በኢትዮጵያ ነፍጥ ያነሱ፣ ” ሰላማዊ ትግል መርጠናል” ቢሉም ከጀርባ ሆነው ነፍጥ ያነሱትን ከሚመሩና ከሚያደራጁ፣ በድርጅት መልክ ሳይሆን በተናጠል ታጣቂዎችን ከሚመሩና በትቅሉ ጫካ ካሉ ሃይሎች ጋር በሚስጢር ተያዞ እየተካሄደ ያለው ንግግር መልክ እየያዘ መሆኑ ተሰማ። ችግሮቹም ተጠቁመዋል።መንግስ የኢትዮጵያ አገራዊ ኮሚሽን የሚያቀርበውን አማራጭ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበል አስታውቋል።
ነዋሪነታቸው በውጭ አገር የሆኑ ሁለት አካላት ለመንግስት አማራን ወክለው ለመደራደር ዕውቅና የሚጠይቅ የመደራደሪያ መነሻ ሰነድ አዘጋጅተው መላካቸውንና መንግስት ለጊዜው ምንም በገሃድ ምላሽ እንዳልሰጠ ጠቁመን መዘገባችን ይታወሳል። ይህንኑ ዜና ተከትሎ በአገር ቤት ውስጥ ያሉና የተበታተነው የፋኖ ትግል ያሳሰባቸው ወገኖች ክልሉ ወደ ማይነሳበት ኪሳራ ከማምራቱ በፊት የሰላም አማራጭ ሊከተል እንደሚገባ ያመኑ ወገኖች ሃላፊነት ወስደው ጥረት መጀመራቸውንም አስታውሰን እንደነበር አይዘነጋም።
በአገር ውስጥ በእነዚሁ ግለሰቦች፣ የክልሉ ባለስልጣናት አሜሜካ በቆዩበት ወቅት በተደረገ ሚስጢራዊ ግንኙነት፣ እንዲሁም የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ስም ሳይዘረዝር ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ግንኙነት መጀመሩን ማስታወቁን ተከትሎ ኢትዮሪቪው እንደሰማችው ከሆነ በሁሉም አቅጣጫ የተጀመረው የሰላም አካሄድ ተስፋ ሰጪ ከሚባልበት ደረጃ አልፏል።
በተእይ በኦሮሚያና በአማራ ክልል ህዝቡ “ነጻ እናውጣችኋለን” በሚሉት ወገኖች መማረሩ፣ በጥቅሉ በዕገታ፣ በዝርፊያ፣ በግብር፣ በግድያና የተለመደ የግብርናና የማህበራኢ እንቅስቃሴው በ፣እግታቱ ሳቢያ ታጣቂዎቹ የሰላም አገባብን እንዲያጤኑ ገፊ ምክንያት እንደሆነ ዜናውን የነገሩን አመልክተዋል።
አሁን ላይ እንደ መጠነኛ ተግዳሮት የሚነሳው በኢትዮጵያ ጦርነትን ስፖንሰር የሚያደርጉ ባእዳንና ከነዚሁ ባዕዳን ጋር ግንኙነት መስርተው ብር በመላክ ተጽዕኖ የሚፈጥሩትና ” የግጭት ነጋዴዎች” በሚል ድርድሩን ለማመቻቸት የሚጥሩ የሚገልጹዋቸው ክፍሎች የሚያደርጉት ጫና ነው። ይህም ቢሆን ጫናው ከዛሬ አምስትና አራት ወራት በፊት እንደነበረው አለመሆኑን የዜናው ሰዎች ገልጸዋል።
እስክንድ ነጋ ቀደም ብሎ አቋሙን ባስታወቀው መሰረት በአሁን ሰዓት ንግግር እንዲጀመር ከሚያመቻቹ ወገኖች ጋር በቅድመ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ እንደሆነ የሚገልጹት ክፍሎች፣ በጎጃም ከሚንቀሳቀሱት ውስጥ ትልቅ ሃይል አላቸው የሚባሉትና አሁን ላይ ይዞታቸውን ለቀው ወደ በረሃ ያፈገፈጉት ለመስማማት ጫፍ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።
ክልሉ ራሱን ከላይ ጀምሮ በአዲስ ካዋቀረ በሁዋላ በጀመረው እንቅስቃሴ የሰላም ድርድር እንዲደረግ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በየጊዜው የታጠቁ ሃይሎች ወደ ሰላማዊ ኑሯቸውም መመለሳቸው ለሰላም ንግግሩ እንደ ተጨማሪ ግብአት ሆኖ እንደረዳ ከዜናው ሰዎች ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ መሰረት ከየአቅጣጫው እየተደረገ ባለው ጥረትና በመሬት ላይ ባለው ሃቅ የድርድር አግባቡ ወደሚቁጭበት ደረጃ ተደርሷል።
እስክንድር የፋኖ ሃይ፣ኦችን በመወከል ለመደራደር ቅድም ንግግር መጀመሩን ያወሱት ወገኖች የትኞቹን የፋኖ ሃይሎች እንደሚያካትት ገና ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ምን ያህል አቅም እንዳለው አሁን ድረስ እንዳልጠራም አመልክተዋል። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አቋሙን ቀይሮ ከብልጽግናና ጋር ለመስራት እያመቻመቸ መሆኑ ሌሎቹ ተስፋ አስቆርጧል።
በኦሮሚያ ክልል ነፍ አንስቶ ጦርነት የገጠመውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሃይል የሚለው ቡድን ቀደም ሲል በተደረገው ድርድር ለመግባባት ጫፍ ከደረሰ በሁዋላ አቋሙን የለወጠው ከአዲስ አበባ በተሰጠ መመሪያ እንደሆነ መዘገባችን አይዘነጋም። ይህንኑ በሚያጠናክር መልኩ ጃል መሮ በዙም በተካሄደ ኮንፍረንስ “የማይለወጡ ሽማግሌዎቼ” እስከማለት የደረሰው በድርድሩ መጨናገፍ ሳቢያ በርካታ የሰራዊቱ አባላትና አመራሮች ስለከዱት፣ እንደማይታዘዙ ስለገለጹለትና በግልጽ ስሙን ጠርተው ስለተቃወሙት እንደሆነ መረጃዎች ወጥተዋል። ይፋ የሆነው የስብሰባቸው ቃለ ምልልስም ይህንኑ ያስረዳል።
አሁን ላይ ጃልመሮ የሚመራው የኦእነግ ታጣቂ አሃይል አቅም በይፋ ባይታወቅም ቀደም ሲል የነበሩዋቸውን ይዞታዎች አጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወለጋ ገብተው ከህዝብ ጋር መከራቸው፣ ደንቢዶሎን ጨምሮ አውሮፕላን በረራ መጀመሩ፣ የተቋረጡ ፕሮጀክቶች መጀመራቸው፣ ህዝቡ ኤከጨላማ ወጣኔ በሚል ድጋፍ መከልከሉ አሁን ላይ ከላይ የተዘረዘሩት አሸማጋዮች እያደረጉ ላለው ጥረት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ዕርቅ ኮሚሽን ለሚያቀርበው ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዐድዋ አዳራሽ ባደረጉት ንግግር የሰጡት ምላሽ ለበርካቶች መነጋገሪያ ምክንያት ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምክክር ኮሚሽኑን የመጨረሻ ውጤት መንግስታቸው ያለማቅማማት እንደሚቀበለው ማስታወቃቸው አሁን ተስፋ ከተጣለበት የውይይት ዜና ጋር ያቆራኙ ወገኖች “ይህ የመጨረሻ ዕድል እንዳያመልጠን” የሚለው ማሳሰቢያም ንግግር የጀመሩ ሳይረፍድ ወደ ገሃድ ዕርቅ ዞረው ምክክር በተጀመረበት የኢትዮጵያ የወደፊት ጉዳይ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያበረታታ እንደሆነ የገለጹ ጥቂት አይደሉም።
አገራዊ የምክክር መድረኩ እንደሚጀመር ይፋ መሆኑንን ተከትሎና ከተጀመረ በሁዋላ በሶማሌ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጋ አብረው ለምስራት መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል። የኦሮሚያ ክልልም ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ምክክር እያደረገ መሆኑ ይፋ ሆኗል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ ” ሰላም ሰላም …” በሚል ጥሪ ካቀረቡ በሁዋላ እየተደረገ ያለው ውይይት ውጤቱ ለጊዜው አልተገለጸም።