አስተውይ! :- በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የግፊት ምልክት ስለሆነ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ።
- ከ 7 ወር በኋላ ከማህፀን የሚወጣ ደም አለን?
አስተውይ! :- የእንግዴ ልጁ ቀድሞ ከሆነ፣ ከእንግዴ ልጁ ጀርባ ደም እየፈሰሰ ከሆነ፣ የማህፀን ኢንፌክሽ ካለ እናም ሌሎች ከባድ የሆኑ የጤና እክሎች ምክንያት ስለሚሆን በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ::
- በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት ደም እና ስጋ የመሰለ ነጭ ነገር ከማህፀን መፍሰስ ፣ ከእምብርት በታች ሆድ መቁረጥ፣ የጀርባ መቁረጥ፣ ውሀ የመሰለ ፈሳሽ መፍሰስ ካለ
አስተውይ! :- የውርጃ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የጤና ተቆምን መጎብኘት ግድ ያስፈልግሻል
- ጆሮ መጮህ ፣ ማዞር ፣ ከፍተኛ ድካም ፣ እራስ ምታት፣ ልብ ሲመታ መታወቅ ካለ
አስተውይ! : – እነኝህ የ ደም ማነስ ምልክቶች ስለሆኑ በቶሎ ወደ ጤና ተቆም ሂጂ
- በመጀመሪያዎቹ 4 ወራት ከፍተኛ የሆነ ማስታወክ እና ማቅለሽለሽ ፣ ከ5% በላይ ከእርግዝና በፊት ካለሽ ኪሎ መቀነስ
አስተውይ! :- ይህ (ማቅለሽለሽና ማስታወክ) በአብዛኞቹ እናቶች ላይ ሊታይ የሚችል ችግር ቢሆንም ነገር ግን በጣም ከፍተኛ ሲሆን እና ኪሎ መቀነስ ሲኖር የህክምና እርዳታ ስለሚያስፈልግሽ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ
- የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው ቀንሶብሻልን?
አስተውይ! :- ከ5 ወር በውሀላ አብዛኞቹ እናቶች የልጃቸውን እንቅስቃሴ ማስተዋል ይጀምራሉ ይሁንና የልጅን እንቅስቃሴ የሚቀንሱ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው በጣም ከቀነሰብሽ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች:- ውሀው መቀንስ ወይም ደሞ በጣም መጨመር ሲኖር ፣ ከማህፀን ደም ሲፈስ ፣ ፅንሱ ከአእንግዴ ልጁ ታች ሲሆን ፣ ወይም የአንቺ ክብደት እና የስራ ሁኔታ እንዳይሰማሽ ካደረገ አልያም ደግሞ ልጅሽ እንቅልፍ ላይ ሲሆን ሊሆን ይችላል።… ለሁሉም ግን ሀኪምሽን ማማከሩ እና ምርመራ ማድረጉ ተገቢ ነው።
- ከ 9 ወር በፊት ድንገት በተኛሽበት ፣ ቁጭ ባልሽበት ወይም ስራ ላይ ሆነሽ ውሀ የመሰለ ወይም ሽንት የመሰለ ነገር ‘ፏ ‘ ብሎ ከመሀፀንሽ ከፈሰሰ
አስተውይ!:- ይህ የእንሽርት ውሀ ሰለሆነ ቶሎ ብለሽ ወደጤና ተቋም ሂጂ አለበለዚያ ለተለያዩ አደጋዎች ልትጋለጭ ትችያለሽ ለምሳሌ የህፃኑ እትብት ሊወጣና እና መታፈን ፣ ለመሀፀን ኢንፌክሽን መጋለጥ እና ለደም መፍሰስ ልትጋለጪ ትችያለሽ::
ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት – 0911138054
Join the following telegram channel for more https://t.me/DrDawitMOBGYN