ከሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት እየወጣ ያለው መረጃ ዜጎችን ስሜት የሚፈታተን ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሞቃዲሾ ነዋሪዎችን አቅፋና ደጋፍ የያዘቸው ኢትዮጵያ ላይ የተከፍተው ዘመቻ ሳያንስ፣ ለሶማሊያ ሰላም ከአልሸባብ ጋር ህይወቱን እየከፍለ ለኖረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚሰጠው ግብረመልስ
ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዓመታት ትከተል በነበረው የተላላኪነት ፖሊሲ እንደተለመደው ዓይነት ሳይሆን ጥቅሟን ለማስከበር በሰጥቶ መቀበል መርህ መንቀሳቀሷ ኤርትራን ጨምሮ ታሪካዊ ጠላቶቿ የአድማ ዘመቻ ጀምረዋል። ለዚህ ደግሞ አሜሪካ አንዷ ናት።
የዚህ የአድማው አካል የሆነው ዜና የሞቃዲሾ መንግስት በሶማሊያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በቀጣይ ታህሳስ ወር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ቪኦኤ መዘገቡ ነው። ከኢትዮጵያ ወገን ምን ምላሽ እንዳለና የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል በስለም አስከባሪነት ሶማሊያ ሲቀመጥ ያበረከተውን አስተዋጾ በዘነጋ መልኩ የቀረበው ሪፖርት ምላሹ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።
ከኢትዮጵያ በኩል በይፋ የተሰጠ አስተያየት ባይኖርም የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሶማሌ ዘኤጎች ጦሩ ጥሏቸው እንዲሄድ እንደማይፍለጉ በተደጋጋሚ መግላጻቸው አይዘነጋም። በአፍሪካ ህብረት ውሳኔም ባይሆን ኢትዮጵያ ለስለሟ ስትል ምን ዓየነት አካሄድ ልትከተል እንደምትችል ግን ፍንጭ አለ።
ሶማሊያ በሀገሯ በሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኙ ሁሉም የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣይ አመት 2017 ታህሳስ ወር ላይ ጠቅልለው ይወጣሉ ብላ እንደምትጠብቅ ቪኦኤ የዘገበው የአገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ ነው።
የቪኦኤ ዘጋቢ ሃሩን ማዕሩፍ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑትን ሁሴን ሼክ አሊን ጠቅሶ ያሰራጨው ዜና እንደሚያመልክተው የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ተልዕኮው ካበቃ በኋላ “የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሃይል አባል አይሆኑም” ብሏል።
ዘገባው አክሎም ከቀጣይ ዓመት በኋላ በሶማሊያ በሚሰፍረው ጦር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደማይኖሩ እና ከሌሎቹ የሰላም አስከባሪ ሀይል ካበረከቱ አራቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ የተውጣጡ ብቻ እንደሚሆኑ ጠቁሟል።
በሶማሊያ ሰላም በማስከበር ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቀጣይ አመት 2017 ታህሳስ ወር ላይ በሶማሊያ የሰፈረው የሰላም አስከባሪ ጦር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል።
ይሁን እንጂ የሰላም አስከባሪው ሀይሉ ለቆ ከወጣ በኋላ ዋና ዋና የህዝብ ማዕከላትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን እና የሀሪቱ መንግስት ቁልፍ ተቋማትን በመቆጣጠር ጸጥታ የሚያስከብር ሀይል ለማቋቋም ዕቅድ መኖሩ ተጠቁሟል።
በያዝነው አመት የታህሳስ ወር መጨረሻ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ ይታወቃል።
ለዜናው የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ምላሽ አልሰጠም። በቅርቡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከስልሳ በመቶ በላይ የሶማሌን ግዛት ሰላም የሚያስጠብቀው የኢትዮጵያ መከላከያ መሆኑንን መግለጻቸው ይታወሳል። ሰራዊቱ በሰፈረባቸው አካባቢዎች ሁሉ ህዝቡ መከላከያ ለቆ እንዲወጣ ፍላጎት እንደሌለው ማግለጻቸውም የሚዘነጋ አይደልም።
ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለደህንነቷ ስትል የምትወስደው የራሷ አቋም እንዳለም ፍንጭ ሰጥተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ አስቀድመው ማብራሪያና አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ ወገኖች ኢትዮጵያ ሰላሟን፣ ጸጥታዋንና፣ ጥቅሟን ለማስከበር የምትችልበትን አግባብ ለትከተል እንደሚገባ ደጋግመው ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል። መንግስትም አሁን ላይ የያዘውን የመለሳለስና የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት የቀድሞ አካሄድ ያስቀረ መሆኑንን በተለያዩ አጋብቦች ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ሶማሊላንድና ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ያጠናቅቁታል በተባለው የባህር በር ስምምነት ውል መሰረት የጸጥታና የደህነት ትብብራቸውን ስለሚያጠናክሩ ኢትዮጵያ ከሶማሌያ የሚነሳባትን ማናቸውም ስጋት ለመቆጣጠር የጦር መሰረቷን እንደምታጠናክር ይጠበቃል።፡