምፅ ቆጠራዉ እየተካሄደ ነዉ። በምርጫ ማዕከሎች ረጅም የምርጫ ሰልፎች ማስተናገዳቸዉን የታዘቡ ባለስልጣናት ከፍተኛ መራጮች የታዩበት ምርጫ ሲሉ አስተያየታቸዉን እንደሰጡ የጀርመን ድምጽ ዘገባ ያስረዳል።
የምርጫ ጣብያ ሠራተኞች ድምፅ መቁጠር የጀመሩት ባለፈዉ ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት የምርጫ ጣብያዎች ከተዘጉ በኋላ ነበር። የደቡብ አፍሪቃ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን (IEC) በህጉ መሰረት በሰባት ቀናት ውስጥ ውጤቱን ማሳወቅ ይኖርበታል። ይሁን እንጂ የደቡብ አፍሪቃ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሳይ ማቦሎ ሰባት ቀናት ሳይሞላዉ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል አመላክተዋል።
የምርጫ ጣብያዎች በይፋ ተዘግተዉ የድምፅ ቆጠራዉ ጀምሯል
ረቡዕ እለት በወጡ የመጀመርያ ደረጃ ዉጤቶች መሰረት፤ የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) 42.3 በመቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመምራት ላይ ይገኛል። ዴሞክራቲክ አሊያንስ (DA) ፓርቲ ከተያዙት ድምጾች 23.9 በመቶ ድርሻ ይዞ በርቀት ይከተላል። በዚህ የግማሽ የድምጽ ቆጠራ የመጀመርያ ዉጤት መሰረት በርካታ ተንታኞች በሀገሪቱ ከሚገኙ ዘጠኝ ክፍለ ሃገራት በሰባቱ እየመራ የነበረዉ ገዥው ANC ፓርቲ ከ50 በመቶ በታች ዉጤት እንደሚያገኝ ተንብየዋል። የፖለቲካ ተንታኝ ሳንድሌ ስዋና ANC በመጀመርያ የድምፅ ቆጠራ ዉጤት ከፍተኛ ቢሆንም የገዥዉ የ ANC ፓርቲ የመጨረሻ ውጤት ከ50 በመቶ በታች ሲሉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ።
“የ ANC ን ታሪካዊ ርምጃ በማየት እና የ MK ን መሰንጠቅ ብናቀናጅ፣ ገዥዉ የ ANC ፓርቲ በምርጫዉ 42 በመቶ ገደማ ዉጤት ላይ ሊያበቃ እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል”
የአምስት ወራት እድሜ ያለዉ (MK) ፓርቲ ማለትም ዩምኮንቶ ዌሲ ዝዌ ይፋ በሆነዉ የመጀመርያ መዘርዝር ትልቁና አስገራሚ ዉጤትን አሳይቷል። (MK )ፓርቲ በመጀመርያ ዉጤት መዘርዝር ከ11 በመቶ በማግኘት በአገሪቱ የምርጫ ሰሌዳ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል። ፓርቲዉ በክዋዙሉ ናታል ግዛት ትናንት አርብ በታየዉ የግማሽ ዉጤት መሰረት በሰፊ ልዩነት እየመራ ነዉ።
የ MK ዋና ሊቀመንበር ሲህሌ ንጉባቤን ለDW እንደገለፁት በሃገሪቱ ፓርቲ ባከናወነው ተግባር ለመጀመሪያ ጊዜ የተደነቀ ብለዉታል።
«በእዉነቱ ደስ ይላል፤ በጣም ደስ ይላል። ያም ሆነ ይህ፤ ይህን ዉጤት እንጠብቅ ነበር። የምርጫ ዘመቻዉን ስናካሂድ መሬት ላይ ምን እያደረግን እንደሆነ እናውቅ ነበር። ለነዋሪዎች ስለ MK ፓርቲ እውነቱን እየነገርን ለምን MK ን መምረጥ እንዳለባቸዉ አስረድተናቸዋል። አሁን ስላለው መንግሥትም እውነቱን ነግረናቸዋል።»

ውጤቱ ይፋ የሚሆነዉ መቼ ይሆን?
ምንም እንኳ በርካታ መራጮች የድምፅ ቆጠራዉ አዝጋሚ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ውጤቱ አጠያያቂ እንዳይሆን ለማረጋገጥ እና የተሟላ ሆኖ እንዲቀርብ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ አፍሪቃዉ የነፃ ምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል። ሁሉም የድምፅ ቆጠራ የሚካሄደው ድምፅ በተሰጠባቸዉ በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያዎች ነዉ። ይህ የሚከናወነዉ ደግሞ በፓርቲ ወኪሎችና ታዛቢዎች ፊት ነዉ። ከዚያም ቆጠራዉ ሲጠናቀቅ ውጤቱ ወደ ጎቴንግ ግዛት ሚድራንድ ወደ ሚገኘው ብሔራዊ የምርጫ ማዕከል ዋና መስርያቤት ከመተላለፉ በፊት በእያንዳንዱ የምርጫ ጣብያ ቅፅር ጊቢ ፊት ለፊት በሚገኝ ሰፊ ሰሌዳ ላይ ለሕዝብ በይፋ ይቀርባል።
በምርጫ እለት የሚያጋጥሙ ፈተናዎች
በብሔራዊው የነፃ ምርጫ ማዕከል ከተለያዩ ግዛቶች የመጡ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት በአንድነት ይደመራል። ይህን ዉጤት የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ከማድረጉ በፊት በኮሚሽኑ የቀመር ቡድኖች እንደሚመረመር እና የመጨረሻዉ ዉጤት ምርጫዉ በተካሄደ በሰባተኛዉ ቀን ይፋ እንደሚሆን የኮሚሽኑ ተለዋጭ ኃላፊ ዴቪድ ማንዳሃ ተናግረዋል።
“በእኛ እምነት ቅዳሜና እሁድ ውጤቱን ለማሳወቅ ዝግጁ ነን፤ ለማለት መቻል አለብን”
ረቡዕ ዕለት የተካሄደው የምርጫ ሂደት በአንዳንድ ጣብያዎች ባጋጠሙ የተበላሹ የኤሌክትሮኒክ የምርጫ መሳርያዎች፤ እና ባጋጠመ የመብራት መቋረጥ፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከደቡብ አፍሪቃውያን ከፍተኛ ቅሬታ እና ትችት ተሰምቷል።
በተለይ በጆሃንስበርግና በደርበን ዉስጥ በሚገኙ በርካታ የምርጫ ማዕከሎች የምርጫ ጣብያዎች ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ከተዘጋም በኋላ ተጨማሪ ረጅም ሰልፎች ታይተዋል። የጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነውችዉ ቻርሜን ሻባላላ የምርጫ ጣብያዉ ከተዘጋ ከ2 ሰዓት በኋላም ተስፋ አልቆረጠችም ነበር።
“በደቡብ አፍሪቃ እየተፈጸሙ ባሉ ብዙ ነገሮች ደክሞናል። የምንፈልገዉ ለውጥ ብቻ ነዉ። ስለዚህ ድምፅ መስጠት እንፈልጋለን
ጥምር መንግስት የደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ዉጤት ግምታዊ አስተያየቶች
በምርጫዉ 50 በመቶ በታች ዉጤትን እንደሚያገኝ ተተንብዮ የነበረዉ የደቡብ አፍሪቃዉ ገዥ ፓርቲ ANC፤ በወጡት የመጀመርያ ዉጤቶች መሰረት ትንበያዉ እዉን እየሆነ ይመስላል። በዚህም በአሁኑ ወቅት ምናልባትም የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚሉ ዉይይቶች እየተካሄዱ ነዉ። በምርጫዉ የተሳተፉ ፓርቲዎች የመጨረሻዉ ዉጤት ይፋ እስኪሲደረግ ካርዳቸውን ደረታቸዉ ኪስ አድርገዉ ለጥምር መንግሥት ዉሳኔ እየተዘጋጁ መሆኑን ይገልፃሉ።
ምንም እንኳ ብዙ ፓርቲዎች ከገዢው ANC ፓርቲ ጋር ምንም ዓይነት ጥምረት ላለመፍጠር ቃል ቢገቡም፣ ANC መንግሥት ለመመስረት የሚያስፈልገውን 50.1 በመቶ ድምፅን ለማግኘት ከሌላ ትልቅ ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር ጥምረት እንደሚያስፈልገው አሁን መገመት እንደሚቻል ብዙዎች ይናገራሉ።
የደቡብ አፍሪቃ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫዉ ያለምንም እክል አልፏል ሲሉ የእጅ አዉራጣታቸዉን ከፍ አድርገዉ አሳይተዋል። የምርጫ ተቋም ለአፍሪቃ ዘላቂ ዴሞክራሲ የተባዉን ድርጅት የሚመሩት እና የደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ጉድለክ ጆናታን የደቡብ አፍሪቃዉ ነፃ ምርጫ ኮሚሽን ከአህጉሪቱ የመጀመርያዉ እና ጠንካራዉ በመሆኑ በስራዉ እምነት አለኝ ብለዋል።
በደቡብ አፍሪቃ የምርጫ ኮሚሽን ላይ እምነት አለኝ። በአፍሪቃ ምርጥ ከሚባሉ የምርጫ ኮሚሽኖች አንዱ ነዉ። በጣም ጥሩ ሥራ እየሠሩ ነው ። አዎ፤ ሊመለከቷቸው የሚገቡ አንዳንድ ነጥቦች አሉ። እስካሁን ግን ጥሩ እየሰሩ ነው ሲል የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።
ዙማ ኤምኬን አዋልደው ዳግም መመለሳቸውና ስኬታቸው
የ82 ዓመቱ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ወደ ምርጫው ተመልሰዋል። ሲመለሱ ደግሞ ዝም ብለው ለመሳተፍ አይደለም የተመለሱት – በቀል ቋጥረው ነው። ኤኤንሲ በአውሮፓውያኑ 2018 በሙስና ቅሌት ክስ ከሥልጣን አባሯቸው ነበር። እሳቸው ግን ይህንን አስተባብለዋል። ያም ቢሆን ግን ከመሪነት ስፍራቸውም ተነስተው በሲሪል ራማፎሳ ተተኩ።
ከሥልጣን ከተነሱ ከሦስት ዓመት ገደማ በኋላም በዘጠኝ ዓመታት የፕሬዚዳንት ዘመናቸው የተፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን የሚመለከት አጣሪ ፊት እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት አዘዘ። ፕሬዚዳንቱ ይህንን ትዕዛዝ በመጣሳቸው የ15 ወራት እስር ተፈረደባቸው። ሆኖም ዙማ ለሦስት ወራት በእስር ከቆዩ በኋላ፤ እርሳቸውንም ሆነ የተቆጡ ደጋፊዎቻቸውን የበለጠ ላለማስቆጣት ፕሬዚዳንት ራማፎሳ እንዲለቀቁ ወሰኑ።
ነገር ግን አሁን የራማፎሳን ውሳኔ የሚያጸጽት ነገር ሳይከሰት አልቀረም። ዙማ ምኾንቶ ዊስዝዌ (ኤምኬ) በሚል ፓርቲ ወደ ፖለቲካው ግንባር ተመልሰዋል።
እስካሁን የወጡ የምርጫ ውጤቶች እንደሚያመለክቱ ኤኤንሲ ዋነኛው የድጋፍ መሠረቱ ነው በሚባልለት የኩዋዙሉ ናታል ግዛት በዙማ ፓርቲ ድምጽ ተነጥቋል።
በደቡብ አፍሪካ ትልቁ ሁለተኛው ትልቁ ክዋዙሉ ናታል ግዛት የዙማ ኤምኬ ፓርቲ 45 በመቶ ሲያሸንፍ፣ በመቀጠል ኢንካታ ፍሪደም ፓርቲ 18 በመቶ እንዲሁም ኤኤንሲ 17 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሦስተኛ ሆኗል።
ይህም ዙማ የግዛቲቱ አድራጊ ፈጣሪ ያደርጋቸዋል የተባለ ሲሆን፣ በዚህም ዋነኛ ዓላማቸው የሆነውን የራማፎሳን ውድቀት የሚያሴሩበትን መሠረት እንደሚፈጥርላቸው እየተነገረ ነው።
ምንም እንኳን በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በመባላቸው በአገሪቱ ምክር ቤት መግባት ባይችሉም፤ ሆኖም ከመጋረጃው በስተጀርባ ፖለቲካውን ሊያሽከረክሩት ይችላሉ ተብሏል።
የዙማ ፓርቲ ኤምኬ በዚህ መንገድ ድጋፍ ማግኘቱ ያልተለመደ ነው። ፓርቲው የተመዘገበው ከወራት በፊት መስከረም ላይ ሲሆን፣ ዙማ በራማፎሳ ለሚመራው ኤኤንሲ ድምጽ እንደማይሰጡ በመግለጽ ፓርቲውንም በታኅሣሥ ወር ነበር የተቀላቀሉት።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአፓርታይድ ሥርዓት ካከተመ በኋላ አዲስ ፓርቲ አድርጎት በማያውቀው መንገድ የደቡብ አፍሪካን ፖለቲካ አናግቷል።
የደቡብ አፍሪካው ሜይል እና ጋርዲያን ጋዜጣ የክዋዙሉ ናታል ዘጋቢ ፓዲ ሃርፐር እንደሚለው ኤምኬ የኤኤንሲን ድጋፍ ብቻ ሳይሆን፣ የአገሪቱ ሦስተኛ ትልቅ ፓርቲ የሆነውን ለስር ነቀል ለውጥ የሚታገለውን የጁሊየስ ማሌምን ኢኤኤፍ ፓርቲ ድጋፍን መሸርሸሩ ነው። እስካሁን በተገኘው የምርጫ ውጤት ኤምኬ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተምጧል። ሃያ በመቶ የሚጠጋ ድምጽ እንዳገኘም እየተሰማ ነው።
ዘገባው ኤፒ፣ ቢቢሲ፣ የጀርመን ድምጽ፣ ማህበራዊ ገጾችና አስተያየቶች የተካተቱበት ነው