በወለጋና አካባቢው በስፋት ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ ወደ ሸዋ ማቅናቱን መሪያቸው ጃል መሮ መናገሩ ተገለጸ። ጃልመሮ ኤ የተቀባ” ያሉት ጦራቸው አዲስ አበባን በአምስት አቅጣጫ እንደከበበ ተናግረዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም በወለጋና አካባቢው የኦነግ ሰራዊት ሽንፈት መከናነቡንና ህዝብ በምሬት ከመንግስት ጋር በመቆሙ ለደረሰው ኪሳራ የተሰጠ ምክንያት መሆኑም ከሰላም ድርድሩ መክሸፍ በሁዋላ “ጦርነት ይቁም” በሚል የሚነቀሳቀሱ አካላት አስታውቀዋል።
በዙም ውይይት የተሳተፉ ለኢትዮሪቪው እንዳሉት ጃልመሮ ጦራቸው ወለጋን ለቆ መውጣቱን ሲያስታውቁ እንዳሉት አሁን ላይ በወለጋ በስም ባልተጠቀሰ አካባቢ የሚገኘው ስልጠና ላይ ያለ ምልምል ሃይል ብቻ ነው። ዜናውን የነገሩን እንዳሉት ጃልመሮ ይህን ሲሉ ወለጋ መድቀቁ፣ ህዝቡ ማለቁንና ለከፋ ድህነት መዳረጉን እንደተገለጸ አመልክተዋል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ተፈናቅለው ከወለጋ የተፈናቀሉ እንደመሰከሩት ላለፉት አምስት ዓመታት ወለጋ ገሃነም ሆናለች። ህጻናት በግዳጅ ለውትድርና ተመልምለዋል፣ አሁንም እየተመለመሉ ነው። በጦርነቱ ሳቢያ ለዓመታት አርሶ አደሩ ማረስ አልቻለም። የደረሰ ቡና መልቀም አልቻለም። አርሶ አደሩ ሃብቱን ከስሯል። ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም። ማንኛውም ህጋዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል። በርካቶች ከዛም ከዚህም ተገድለዋል። አፈናና እገታ መረን ለቋል። በምርታማነቱ የሚታወቀው ወለጋ በታሪኩ ተርቦ ተረጂ ለመሆን ተዳርጓል።
ከወለጋና አካባቢው ነጋዴዎች ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል። ለወትሮው ቡና ነግዶ የሚዝናና ገበሬ ለማኝ ሆኗል። የህክምና ተቋማትና አገልግሎት መስጫዎች ቆመዋል፣ ወድመዋል። ስልክ፣ ኤሌክትሪክ የለም። በጥቅሉ ያለፉት ዓምስት ዓመታት የሆነው ሁሉ ህዝቡ ክፉኛ መማረሩን የሚገልጹ በአካባቢው የሚነቀሳቀሰው የኦነግ ሰራዊት ተቀባይነት ማጣቱን ጃልመሮ ወለጋን ለቀው ለመውጣታቸው ምክንያቱ ያሉትን ዘርዝረዋል።
ጃልመሮ ከቀናት በፊት በዙም ለወዳጆቻቸውና ለትግል አጋሮቻቸው ባደረጉት የዙም ንግግር የኦነግ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ለማምራት ወደ ሸዋ መትመሙን ይፋ አድርገዋል። ይሁን እንጂ እሳቸው ጦሩን ሸዋ አዲስ አበባ ዙሪያ ሆነው ስለመምራታቸውም ሆነ አተቃላይ ስለ ሰራዊታቸው ቁመና አላብራሩም።
ባለፉት ሶስትና አራት ወራት ኦነግ ለረጅም ጊዜ ሲቆጣጠራቸው የነበሩ አካባቢዎችን ማጣቱን፣ ሰፊ ቁጥር ያለው ተዋጊዎች መማረካቸውንና መመታታቸውን መንግስት በምስልና በምስክር በማረጋገጥ ማቅረቡ፣ በወለጋና ደንቢዶሎ ተቋርጦ የነበረ አገልግሎት መጀመሩ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነቀምት በይፋ መገኘታቸው፣ የመንግስት ባለስልጣናት አደገኛ በሚባሉ አካባቢዎች በተደጋጋሚ መገኘታቸው፣ ህዝብም በስፋት ወጥቶ አቀባበል ማድረጉን ተከትሎ ኦነግ በወለጋና አካባቢው እንዳበቃለት ጠቅሰው የመንግስት ካድሬዎች በተደጋጋሚ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል።
ከትናንት በስቲያ በአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም፤ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋና ምስራቅ ወለጋ የሞባይል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ወረዳዎችን ዘርዝሮ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። የስልክ አገልግሎትን ተጀምሯል።
“እኔ የምገኘው ኦሮሚያ ጫካ ውስጥ በወለጋ የቡና ዛፍ ሥር ነው” በማለት ለቢቢሲ ቀደም ባሉት ዓመታት የገለጸው ጃል መሮ መንግስት በስፋት የማጥቃት ዘመቻ መክፈቱንና ጦራቸው የሚቆጣጠራቸውን አካባቢዎች መነጠቁን ተከትሎ የት ሆነው ጦሩን እንደሚመሩ በዙም ስብሰባው ላይ አላስታወቁም። ወይም አላነሱም። ጦራቸው ለረጀም ዓመታት ያለ ከላካይ የሚቆጣጠራቸውን ይዞታዎቹን ስለማጣቱም አላብራራም።
በቅርቡ “ነገሮች ተበላሽተዋል” ሲል የተደመጠው ጃልመሮ ማብራሪያውን ለነማን እንደሚያቀርብ ባይታወቅም “ያረጁ” በሚል የሚወቅሳቸው ክፍሎች እንዳሉ በተጠለፈ ስልክ ሲናገር ተሰምቶ ነበር። ጃልመሮ ” የሚታዘዝ የለም። የሚሰማ የለም” ሲል ሰራዊቱ ውስጥ የአመራሮች መከፋፈል መኖሩን ማመልከቱ አይዘነጋም።
ጃልመሮ ከመንግስት ጋር በነበረው ድርድር ተሳትፎ ሲመለስ ተቃውሞ እንደገጠመውና አለመግባባቱ እንዳየለ የተሰማው ወዲያው ነበር። በአገር ቤት ያሉት የኦነግ ሰራዊት አብዛኛው አመራር በመርህ ደረጃ የሰላም ስምምነቱ እንደሚሳካ አስቀድሞ እምነት ነበራቸው። በጉዳዩ ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚሉት ቅድመ ስምምነትም ነበር። የሰላም ድርድሩን ያመቻቹ ለዝግጅት ክፍላችን እንደጠቆሙት ጃል መሮ ከደንቢ ዶሎ በመንግስት በሄሊኮፕተር ለድርድር ጉዞ ሲመቻችላቸው ቅድም ስምምነቱ የላቀ ደረጃ መድረሱን እንደሚያሳይም አመልክተው ነበር።
በታንዛንያው የድርድር የመጨረሻ ሰዓት ከአገር ቤት ለጊዜው ስማቸው የማይጠቀስ ነባር አመራር ስልክ በመደውል ” የሽግግር መንግስት ካልሆነ አትቀበሉ” በሚል በሰጡት መመሪያ ሳቢያ ድርድሩ መክሸፉ በታጣቂዎቹ አመራሮች ዘንዳ ለተከሰተው ልዩነትና የእርስ በርስ ግጭት ዋና ምክንያት እንደሆነ እነዚህኑ የመረጃ ሰዎች ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።
” NO WAR” በሚል መርህ በሚካሄድ ውይይት ላይ የጃል መሮ አዲሱ ዜና ተነስቶ ነበር። በውይይቱ “ወለጋ ደቋል፣ ተረኛው ሸዋ ነው” በሚል ከወለጋ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተው ” ሸዋ ተረኛ” ሲሉ ተደምጠዋል።
በዚሁ ውይይት ከኦነ፣ ከብልጽግና እንዲሁም ከኦፌኮ ደጋፊዎች ተካተዋል። ገለልተኛ መሆናቸውን የሚገልጹም ነበሩበት። የኦነግ ደጋፊም ሆነው ጦርነት የሰላቻቸው መበራከታቸውን። ማናቸውም ጉዳዮች በንግግር ይፈታ የሚሉ ድምጾች እየበዙ መሆናቸውን ጠቅሰው ሲወያዩ ” አሁን ተረኛው ሸዋ ነው። ልክ እንደወለጋ ሸዋን ለማራቆት ያለመ ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም ምክንያት ሊቀርበለት አይችልም” ሲሉ ጃልመሮ ወደ ሸዋ ማምራታቸውን ነቅፈዋል። “እስከመቼስ ነው ኦሮሞ ከዚህም ከዚያም የሚገደለው” ብለዋል።
“ህዝብ አርሼ ልብላ፣ እንደልቤ ልንቀሳቀስ፣ ጦርነት ይቁምልን” እያለ መሆኑን ያመለከቱ በኦሮሚያ አምስት አቅጣጫ ከቦ ወደ አዲስ አበባ እየመጣ እንደሆነ መሮ የገለጹለት ” የተቀባ የኦነግ ሰራዊት” ያሰበው ይሳካለትም አይሳካለትም፣ እንደተባለው ኦነግ ሸዋ ውስጥ አዲስ አበባ ዙሪያ የሽምቅ ጥቃት ከመረጠ አሳቡ ኦሮሚያን ሙሉ በሙሉ የሚያደቅ እንደሆነ አመልክተዋል። ይህ ደግሞ ለኦሮሞ ህዝብ የሚፈይደው አይኖርም። ህዝቡንም፣ ኦሮሚያንም ሆነ ኢትዮጵያን አመድ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የጃል መሮን አዋጅ ተከትሎ አስተያየት የጠየቅናቸው የኦፌኮ አመራር ቀደም ሲልም ጀምሮ በሸዋ በቡድን በቡድን ሆነው እዛም እዚህም የሚንቀሳቀሱ አሉ። አሁን ባለው ሃቅ በጦርነት ብልጽግናን ማስወገድ የሚሳካ እንደማይመስላቸው ማሳያዎችን ዘርዝረው ካስረዱ በሁዋላ፣ ” በደፈጣ መንገድ ማስተጓጎ፣ ጥቃት መሰንዘር፣ ማፈንና መግደል ይቻል ይሆናል እንጂ ከዛ የዘለለ ነገር ይገኛል ብዬ አላስብም” ብለዋል።
በጦርነት ይቁም ዘመቻ አራማጆች አውድ አዱና የተባሉ ተናጋሪ ኦነግም ሆነ የክልሉ መንግስት ሁሉም የራሳቸውን ስልታን እንጂ የህዝብን ፍላጎት ማዕከል አድርገው እንደማያውቁ ገልጸዋል። ” የታንዛንያው የሰላም ድርድር የፈረሰው ስልጣን ስጠኝ፣ ስልጥን አልሰጥም በሚል ሙግት ነው። ይህ የሚያስረዳው ግጭቱም፣ ጦርነቱም፣ ሽኩቻውም የስልጣን ጉዳይ እንጂ የህዝብ ፍልጎትን የማሳካት ጉዳይ አይደለም። ስለሆነም ስልጣን ፈላጊዎች ስልጣን እስኪያገኙ ህዝብ ይሞታል። ይፈናቀላል። ይዘረፋል። ይታገታል። አገር ይወዳማል “