በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ የትግራይ ሃይሎች ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመው ህጻናትን ጨምሮ ንጹሃንን መግደላቸው፣ ንበረት መዘረፋቸውንና መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሩ አስታወቁ።
ቢቢሲ ሁሉንም ወገኖች አነጋገሮ እንደዘገበው በተፈጸመ ጥቃት 15 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውተቃጥለዋል። ከአምስት መቶ በላይ እንሳሳትን ዘርፈዋል። ድሽቃን ጨምሮ ከባድ የርቀት መሳሪያ በመጠቀም ሰፊ ጉዳይ አድርሰዋል።
“የትግራይ ኃይሎች” መሆናቸውን እንዴት እንዳወቁ ቢቢሲ ለጠየቀው፣ በሚናገሩት ቋንቋ እንደለይዋቸውና በተለያዩ ጊዜያትም ትንኮሳዎችን ይፈጽሙ ስለነበውር እነሱ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ምስክርነት ሰጥተዋል። የቆሰሉና ወልቃይት ለህክምና የሄዱ ተናግረዋል።

“የትግራይ ታጣቂዎች ናቸው። ከእነሱ ውጪ የሚመጣብን ሌላ እንደሌለ ነው የተረዳነው” ሲሉ ነዋሪዎች ለሰጡት ምላሽ፣ የአድርቃይ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮንም “ቡድኑን የሚመራውን ግለሰብ ጭምር እናውቃለን” ሲሉ ጥቃት አድራሾቹ “የትይህነግ ታጣቂዎች” ስለመሆናቸው ተጨማሪ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በበኩሉ ጥቃቱን የትግራይ ኃይሎች አለመፈጸማቸውን በመግለጽ አስተባበለዋል።
የትህነግ ሃይሎች ፈጽመውታል ስለተባለው ጥቃት የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስት ይህ እስከተጻፈ ድረስ በይፋ የሰጡት መግለጫም ሆነ አስተያየት የለም። “ትህነግ ጦርነትን አቁሟል፣ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሷል” በሚል የተገፈፈውን የፓርቲነት መብት ዳግም ለመመለስ ህግ ተሻሽሎ በጸደቀበት ቀን ይህ መሰማቱ ለበርካቶች አስገራሚ ጉዳይ ሆኗል።
በራያና በአላማጣ አቅጣጫ የትግራይ ሃይሎች ወረራ መፈጸማቸውና በርካታ ነጹሃን ቀያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። በዚያም አካባቢ ዝርፊያ መካሄዱንና አሁን ድረስ አርሶ አደሮ እየተዘረፈ እንደሆነ ቢገለጽም፣ አቶ ጌታቸው አክላባቢውን ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ከመ4ግለጻቸው አውጪ በተግባር የታየ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል
ቢቢሲ ያቀረበው ሪፖርት ከስር ያንብቡ
በወረዳው አሊጣራ ቀበሌ አንካቶ በተባለ ጎጥ ማክሰኞ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት “የቡድን መሳሪያ” ታጥቀዋል የተባሉ ከየትግራይ ክልል በኩል የመጡ ናቸው ያሏቸው ኃይሎች ከባድ ጥቃት መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለትግራይ ክልል አዋስኝ በሆነው አካባቢው “በዋልድባ ገዳም” በኩል አድርገው ገብተዋል የተባሉ በመቶዎች የተገመቱ “የትግራይ ኃይሎች” ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና ከብቶችን መዝረፋቸውንም የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከትግራይ በኩል ጥቃት ተፈጽሞበታል ወደ ተባለው “አካባቢ የተደረገ እንቅስቃሴ የለም” ሲል ጥቃቱን አስተባብሏል።
የአካባቢው ነዋሪ በተኛበት የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተ በስፍራው ነዋሪ የሆኑት አቶ ታለ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልጸው፤ ጥቃቱ ከንጋቱ 11፡00 ጀምሮ እስከ ጠዋት 2፡30 ገደማ መዝለቁን ተናግረዋል።
ጥቃቱ ሲፈጸም “ከተኛንበት በውስጥ ሱሪያችን ነው የወጣነው” ያሉት አቶ ባቡል ፀጋዬ፤ በጥቃቱ አራት ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉባቸው ተናግረዋል።
“በአንድ ቤት አምስት ነበርን፣ ከአምስታችን እኔ ነኝ በአጋጣሚ የተረፍኩት፤ ሌሎቹ ሞቱ። አሰልፈው ነው የተኮሱብን።. . . እኔንም ሞቷል ብለው ነው ትተውኝ የሄዱት። በፈጣሪ ፈቃድ ነው የተረፍኩት” ሲሉ ጥቃቱን የገለጹት ነዋሪው፤ በጥይት ጀርባቸውን ተመተው ሆስፒታል መተኘኛታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በጥቃቱ 15 ሠዎች መገደላቸውን በዐይናቸው እንተመለከቱ የተናገሩት ሌላ እማኝ፤ ሁለት የ16 እና የ19 ዓመት የእህት ልጆቻቸው እንደተገደሉባቸውም ተናግረዋል።
ይህኑ ቁጥር ያረጋገጡት ሌላ ነዋሪ በእሳት እና በጥይት ሦስት ታዳጊዎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።
“. . .ህጻናትን ጨምሮ 15 ሠዎች መገደላቸውን አይቻለሁ” ያሉት ነዋሪው፤ በጥቃቱ እግራቸውን ሁለት ቦታ ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
የአድርቃይ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ታደሰ በበኩላቸው በጥቃቱ ተገድለው ቀብራቸው መፈጸሙን ማረጋገጥ የቻሉት ስምንት ሰዎች መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከስምንቱ ሟቾች መካከል ስድስቱ ንጹሃን ነዋሪዎች ናቸው ያሉት አስተዳዳሪው፤ ሁለቱ ደግሞ የአካባቢው ሚሊሻ አባላት የነበሩ ናቸው ብለዋል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ሦስት የአካባቢው ነዋሪዎች ቆስለው ሆስፒታሉ እንደገቡ የወልቃይት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለቢቢሲ አረጋግጧል።
የሆስፒታሉ ተወካይ አቶ ዮናስ ካሳሁን ሁለቱ ታካሚዎች እግራቸውን፣ አንድ ታካሚ ደግሞ ጀርባቸውን በጥይት መመታታቸውን ገልጸው ሁለቱ ታካሚዎች “ከባድ ጉዳት” እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የጥይት ተኩስ ሰምተው ከቤታቸው መውጣታቸውን የተናገሩ አቶ ወንድሙ ደግሞ፤ ሚሊሻ በመሆናቸው ከጥቃት ፈጻሚዎች ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ውስጥ መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
አብሯቸው የነበረው ታናሽ ወንድማቸው በጥቃቱ መገደሉን የተናገሩት ነዋሪው፤ የጉዳቱን መጠን “ከባድ” ብለውታል።
“ቦምብ ጉዳት አድርሷል፤ ጥይቱ፤ መሳሪያውም ብዙ ስለሆነ፤ ድሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬን አላቸው። በእርቀት እየተኮሱ ነው ጉዳት ያደረሱት” ብለዋል።
“ምንም ያልያዙት መሳሪያ የለም” ሲሉ በጥቃቱ ቦምቦቹም መወርወራቸውን የተናገሩት አንድ ነዋሪ፤ ስምንት ቤቶች ሲቃጠሉ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ከትግራይ በኩል መጡ የተባሉት ኃይሎች ጥቃቱን ፈጽመው አካባቢውን ለቀው ሲወጡ ሦስት ሰዎችን መውሰዳቸውን እና 500 ከብቶችን መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
“የመንደሩን ከብት በሙሉ ወስደውታል። ምን ያህል አህያ እንደወሰዱ እና እንደተዉ ነው እንጂ ያላወኩት ከብት ከ500 በላይ የሚሆን የሁሉንም [ነዋሪ] ወስደውታል። የቀረ ነገር የለም። ጥጃውን እየፈቱ ነው ይዘውት የሄዱት” ያሉት ነዋሪ የእሳቸውም 24 ከብቶች እና አንድ አህያ ከተዘረፉት መሀል ናቸው ብለዋል።
“በጣም ብዙ ናቸው። ቢያንስ ከ400 ያላነሱ ናቸው” ሲሉ ጥቃት አደረሰብን ስላሉት ኃይል የተናገሩት አንድ ነዋሪ ማንነታቸውንም “ህወሓቶች ናቸው” ብለዋል።
ጥቃት የፈጸሙት ታጣቂዎች “ድብልቅልቅ” ያለ ልብስ የለበሱ ናቸው በማለት ሁሉም የወታደር መለያ ልብስ አለመልበሳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ ለጥቃቱ “ዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚንቀሳቀሱ” ያሏቸውን የትግራይ ኃይሎች ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፤ ታጣቂዎቹ ወደ አካባቢው ከዚህ ቀደም “ሰርገው ይገቡ” የነበረ ቢሆንም ጥቃት አለማድረሳቸውን ጠቅሰዋል።
“የትግራይ ኃይሎች” መሆናቸውን በምን እንዳወቁ በቢቢሲ የተጠየቁት ነዋሪዎች በሚናገሩት ቋንቋ መሆኑን እንደለይዋቸው እና በተለያዩ ጊዜያትም ትንኮሳዎችን ይፈጽሙ እንበነበሩ አንስተዋል።
“የትግራይ ታጣቂዎች ናቸው። ከእነሱ ውጪ የሚመጣብን ሌላ እንደሌለ ነው የተረዳነው” ብለዋል።
የአድርቃይ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮንም “ቡድኑን የሚመራውን ግለሰብ ጭምር እናውቃለን” ሲሉ ጥቃት አድራሾቹ “የህወሓት ታጣቂዎች” ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በበኩሉ ጥቃቱን የትግራይ ኃይሎች አለመፈጸማቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል።
“እኛ እስካሁን ድረስ ወደዚያ አካባቢ ያደረግነው ምንም እንቅስቃሴ የለም” በማለት በጥቃቱ “የትግራይ ኃይል” እጅ እንደሌለበት የተናገሩት የቢሮው ባለሙያ አቶ አማረ ኃይሌ ውዝግብ ያለባቸውን አካባቢዎች “በግጭት የመያዝ ፍላጎት የለንም” ብለዋል።
አድርቃይ ወረዳ ውዝግብ ከሚነሳባቸው ‘ወልቃይት እና ጠለምት/ጸለምት’ አካባቢዎች ጋር የሚዋሰን ነው።
የወረዳው አስተዳዳሪ ጥቃቱ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የይገባኛል ውዝግብ የሚነሳባቸውን አካባቢዎችን ለመያዝ “ስልታዊ” በመሆኑ ጥቃቱ ሳይፈጸም አልቀረም ሲሉ ተናግረዋል።
“የማንነት ጉዳይ ሚነሳባቸውን አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ለማድረግ የግድ የእኛን አካባቢ ማጥቃት አለባቸው። በ2013 የተመለከትነውም ይህንን ነው። ስለዚህ ይህን አካባቢ የመቁረጥ፤ ቆርጦ መሀል ላይ ያለን የመንግሥትን መዋቅር የማጥቃት ፍላጎት አለ” ሲሉ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ወረዳው ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በትግራይ ኃይሎች ተይዞ እንደነበር አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል።
ከትግራይ ፀጥታ ቢሮ አቶ አማረ ለዚህ በሰጡት ምላሽ “እኛ ያለንበት ቦታ እና አሁን እየተባለ ባለው ቦታ [አድርቃይ ወረዳ] በጣም ሰፊ ርቀት ነው ያለው። በቀጥታ የሚዋሰን ቦታም አይደለም” ሲሉ ጥቃቱን እንዳላደረሱ ደጋግመው ተናግረዋል።
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል ያሉ ችግሮችን “ግጭት አልባ በሆነ መንገድ ነው ችግሮችን ለመፍታት የምናስበው እንጂ ወደ ግጭት የመግባት ሁኔታ የለንም” ብለዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ በሰጠው መግለጫ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ባደረገው ስምምነት ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል በኩል የአስተዳደር መዋቅር ተዘርግቶላቸው የተጠቃለሉ አካባቢዎችን እስከ ሰኔ 30 እንደሚመልስ ማስታወቁ ይታወሳል።