ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያና ደ.ኮሪያ የአንድ ቢሊዮን ዶላር የልማት ፋይናንስ ትብብር ስምምነት ፈጸሙ። የፋይናንስ ልማት ትብብር ስምምነቱ የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነ ተመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴኡል ባደረጉት ቆይታም ይህንን ታሪካዊ ወዳጅነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ውይይቶችን አድርገዋል። ኮሪያ ሪፐብሊክ ባለፉት 50 ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገሮች አንዷ መሆኗን በዋናነት የዕድገት ልምዷን ለመጋራት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትኩረት መስጠታቸው ታውቋል።
በዚሁ መነሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ጋር መክረዋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከውይይቱም በሁዋላ ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስራቸውን የሚያጠናክርላቸውን የፋይናንስ ስምምነት መፈራረማቸውን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ የተፈራረሙት የፋይናንስ ልማት ተከትሎ ትብብር ስምምነት የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኮሪያ ሪፐብሊክ ሴኡል መግባታቸውን ተከትሎ ከኮሪያ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት መደረጉን የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሸዲ ገልጸዋል።
በውይይታቸውም የኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸውን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል።
የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት ለኢትዮጵያ ልማት የፋይናንስ እገዛ ማድረግን ጨምሮ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ማጠናከር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ግብርና ልማት ዙሪያ ይበልጥ ተቀራርበው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ብለዋል።
ከመሪዎቹ ውይይት በኋላም ለአራት አመታት የሚተገበር የ1 ቢሊዮን ዶላር የልማት ፋይናንስ ትብብር ስምምነት መፈረሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ገንዘቡ ለመሰረተ ልማት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ፣ ለጤና እና ለከተማ ልማት የሚውል ይሆናል ነው ያሉት።
የፋይናንስ ልማት ትብብር ስምምነት የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ተናግረዋል። የአሁኑ የልማት ፋይናንስ ትብብር ስምምነቱ የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል በኢትዮጵያ በቀጣይ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑን አረጋግጠዋል ነው ያሉት አቶ አህመድ ሽዴ በማብራሪያቸው።